Wednesday, June 29, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ያላትን ልዩ ጥቅም ለመወሰን በተረቀቀው አዋጅ ላይ ሕዝባዊ...

  ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ያላትን ልዩ ጥቅም ለመወሰን በተረቀቀው አዋጅ ላይ ሕዝባዊ ውይይት ተጠራ

  ቀን:

   የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትሕና አስተዳደር እንዲሁም የከተማና ኮንስትራክሽን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ያላትን ልዩ ጥቅም ለመወሰን የተረቀቀውን የሕግ ሰነድ በዝርዝር ለመመልከት ሕዝባዊ ውይይት ጠሩ።

  ሕዝባዊ የውይይት መድረኩ የተጠራው ለፊታችን ዓርብ ታህሳስ 13 ቀን 2010 ዓ.ም. መሆኑን፣ የሕግ ፍትሕና አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር አቶ ጴጥሮስ ወልደ ሰንበት ለሪፖርተር ገልጸዋል።

  ውይይቱ የሚካሄደው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አዳራሽ እንደሚሆንና በጉዳዩ ላይ መሳተፍና አስተዋጽኦ ማድረግ የሚፈልግ ማንኛውም ኢትዮጵያዊገኘት እንደሚችልም አስረድተዋል። ረቂቅ አዋጁ ለፓርላማው የቀረበው ለክረምት ዕረፍት ሊበተን ሁለት ቀናት ሲቀሩት በመሆኑ በጥድፊያ መፅደቅ አይገባውም ተብሎ፣ 2010 ዓ.ም. የሥራ ዘመን መተላለፋን በወቅቱ መዘገባችን ይታወሳል።

  ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ያላትን ልዩ ጥቅም ለመወሰን የቀረበው ረቂቅ አዋጅ አስገዳጅ እንዲሆን የኦሕዴድ የፓርላማ አባላት በወቅቱ አስተያየት በመስጠት፣ ለዝርዝር ዕይታ የሚመራለት ቋሚ ኮሚቴ ያነሱትን አስተያየት እንዲያጤን አሳስበው ነበር። የረቂቅ አዋጁ የተለያዩ አንቀጾች የኦሮሚያን ጥቅም የሚያስከብሩ ሳይሆን፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍላጎት ላይ የተመሠረተ የሚመስሉ አንቀጾችን የያዘ በመሆኑ አስገዳጅ ሊሆን ይገባል በማለት የክርክር ነጥቦችን አንስተዋል።

  ‹‹የኦሮሞ ሕዝብ ማንነት የሚያንፀባርቅ አሻራ በከተማው ውስጥ በቋሚነት እንዲኖር፣ ከክልሉ ሕዝብ ጋር በተያያዙ ታሪካዊ ክስተቶች ስም መታሰቢያዎች እንዲኖሩ አመቺ የሆኑ እንደ አደባባዮች፣ ጎዳናዎች፣ ሠፈሮችና የመሳሰሉት ቦታዎች እንዳስፈላጊነቱ በቀድሞ የኦሮሞ ስማቸው እንዲጠሩ ይደረጋል፤›› የሚለውን የረቂቅ አዋጁ አንቀጽ 6(2) አስገዳጅ መሆን አለበት የሚለው ከተነሱት ነጥቦች መካከል አንዱ ነበር።

  በሌላ በኩል በረቂቁ የተቀመጡትን የኦሮሞ ልዩ ጥቅሞች ለኦሮሞ ብሔር ተወላጆች ለማቅረብ እንዲቻል አፋን ኦሮሞ በከተማ አስተዳደሩ የሥራ ቋንቋ ሆኗል መባሉን የኦሕዴድ የፓርላማ አባላት የተቀበሉ ቢሆንም፣ የሥራ ቋንቋ እስከሆነ ድረስ እንደ አማርኛ በሁሉም የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት እንዲሰጥ የሚል የማሻሻያ ነጥብ አንስተው ነበር። በተጨማሪም በከተማዋ በመንግሥት የሚሠራጩ የመገናኛ ብዙኃን በአፋን ኦሮሞ ጭምር የሚጠቀሙበት ሁኔታ ይኖራል የሚለውን የረቂቁን አንቀጽ 6(5) አስገዳጅ እንዲሆን የማሻሻያ ሐሳብ አቅርበዋል።

  ከአካባቢ ብክለት የሚጠብቅ መብትን አስመልክቶ በተቀመጠው የረቂቁ አንቀጽ ላይ ጉዳት የደረሰባቸው ካሳ እንዲያገኙ ቢደነገግም፣ ጉዳቱን ባደረሰው ላይ ቅጣት እንዲጥል ጠይቀዋል፡፡ ረቂቁ በሰጠው ትርጓሜ የአዲስ አበባ ከተማ ወሰን ማለት የከተማው አስተዳደር ከኦሮሚያ ክልል ጋር በሚያደርገው ስምምነት ተወስኖ ምልክት የተደረገበት ወሰን እንደሆነ ተገልጿል፡፡ በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ ማለት ፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን መሆኑ ተመልክቷል፡፡

  የምክር ቤቱ አባል አድሃኖ ኃይሌ (/) ይህ ዞን የት ድረስ እንደሆነ በአዋጁ እንዲካተት የሚል ሐሳብ ማቅረባቸውን መዘገባችን አይዘነጋም።

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ብልፅግና ሸኔን ከማጥፋት ውጪ አማራጭ እንደሌለ አቅጣጫ ማስቀመጡን አስታወቀ

  ካለፈው ሳምንት መጨረሻ አንስቶ የማዕከላዊና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴዎች ውይይት...

  የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ የፓርላማውን ሥልጣን በመጣስ ዳኞችን ሰይሟል የሚል ቅሬታ ቀረበበት

  የአማራ ክልል ዳኞች ማኅበር የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ...

  ለደን ውጤቶች የተሰጠው ዝቅተኛ ትኩረት ሊገኝ የሚገባውን የውጭ ምንዛሪ ማሳጣቱ ተነገረ

  በኢትዮጵያ የደን ውጤቶች ለሚባሉት ዕጣን፣ ሙጫ፣ ከርቤና ሌሎችም የወጪ...

  የወንጀል ሕግ ሥነ ሥርዓት ረቂቅ የፖሊስን ሥልጣን ይጋፋል የሚል ትችት ቀረበበት

  ላለፉት 15 ዓመታት በዝግጅት ላይ የቆየው የወንጀል ሕግ ሥነ...