Monday, December 5, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መብቶች እንዳይጣሱ እየሠራሁ ነው አለ

  ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መብቶች እንዳይጣሱ እየሠራሁ ነው አለ

  ቀን:

  የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በአገሪቱ በታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት በዜጎች ሰብዓዊ መብት ላይ ጥሰት እንዳይፈጸም እየተከታተለ እንደሆነ አስታወቀ፡፡

  የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ዶ/ር አዲሱ ገብረ እግዚአብሔር ይህን ያስታወቁት፣ ሐሙስ ጥቅምት 17 ቀን 2009 ዓ.ም. ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ስለኮሚሽኑና የእንባ ጠባቂ ተቋም የ2009 በጀት ዓመት የመልካም አስተዳደር ንቅናቄ ዕቅድ ላይ በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ነው፡፡

  ኮሚሽኑ በሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ጉዳይ ላይ አተኩሮ እንደሚሠራ ገልጸው፣ ‹‹እርግጥ ነው ኮማንድ ፖስቱ ባለው አደረጃጀትና በቀረፀው የሕግ ማዕቀፍ ውስጥ ይህ እንደሚከበር ግልጽ አድርጓል፡፡ እኛ ደግሞ ይህን የመከታተል ኃላፊነት አለብን፡፡ ተጥሶም ሲገኝ ለሚመለከተው አካል የማቅረብ ግዴታ አለብን፡፡ እርሱን አቀናጅተን ለመሄድ እየሠራን ነው፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

  በተጨማሪም በሕግ ፊት መጠየቅ ያለበቸውም በአግባቡ የመጠየቃቸውን፣ የታሰሩም ካሉ የእነዚህ ዜጎች ሰብዓዊ መብት ተከብሮ በማረሚያ ቤት የሚቆዩበትንና ጉዳያቸው በአግባቡ የሚታይበትን፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳይኖር መከታተልም የኮሚሽኑ ኃላፊነት እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

  ተቋሙ በሕገ መንግሥቱ መሠረት መቋቋሙን የገለጹት ኮሚሽነሩ፣ ‹‹በዚህም መሠረት የዜጎች ሰብዓዊ መብቶች መከበራቸውን የመከታተል፣ የመፈተሽና የማጥናት ኃላፊነት አለብን፡፡ ይህንን ሥራችንን አሁንም አጠናክረን እየቀጥልን ነው፤›› በማለት ገልጸዋል፡፡

  ‹‹ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር ተያይዞ በአዋጁ የተቀመጠው እንደተጠበቀ ሆኖ በዋናነት ግን የሰዎች የሰብዓዊ መብት የትም ቦታ መከበር አለበት፤›› በማለትም አክለዋል፡፡

  ኮሚሽነሩ ከአዋጁ ጋር በአንድ ላይ ለመጓዝ የሚመጥን ዕቅድ ለመንደፍ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጋር ውይይት ማካሄዳቸውንም ጠቁመዋል፡፡ በዚህም መሠረት የኮሚሽኑ መርማሪዎች ይህን ታሳቢ ያደረገ አቅጣጫና ግንዛቤ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል፡፡

  ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ደንብና መመርያን ታሳቢ ባደረገ ሁኔታ ሆኖም ግን ከተቋቋምንበት አዋጅ አንፃር አዋጁን መሠረት ያደረገ ሥራ እንዲሠራ፣ ጥሰትም ሲገኝ ለሚመለከተው አካል ፈጥነን የማቅረብና የመፍታት አካሄድ እንዲኖር እየሠራን እንገኛለን፤›› ብለዋል፡፡

  ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈጻጸም ጋር በተያያዘ ለኮሚሽኑ ከምሥራቅ ሐረርጌና ከመቂ አከባቢ ሁለት ቅሬታዎች መቅረባቸውን የጠቆሙት ኮሚሽነሩ፣ ቅሬታዎቹን ለማጣራት የኮሚሽኑ ባለሙያዎች ወደ ሥፍራዎቹ መላካቸውንም ገልጸዋል፡፡ 

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ዳግም ነፍስ የዘራው የተማሪዎች ማርች ባንድ

  የሙያው ፍቅር ያደረባቸው ገና በልጅነታቸው ነው፡፡ በ1970ዎቹ መጀመርያ፣ ለቀለም...

  በስንደዶና ሰበዝ የተቃኘው ጥበብ

  በአንዋር አባቢ ተወልዳ ያደገችው መሀል አዲስ አበባ አራት ኪሎ ነው፡፡...

  አዲስ ጥረት የሚጠይቀው  ኤችአይቪ  ኤድስን  የመግታት  ንቅናቄ

  ‹‹ኤችአይቪ በመላው ዓለም  በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያጠቃ ዋነኛ የሕዝብ...

  የኅትመት ብርሃን ያየው ‹‹የቃቄ ወርድዎት›› ቴአትር

  ከአራት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ ይታይ...