Tuesday, December 5, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናለአዲስ አበባ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ ተሾመ

ለአዲስ አበባ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ ተሾመ

ቀን:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ የነበሩትን አቶ ለዓለም ተሠራ መልቀቂያ ተቀብለው፣ ለአቶ ሀርጋሞ ሀማሞ አዲስ ሹመት ሰጡ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2008 ዓ.ም. ከተማውን በድጋሚ ሲያደራጅ፣ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮን ተረክበው ከሁለት ዓመት ለበለጠ ጊዜ የመሩት አቶ ለዓለም በጤና ምክንያት መቀጠል ባለመቻላቸው መልቀቂያ አስገብተዋል፡፡

ከንቲባ ድሪባ የአቶ ለዓለምን ጥያቄ በመቀበል ለአቶ ሀርጋሞ ሹመት ሰጥተዋል፡፡ አቶ ሀርጋሞ ማክሰኞ ታኅሳስ 10 ቀን 2010 ዓ.ም. ከአቶ ለዓለም ቢሮውን ተረክበው በይፋ ሥራቸውን መጀመራቸው ታውቋል፡፡

ከደቡብ ክልል ይርጋለም የተገኙት የደኢሕዴን አመራር የሆኑት አቶ ሀርጋሞ ወደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከመምጣታቸው በፊት፣ የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ምክትል ዳይሬክተርና የአካዳሚ ዘርፍ ኃላፊ ሆነው ሠርተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በመሆን፣ በተለይ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል ሆነው ሠርተዋል፡፡

ከዘጠኝ ወራት በፊት አቶ ሀርጋሞ ከመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ወደ አዲስ አበባ የመጡ ሲሆን፣ በመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ከሦስት ምክትል ሥራ አስኪያጆች አንዱ በመሆን የፕላንና ፕሮግራም ዘርፉን መርተዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት አቶ ሀርጋሞ በዘርፈ ብዙ ችግሮች የተተበተበውን የአዲስ አበባ መሬት የተረከቡ ሲሆን፣ ቢሮአቸውን ከመረከባቸው በፊት ዓርብ ታኅሳሰ  6 ቀን 2010 ዓ.ም. ከአቶ ለዓለም ጎን ተቀምጠው ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች ጋር በመሬት ሥሪት ችግሮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በቀድሞ ቢሮ ኃላፊ አቶ ለዓለም በዴሊቨሪ ዩኒት ፕሮግራም በመሬት ዘርፍ 18 ችግሮች ተለይተዋል፡፡ ‹‹በተለይ የመልሶ ልማት ፕሮጀክቶችን በዕቅድ መሠረት ለማካሄድ ብዙ መሥራት ይገባናል፡፡ መሬት አጥረው ያስቀመጡ አልሚዎች ላይ ዕርምጃ በመውሰድ ረገድ ሰፊ ሥራ ማከናወን አለብን፤›› ሲሉ አቶ ለዓለም ለተሰብሳቢዎች ሲገልጹ፣ አቶ ሀርጋሞም ማስታወሻ ይዘዋል፡፡

አቶ ሀርጋም በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፣ በመሬት ዘርፍ የተንሰራፋውን ኪራይ ሰብሳቢነት (ሙስና) በመዋጋት ሒደት የከተማው ነዋሪዎች ከቢሮው ጋር እንዲሠለፉ ጠይቀዋል፡፡

የአቶ ሀርጋሞ የትምህርት ታሪካቸው ከከተማ ልማት ጋር የሚገናኝ ነው፡፡ በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ለ11 ዓመታት ኧርባን ፕላኒንግ ያስተማሩት አቶ ሀጋርሞ፣ በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ዝግጅትም የተወሰነ ተሳትፎ ነበራቸው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...