Sunday, December 3, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየኤርትራ አየር ኃይል የመለማመጃ አውሮፕላን በኢትዮጵያ ተዋጊ ጄቶች ከለላ ተደርጎለት ማረፉ ተጠቆመ

የኤርትራ አየር ኃይል የመለማመጃ አውሮፕላን በኢትዮጵያ ተዋጊ ጄቶች ከለላ ተደርጎለት ማረፉ ተጠቆመ

ቀን:

በሁለት ነባር አብራሪዎች ወደ ኢትዮጵያ የኮበለለው የኤርትራ አየር ኃይል መለማመጃ አውሮፕላን፣ ከድንበር ጀምሮ በኢትዮጵያ አየር ኃይል ተዋጊ ጄቶች ከለላ ተደርጎለት መቐለ እንዲያርፍ መደረጉ ተጠቆመ፡፡

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. ማለዳ በመቐለ አየር ኃይል ጣቢያ እንዲያርፍ የተደረገው ይኼው አውሮፕላን “Zlin-143-102” የሚባል ሲሆን፣ በሁለት ነባር የኤርትራ አየር ኃይል አብራሪዎች ነው ኢትዮጵያ የገባው፡፡ በሑመራ በኩል ባለው ድንበር አቋርጦ መምጣቱን ለትግራይ ክልል መንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

በተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ከኤርትራ የኮበለሉት ሁለት አውሮፕላኖች መሆናቸው የቀረበው ዘገባ የተሳሳተ መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

የኤርትራ ቀይ ባህር አፋር ነፃ አውጪ ድርጅት ቃል አቀባይ አቶ ነስረዲን አህመድ ዓሊን ዋቢ በማደረግ ቀዳሚ ዘገባ ያቀረበው አሶሼትድ ፕሬስ፣ መቐለ እንዲያርፉ የተደረጉት አውሮፕላኖች ሁለት መለስተኛ መጠን ያላቸው መሆናቸውን ዘግቦ ነበር፡፡

ለልምምድና ለሥልጠና የሚውለውን የኤርትራ አየር ኃይል አውሮፕላን ወደ ኢትዮጵያ እንዲኮበልል ያደረጉት ሁለት አብራሪዎች አፈወርቂ ፍስሐዬና መብራህቱ ተስፋማርያም መሆናቸውን፣ አብራሪዎቹ በኤርትራ አየር ኃይል ለረጂም ጊዜ ያገለገሉና ከፍተኛ ልምድ ያላቸው መሆናቸውን ምንጮች ለሪፖርተር ጠቁመዋል፡፡

እንደ ምንጮች ገለጻ፣ አውሮፕላኑ ከኤርትራ እንዲኮበልል የተደረገው በሑመራ በኩል ነው፡፡ መቐለ እንዲያርፍ የተደረገው ከድንበር ጀምሮ ጥቃት እንዳይደርስበት በኢትዮጵያ አየር ኃይል ሁለት ተዋጊ ጄቶጅ ታጅቦ ነበር፡፡

በአካባቢው የነበሩ ዓይን እማኞች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ አውሮፕኑ መቐለ በሚያርፍበት ወቅት በጣም ዝቅ ባለ ከፍታ የሚበሩ የጦር አውሮፕላኖች ከፍተኛ ድምፅ ባልተለመደ ሁኔታ ተሰምቷል፡፡

የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረ መስቀል ግን ዘገባው መሠረት የሌለው ውሸት መሆኑን ለቢቢሲ ቢናገሩም፣ አብራሪዎቹ በፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሚመራውን መንግሥት በመቃወም መኮብለላቸው ታውቋል፡፡ አንድ የኤርትራ አውሮፕላን ወደ ኢትዮጵያ ኮብልሎ ሲገባ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ የኤርትራ አብራሪዎች የጦር አውሮፕላኖችን ይዘው ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ መኮብለላቸው ይታወሳል፡፡ ባለፈው ዓመት የኢትዮጵያ አየር ኃይል ሚ35 ሔሌኮፕተር አብራሪ ከድሬዳዋ አሰብ መግባቱ አይዘነጋም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...