የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት (ጨፌ) ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ባካሄደው አምስተኛ የሥራ ዘመን ሁለተኛ አስቸኳይ ስብሰባ፣ በቅርቡ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡትን አቶ ለማ መገርሳ የክልሉ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟል፡፡ አቶ ለማ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አማካይነት ቃለ መሃላ ከፈጸሙ በኋላ፣ የክልሉን መንግሥት ካቢኔ አባላት ለምክር ቤቱ አቅርበው አፀድቀዋል፡፡ በአዲሱ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቅራቢነት ሹመታቸው የፀደቀላቸው ተሿሚዎች 21 ሲሆኑ፣ ከእነሱም ውስጥ 16 የሚሆኑት ከዚህ ቀደም በካቢኔው ውስጥ ያልሠሩ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ ከመካከላቸውም ስምንቱ የኦሕዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት አለመሆናቸውን፣ ከተሿሚዎቹ ውስጥ ደግሞ ሦስቱ የኦሕዴድ አባል እንዳልሆኑ ተሰምቷል፡፡ የማነ ናግሽ በአዲሱ የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት ሹመት ላይ ያጠናቀረውን ዘገባ ለመመልከት እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡