Saturday, April 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -

የተመረጡ ፅሑፎች

የአላና ፖታሽ ነገር

በዓለም አቀፍ ደረጃ በፖታሽ አምራችነት ከሚጠቀሱ ኩባንያዎች መካከል አንዱ የሆነውና አይሲኤል የተባለው የእሥራኤል ኩባንያ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ለተመሳሳይ ሥራ ከገባ አንድ ዓመት ሊጠጋው ነው፡፡

ኩባንያው በፖታሽ ሀብት ክምችታቸው ከሚጠቀሱ ጥቂት የዓለማችን አገሮች አንዷ ወደሆነችው ኢትዮጵያ የገባው በአፋር ክልል ፖታሽ ለማምረት ፈቃድ አግኝቶ ሲንቀሳቀስ ከነበረው አላና ፖታሽ ከተባለው ኩባንያ አክሲዮኖችን ጠቅልሎ በመግዛት ነው፡፡ ግዥውም ከኢትዮጵያ ውጭ የተፈጸመ ነው፡፡

አላና ፖታሽ በኢትዮጵያ የአምራችነት ፈቃድ ወስዶ እንቅስቃሴ የጀመረው ከስድስት ዓመታት በፊት ነበር፡፡ ኩባንያው እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ በተመለከተ በተደጋጋሚ ይፋ ያደረጋቸው መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ ከፍተኛ የፖታሽ ክምችት ማግኘቱን ነው፡፡ ይህንን በጥናት ጭምር ማረጋገጡን አስታውቋል፡፡

ወደ ማምረት ሥራ ለመግባት መቃረቡን በመግለጹ ከዛሬ ነገ ወደ ሥራ ይገባል እየተባለ በጉጉት ሲጠበቅ እንደነበርም የምናስታውሰው ነው፡፡ በመጀመርያው የምርት ዘመን በዓመት አንድ ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ የፖታሽ ምርት ለውጭ ገበያ ለማቅረብና በየዓመቱም መጠኑን ለማሳደግ የሚችልበት ዕድል እንዳለም አስነግሯል፡፡ ከኩባንያው ሥሌት አንፃር ማዕድኑ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ማግኛ ሊሆን ይችላል የሚል እምነት አሳደረ፡፡ ይህንኑ መልካም ዕድል በመመልከትም መንግሥት የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱ አይዘነጋም፡፡ በተለይ ምርቱን በቀላሉ ወደ ወደብ ለማጓጓዝ ያስፈልጋል የተባለውን መንገድ ወደ መገንባት የገባውም ይህንኑ ተስፋ በማድረግ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ አላና ፖታሽ ወደ ምርት ሳይገባ፣ የጀመረውን ኢንቨስትመንትም ዳር ሳያደርስ የአላና አክሲዮኖች ለእሥራኤሉ ኩባንያ በሽያጭ ተላልፈው አላና ፖታሽ ከጨዋታው ወጣ፡፡ ቀደም ብሎም ቢሆን 16 በመቶ የአክሲዮን ድርሻ የነበረው የእሥራኤሉ አይሲኤል ኩባንያ፣ ቀሪዎቹን አክሲዮኖች ከ157 ሚሊዮን ዶላር በላይ በመክፈል የፖታሽ ልማቱ ባለቤት ሆነ፡፡ ይህንን ዜናም ሁሉም ሰማው፡፡ የአላና መውጣት ብዙ ቢያነጋግርም የእስራኤሉ ኩባንያ የተጀመረውን ሥራ ዳር ለማድረስ ይችላል ተባለ፡፡ ኩባንያው ጠቅልሎ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባም ያካበተውን ልምድ ተጠቅሞ ለዓመታት ተስፋ የተደረገበትን የፖታሽ ምርት በማውጣት ኤክስፖርት ያደርጋል የሚል ተስፋ ተንሰራፋ፡፡ ምርቱን በቀላሉ አውጥቶ ኢትዮጵያን ፖታሽ ላኪ አገር ያደርጋታል የሚል እምነት ያደረባቸው ወገኖች ሁኔታውን በመልካም አይተውታል፡፡

ይሁን እንጂ የእሥራኤሉ ኩባንያ ሥራ ጀመረ ከተባለ በኋላ እንደ ታሰበው  አልተጓዘም፡፡ ይህ የሆነው አቅም አንሶት ሳይሆን ምቹ የሥራ ከባ ባለማግኘቱ ነው ተባለ፡፡ በእስራኤሉ ኩባንያና በአላና መካከል የተደረገው ግዥና ሽያጭ ከኢትዮጵያ ውጭ የተፈጸመ፣ ሒደቱም ከኢትዮጵያ መንግሥት ዕውቅና ውጪ ነው በማለት የእሥራኤሉ ኩባንያ ኢትዮጵያ በመግባት ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲያደርግ ተፈቅዶለት ሲሠራ ቆይቷል፡፡ በቅርቡ ግን ባልታሰበ መንገድ የእሥራኤሉ ኩባንያ በኢትዮጵያ የጀመረውን ሥራ ማቋረጡን ገለጸ፡፡ ይህ ዜና መጥፎ ነበር፡፡ ኢንቨስትመንቱን ለማቋረጡ የሰጠው ምክንያትም አነጋጋሪ ሆነ፡፡ ለኩባንያው ሥራ ማቋረጥ የተጠቀሱት ምክንያቶች በቀላሉ ሊፈቱ ይችሉ እንደነበር ሲታሰብ ደግሞ የውጭ ኢንቨስተሮች የሚስተናገዱበትን መንገድ አጠያያቂ ማድረጉ አይቀርም፡፡

በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ኦዲት መሠረት አላና ፖታሽ አፋር ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተባለው ድርጅት 1.2 ቢሊዮን ብር (55 ሚሊዮን ዶላር) ታክስ እንዲከፍል ተወሰነ፡፡ ባለሥልጣኑ መከፈል አለበት ካለው ታክስ ውስጥ ልከፍል የማይገባኝ ታክስ ተቀላልቋል በማለት የእሥራኤሉ ኩባንያ ተከራከረ፡፡ ልከፍል የማልችለው፣ የተጠየኩት ታክስ በኢትዮጵያም ሆነ በዓለም አቀፍ ሕግ መከፈል የሌለበት ነው አለ፡፡ በዚህ መካከል ነበር ኩባንያው ወጥቻለሁ ያለው፡፡

ልከፍል የሚገባኝን ታክስ ግን እከፍላለሁ ማለቱመወ ተሰምቷል፡፡፡ ለማንኛውም የተፈጠረው ችግር ይህ ብቻ ከሆነ፣ ነገሩን በቀላሉ ማስተካከል ይቻል አልነበረም ወይ? አንዳንዴ ሰጥቶ መቀበል የሚለውን መርኅ መከተል ግድ ሊሆን ይችላል፡፡ በቶሎ ለመፈጸም ያለው ቁርጠኝነት ቀዝቃዛ በመሆኑ ያመጣው ነው ሊባል ይችላል፡፡ በተለይ ኩባንያው ላልማ ስል ጥያቄን በአግባቡ ተቀብሎ ፈጣን ውሳኔ የሚሰጠኝ በመጥፋቱ ነው የወጣሁት ማለቱ ትክክል ከሆነ፣ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚመለከታቸው አካላት ጥያቄውን በአግባቡ አላስተናገዱም ማለት ነው፡፡

ኩባንያው ሕገወጥ መስመር ተከትሎ ከሆነም መንግሥት ዕርምጃ ቢወስድበት ትክክል ነው፡፡ ነገር ግን ኩባንያው ችግር አለብኝ ብሎ እየተናገረ መልስ ለመስጠት መዘግየቱ ለምን? ተብሎ መጠየቅ አለበት፡፡ በተለይ የኩባንያው ሥራዬን አቁሜያለሁ ካለ በኋላ የኩባንያዎቹ የባንክ አካውንቶች እንዲታገዱ የሚለው ነገር ከታመነበትስ ፕሮጀክቱ እንዳይስተጓጎል ቀድሞ ለምን አልታሰበም? ጉዳዩ የሚመለከተው ሚኒስቴር ፈጣን ምላሽ በመስጠት አካውንቶቹ እንዲንቀሳቀሱ ማድረግ ችሏል፡፡ ችግሩ ግን አካውንቱ እንዲንቀሳቀስ እንደተወሰደው ፈጣን ዕርምጃ ሁሉ ኩባንያው ኢትዮጵያን እንዳይለቅ ይመለሱልኝ ያላቸውን ጥያቄዎች ፈጥኖ መመለስ ይገባው እንደነበር ነው፡፡ መልሱ አወንታዊውም ይሁን አሉታዊ ፈጣን መልስ ቢያገኝ ብዥታው አይፈጠርም ነበር፡፡ ስለዚህ ችግሩ ፈጣን ምላሽ ያለመስጠት ያመጣው ነው ሊባል ይችላል፡፡

ለዓመታት ተለፍቶበት መንግሥትም የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ ያለበት ፕሮጀክት ከሆነ በቢሊዮን የሚቆጠር የውጭ ምንዛሪ ያስገኛል፡፡ በጥቅሉ ግን እንዲህ ያሉ አጋሚዎች ለምን ተፈጠሩ ብሎ ነገሮችን በጥልቀት መመልከት ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይፈጠሩ ይጠቅማል፡፡

ችግሩ ለዓመታት ሲንከባለል የመጣና ከሁለት ኩባንያዎች ስምምነት በፊት መሠራት የነበረባቸው የቤት ሥራዎች ሳይሠሩ መቆየታቸውን ለመገመት ይቻላል፡፡ ስለዚህ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ምን ሲሠሩ ነበር ብሎ መጠየቅም ተገቢ ነው፡፡

ለማንኛውም አንዳንዴ በቸልታ የታዩ ጉዳዮች በኋላ ዋጋ ሊያስከፍሉ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ መንግሥት ይህ የፖታሽ ፕሮጀክት በእርግጥም ጠቃሚ ነው ብሎ ካሰበ የኩባንያው ለምን እንደወጣ ሊፈተሽ ይገባል፡፡ ችግሩ ኩባንያው መውጣት ብቻ ሳይሆን ለተመሳሳይ ኢንቨስትመንት ለመሰማራት የሚፈልጉትንም ሆነ የውጭ ኩባንያዎች ላይ ሊያሳርፍ የሚችለውን ተፅዕኖ ማሰብ ብልህነት ነው፡፡ የኩባንያው ጥያቄ ከኢትዮጵያ ሕግ ጋር የሚቃረን ሆኖ ከተገኘም ይህንኑ አሰሳውቆ በሕግ አግባብ መሸኘት ከዝምታ ይሻሻል፡፡

ልከፍል የማይገባኝ ታክስም ተቀላቅሏል ብሎ የእስራኤሉ ኩባንያ ተከራከረ፡፡ ልከፍል የማልችለውም የተጠየቀኩት ታክስ በኢትዮጵያም ሆነ በዓለም አቀፍ ሕግ መከፈል የሌለበት ነው አለ፡፡ በዚህ መሀል ነው እንግዲህ ኩባንያው ወጣሁ ያለው፡፡

Latest Posts

- Advertisement -

ወቅታዊ ፅሑፎች

ትኩስ ዜናዎች ለማግኘት