አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
- 1 ኪሎ ግራም ቲላፒያ
- 2 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) በደቃቁ የተከተፈ ቲማቲም
- 1 መካከለኛ ጭልፋ (150 ግራም) የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት
- 1 መካከለኛ ጭልፋ (150 ግራም) የቲማቲም ድልህ
- 12 የሾርባ ማንኪያ (200 ሚሊ ሊትር) ዘይት
- ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጨው
- 1 መካከለኛ የደቀቀ ነጭ ሽንኩርት
- ግማሽ የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ
አዘገጃጀት
- ዓሳውን ካፀዱ በኋላ አምስት ቦታ ከፍሎ በሥጋ መጠፍጠፊያ ጠፍጥፎ የሎሚውን ጭማቂ ላዩ ላይ አርከፍክፎ ማስቀመጥ፤
- ቀይ ሽንኩርቱን በዘይት ካቁላሉ በኋላ የቲማቲም ድልሁንና ነጭ ሽንኩርቱን መጨመር፤
- የተከተፈውን ቲማቲም ጨምሮ ትንሽ ማማሰል፤
- ጨውና ቁንዶ በርበሬ ጨምሮ በደንብ ማማሰል፤
- ዓሳውን ጨምሮ በዝግታ እንዳይፈረካከስ እየተጠነቀቁ በማገላበጥ ማብሰል፤
- ከድንች ጥብስና ከስፒናች ጋር አብሮ ሊቀርብ ይችላል፡፡
- ደብረወርቅ አባተ (ሱ ሼፍ) ‹‹የውጭ ምግቦች አዘገጃጀት›› (2002)