አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
- 4 መካለኛ ጭልፋ (600 ግራም) የደቀቀ ቀይ ሽንኩርት
- 4 የቡና ሲኒ (200 ግራም) የፉርኖ ዱቄት
- 1 መካከለኛ ጭልፋ (150 ግራም) ባሮ ሽንኩርት
- 2 ሊትር ትኩስ ወተት
- 4 የሾርባ ማንኪያ (100 ግራም) የገበታ ቅቤ
- 1 የሻይ ማንኪያ ጨው
- 1 የሻይ ማንኪያ ነጭ ቁንዶ በርበሬ
- 1 ሊትር ሙቅ ውኃ ወይም የአትክልት መረቅ
- 6 መካከለኛ ጭልፋ (600 ግራም) ክብ ተደርጎ በስሱ የተቆረጠ ቀይ ሽንኩርት
አዘገጃጀት
- ባሮ ሽንኩርቱን፣ የደቀቀውን ቀይ ሽንኩርትና ቅቤውን ብረት ድስት ውስጥ ጨምሮ ማቅለጥና ማሞቅ፤
- በነጩ ማቁላላት፤
- ዱቄቱን ጨምሮ አሸዋማ መልክ እስኪያወጣ ማቁላላት፤
- በዝግታ መረቅ ወይም ሙቁን ውኃ እየጨመሩ ማቅጠን፤
- ለግማሽ ሰዓት ማብሰልና ጨውና ቁንዶ በርበሬውን አስተካክሎ ማውጣት፤
- በዘርዛራ ማጥለያ አጥልሎ አንዴ ማፍላት፤
- ወተቱን ጨምሮ ካዋሃዱ በኋላ ማውጣት፤
- ክብ ተደርጎ በስሱ የተቆረጠውን ቀይ ሽንኩርት በንፁህ አቡጀዲ ጠቅለል፣ ጠቅለል ካደረጉ በኋላ ዱቄቱ ላይ ለወስ አድርጎ እያራገፉ በጋለ ዘይት መጥበስ፤
- ወርቃማ መልክ ሲያወጣ ማውጣት፤
- ለገበታ ሲፈለግ ሾርባው ላይ የተጠበሰውን ሽንኩርት ነስንሶ ማቅረብ፡፡
- ደብረወርቅ አባተ (ሱ ሼፍ) ‹‹የውጭ ምግቦች አዘገጃጀት›› (2002)