Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየምሥራቅ አፍሪካ የጎልፍ ሻምፒዮናና የኢትዮጵያ ተሳትፎ

የምሥራቅ አፍሪካ የጎልፍ ሻምፒዮናና የኢትዮጵያ ተሳትፎ

ቀን:

በዓለም ላይ ከሚዘወተሩ ስፖርቶች መካከል አንዱ ጎልፍ ነው፡፡ ይሁንና ስፖርቱ በአፍሪካ ደረጃ ኢትዮጵያን ጨምሮ በበርካታ አገሮች ሲዘወተር አይስተዋልም፡፡ በዚያው መጠን ደግሞ እንደ ኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ደቡብ አፍሪካና ሞሮኮ የመሳሰሉት የቱሪስት መዳረሻ የሆኑ የአፍሪካ አገሮች ይህንን ስፖርት ለማካሄድ በሚያስችል ሁኔታ ሪዞርቶችንና ሆቴሎችን ያካተተ መሠረተ ልማቶች የተሟሉለት በመሆኑ በስፋት ሲዘወተር እንደሚታይ የዘርፉ ሙያተኞች ይናገራሉ፡፡

ለስፖርቱ ተስማሚ ሁኔታዎችን በማነቻቸት ጎብኚዎች ወደየአገሮቻቸው እንዲመጡ፣ በአገሮቹ የስፖርት ቱሪዝም እንዲዳብር ስለማድረጉም የሚናገሩ አሉ፡፡ ጎልፍ በኢትዮጵያ ከቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ መዘውተር የጀመረ ቢሆንም፣ ነገር ግን የሚገባውን ያህል ትኩረት ማግኘት ባለመቻሉ  እንዲቀጭጭም ምክንያት ሆኖ ቆይቷል፡፡ ይህንኑ መነሻ በማድረግ ስፖርቱን በአገሪቱ በሚገባው ደረጃ ተስፋፍቶ፣ በስፖርቱም የሚሰጠውን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ተጠቃሚ መሆን ይቻል ዘንድ እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡ ከጥቅምት 17 እስከ 19 ቀን 2009 ዓ.ም. ድረስ በአገሪቱ ለመጀመርያ ጊዜ በአዲስ አበባ የተካሄደው የምሥራቁ አፍሪካ ጎልፍ ሻምፒዮና ለዚህ አንዱ ማሳያ እንደሆነ ነው የኢትዮጵያ ጎልፍ አሶሴሽን ፕሬዚዳንት አቶ ነብዩ ሳሙኤል ለሪፖርተር የገለጹት፡፡

ቅዳሜ ጥቅምት 19 ቀን 2009 ዓ.ም. የተጠናቀቀው የምሥራቅ አፍሪካ ጎልፍ ሻምፒዮና፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለስድስት የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች ኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ሩዋንዳና ቡሩንዲ ተሳትፈውበታል፡፡ ኬንያና ኡጋንዳ በእኩል 16 ነጥብ የሻምፒዮናው አሸናፊዎች ሲሆኑ፣ አስተናጋጇ ኢትዮጵያ ሦስተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ሻምፒዮናውን በእኩል 16 ነጥብ ያጠናቀቁት ኡጋንዳና ኬንያ ቢሆኑም፣ ነገር ግን የኡጋንዳ ቡድን የዘንድሮውን ጨምሮ ለተከታታይ ሦስት ዓመታት ሻምፒዮን በመሆኑና በውድድሩ ደንብና መመርያ መሠረት ሻምፒዮናውን ሦስት ጊዜ አከታትሎ የወሰደ አገር ዋንጫውን ለግሉ ያደርጋል በሚለው መሠረት፣ የኡጋንዳ ቡድን አሸናፊ እንዲሆን ተደርጎ ዋንጫውንም የግሉ ማድረጉ የአሶሴሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ነብዩ ተናግረዋል፡፡

እንደ አቶ ነብዩ በምሥራቅ አፍሪካ አገሮች እንደ ኬንያና ኡጋንዳ እንዲሁም ታንዛኒያ የጎልፍ ስፖርት በስፋትና በጥራት የሚዘወተርባቸው አገሮች ናቸው፡፡ ስፖርቱን ለበርካታ ዓመታትም በማዘውተር እንደሚታወቁ ጭምር አስረድተዋል፡፡ በተለያዩ የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች የጎልፍ ሻምፒዮና ለበርካታ ዓመታት የተካሄደ ሲሆን፣ በነዚህ ዓመታት የኢትዮጵያ ተሳትፎ የዘንድሮው ለአራተኛ ጊዜ ነው፡፡

እንደ ኃላፊው ከሆነ፣ በኢትዮጵያ ጎልፍ ሲዘወተር የቆየው ባለዘጠኝ ጉድጓድ (ኮርስ) ተብሎ በሚታወቀው ብቻ እንደነበር፣ አሁን ግን ባለ 18 ጉድጓድ (ሙሉ ኮርስ) የማዘውተሪያ ግንባታ ተጠናቋል፡፡ ስፖርቱን በአገሪቱ ለማስፋፋት እየተደረገ ባለው እንቅስቃሴም፣ ኢትዮጵያ የምሥራቅ አፍሪካ ጎልፍ አሶሴሽን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ተደርጋ ለቀጣዩ አራት ዓመት መመረጧንም አቶ ነብዩ ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...