Wednesday, June 12, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊየከተሞች የጐንዮሽ መስፋፋት ሊገታ ነው

የከተሞች የጐንዮሽ መስፋፋት ሊገታ ነው

ቀን:

ከተሞች ወደ ጐን የሚያደርጉት መስፋፋት ለመግታት የሚያስችሉ ዘዴዎች ላይ ጥናት ተካሄደ፡፡

በኢፌዴሪ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል የከተማ ልማት ጥናትና ምርምር ዘርፍ የከተሞች መሬት አጠቃቀም፣ መስፋፋት፣ እንዲሁም የሚፈናቀሉ የአርሶ አደሮች በቂ ካሳ የሚያገኙበትን መንገድ በተመለከተ ሦስት ጥናቶች አጠናቆ፣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡

ካለፈው ሳምንት ዓርብ ጀምሮ ለሁለት ቀናት ውይይት የተደረገባቸው የከተሞች የመልሶ ማልማትና የከተሞች ጥግግት፣ አዲስ አበባን ጨምሮ በአገሪቱ ያሉት ከተሞች ወደ ጎን የሚያደርጉት መስፋፋት በዘፈቀደና በዕቅድ ያልተመራ መሆኑን የሚያሳይ ነበር፡፡ ከተሞች በውስጣቸው ያሉትን ጥቅም ላይ ያልዋሉ ቦታዎችን አሟጦ በመጠቀም በትንንሽ ቦታዎች ሕንፃዎች ለመገንባት የሚያስችሉ የጥናቱ ግኝቶች፣ ለከተማ መሬት አስተዳደር አመራሮች ቀርበዋል፡፡

- Advertisement -

እስካሁን የአዲስ አበባን ጨምሮ ከተሞች ልቅ በሆነ መንገድ ወደ ጎን የሚያደርጉት መስፋፋት ለበርካታ አርሶ አደሮች መፈናቀልና በቂ ካሳ እንዳያገኙ ምክንያት መሆኑን፣ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ዋና ዳይሬክተር አቶ ዓባይ ፀሐዬ ተናግረዋል፡፡

ጥናቱ ከአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ከተሞች የተቀናጀ ማስተር ፕላን ጋር በቀጥታ የተያያዘ እንዳልሆነ የተናገሩት አቶ ዓባይ፣ በአጠቃላይ በአገር አቀፍ ደረጃ ያለውን ችግር ለመፍታት ታስበው የተሠሩ ጥናቶች መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ ከተሞች በውስጣቸው ያለውን ሰፊ መሬት መልሶ ለማልማት፣ የከተማ መስፋፋት የግድ ሲሆን ደግሞ አልሚዎችንና ተፈናቃዮችን ይበልጥ በሚጠቅም መንገድ ለመሥራት የተደረጉ ጥናቶች መሆናቸው ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ያለውን የመስፋፋት ጫና ለመቀነስ፣ በሌሎች ክልሎች የሚገኙ ከተሞች በተለይ ሐዋሳ፣ ባህር ዳር፣ መቐለና ድሬዳዋን ይበልጥ እንዲለሙ ማድረግ ጠቃሚ መሆኑንና ቀደም ብሎ በጥናት የተሰጠውን ምክረ ሐሳብ ግምት ውስጥ ያስገባ እንደሆነ አቶ ዓባይ ገልጸዋል፡፡

በቅርቡ የጥናቶቹ ውጤቶች ተግባራዊ መሆን ሲጀምሩ ሕገወጥ ግንባታዎች፣ የመሬት ዝርፊያና የአርሶ አደሮች ያላግባብ መፈናቀልን ለመከላከል እንደሚጠቅሙ ጠቁመዋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...