Sunday, April 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምርጫ ዕጩዎች እየታወቁ ነው

ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምርጫ ዕጩዎች እየታወቁ ነው

ቀን:

– ኃይሌ ገብረሥላሴ ለፕሬዚዳንትነት ከታጩት አንዱ ነው

      በኢትዮጵያ በተለይም በአትሌቲክሱ ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዝናና ክብር ያተረፉ አትሌቶች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ይሁንና ራሳቸውን ከውድድር ያገለሉትም ሆነ በመወዳደር ላይ የሚገኙት አትሌቶች ትኩረት ሰጥተው ሲንቀሳቀሱ የሚስተዋለው በሆቴልና መሰል ኢንቨስትመንት ላይ ካልሆነ ስፖርቱን በማገልገል ረገድ ምንም ዓይነት ድርሻ ሳይኖራቸው ቆይተዋል፡፡ ለዚህም አትሌቶቹን ጨምሮ በርካቶች ዕድሉን ማግኘት ባለመቻላቸው እንደሆነ በምክንያትነት ሲጠቀሱ ይደመጣል፡፡

ከ1950ዎቹ ጀምሮ በትውልድ ቅብብሎሹ አሁን ላይ የደረሰው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ፣ አሳሳቢ ደረጃ ውስጥ መሆኑ መነገር ከጀመረ ስምንት ዓመታት አስቆጥሯል፡፡ ይህ ከቤጂንግ ኦሊምፒክ ጀምሮ በተለይም አገርን በሚወክሉ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ መድረኮች የሚመዘገቡ ሜዳሊያዎች በጣት በሚቆጠሩ አትሌቶች ብቻ መሆኑን በመጥቀስ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በተለይ ከአደረጃጀትና አሠራር እንዲሁም ከአትሌቶች ምልመላና ሙያተኞች ምደባ አንፃር ራሱን በመፈተሽ ማስተካከል እንደሚጠበቅበት ሲነገር ቆይቷል፡፡ አስተያየትና ትችቱ አሁንም እንደቀጠለ ይገኛል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ይኼው ሲሞቅና ሲቀዘቅዝ የቆየው የአትሌቲክሱ ጉዳይ በተለይ ከሪዮ ኦሊምፒክ በኋላ በብሔራዊ ፌደሬሽኑና ይመለከተናል በሚሉ የቀድሞና የአሁን አትሌቶች መካከል ተፈጥሮ የቆየው እሰጥ አገባ እልባት ለማግኘት የተቃረበ ይመስላል፡፡ ከቀናት በኋላ በአዲስ አበባ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ የሥራ አስፈጻሚ ምርጫ የአትሌቶችን ተሳትፎ ያካተተ እንዲሆን መደረጉ የዚሁ እንደ ማሳያ ተደርጎ ይነገራል፡፡

የብሔራዊ ፌዴሬሽኑን የምርጫ ሒደት አስመልክቶ በአንድም ሆነ በሌላ ትልቅ ኃላፊነት እንዳለበት የሚታወቀው የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴርም ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ በጠቅላላ ጉባኤው ድምፅ ካላቸው ክልሎችና ሌሎችም ጋር በመነጋገር ላይ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ ይህንኑ አስመልክቶ ሪፖርተር ያነጋገራቸው አንዳንድ የዘርፉ ባለሙያተኞች በአትሌቲክሱ ትልቁን ድርሻ የሚወስዱ አትሌቶች እንደመሆናቸው በአመራርነት እንዲሳተፉ መደረጉና በሚመለከተው አካላትም እየተሄደበት ያለው እንቅስቃሴ ይበል የሚያሰኝ እንደሆነ ነው ያስረዱት፡፡

የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባኤ ጥቅምት 25፣ 26 እና 27 ቀን 2009 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ጉባኤው ከመደበኛው ዓመታዊ አጀንዳ በተጨማሪ ለቀጣዩ አራት ዓመት የፌዴሬሽኑን ፕሬዚዳንትና የሥራ አስፈጻሚ ምርጫ ያደርጋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የኦሮሚያና የትግራይ ክልላዊ መንግሥታትም ለብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ምርጫ በዕጩነት ያቀረቧቸው ተወዳዳሪዎች ማንነት ታውቋል፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደርን ጨምሮ የተቀሩት ክልሎች ዕጩዎች ማንነት ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ድረስ አልታወቀም፡፡

ቅርበት ያላቸው የፌዴሬሽን ምንጮች እንደሚገልጹት ከሆነ፣ እስካሁን ባለው ሒደት አዲስ አበባ ለፕሬዚዳንትነት ኃይሌ ገብረ ሥላሴን ማቅረቡ ሲታወቅ፣ ከሁለት ዓመት በፊት በማሟያ ምርጫ የአገልግሎት ዘመኑን ካጠናቀቀው አመራር ጋር የቆዩት ዶ/ር በዛብህ ወልዴ ደግሞ ለሥራ አስፈጻሚነት ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የበርካታ ታላላቅ አትሌቶች መገኛ የሆነው የኦሮሚያ ክልል በበኩሉ፣ ለፕሬዚዳንትነት የክልሉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ዳኛቸው ሺፈራውን ሲያጭ፣ ለሥራ አስፈጻሚነት ደግሞ በሲዲኒ ኦሊምፒክ የማራቶን አሸናፊው ገዛኸኝ አበራ በዕጩነት መቅረቡ ተሰምቷል፡፡ የትግራይ ክልል ደግሞ ለፕሬዚዳንትነት በአሁኑ ወቅት የብሔራዊ ወጣቶችና ስፖርት አካዴሚ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ በመሆን በማገልገል ላይ የሚገኙት አቶ ወልደገብርኤል መዝገቡን ሲሆን፣ ለሥራ አስፈጻሚ ምርጫ ደግሞ በተለያዩ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ በውጤታማነቱ የሚታወቀው ገብረ እግዚአብሔር ገብረ ማርያም መሆኑ ታውቋል፡፡

እንደ ዜናው ምንጭ ከሆነ፣ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ድረስ ዕጩዎቻቸውን ያላቀረቡት ክልሎች ለፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንታዊና የሥራ አስፈጻሚ ምርጫ በዕጩ ተወዳዳሪነት የሚያቀርቧቸው አካላት የሦስቱን ክልሎች ተሞክሮ መነሻ ያደረገ እንዲሆን ይፈልጋሉ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ከአገሪቱ አትሌቲክስ አደረጃጀትና አሠራር ጋር ተያይዞ ሲደመጥ ለቆየው ትችትና ወቀሳ የመፍትሔ አማራጭ እንደሚሆን ነው ያስረዱት፡፡

በሌላ በኩል አምና በአርባ ምንጭ ከተማ በተደረገው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ፣ የአትሌቲክሱን ወቅታዊ ሁኔታ የሚያጠና ግብረ ኃይል መቋቋሙ ይታወሳል፡፡ ቡድኑ ባለፈው አንድ ዓመት በተለይም በውጤት ደረጃ በውድቀት ላይ መሆኑ ስለሚነገርለት አትሌቲክሱ ላይ የደረሰበትን የጥናት ውጤት ቅዳሜ ጥቅምት 19 ቀን 2009 ዓ.ም. በብሔራዊ ሆቴል ለባለድርሻ አካላት አቅርቦ እንደሚያወያይ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡

 

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰው መሆን ምንድን ነው? ቅርስና ማኅበራዊ ፍትሕ

በሱራፌል ወንድሙ (ዶ/ር) ዳራ ከጎራዎች፣ ከመፈራረጅ፣ ነገሮችን ከማቅለልና ከጊዜያዊ ማለባበስ ወጥተን...

ኢኮኖሚው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሳት ያሠጋል

በጌታቸው አስፋው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሱ የሚያሠጉኝ አንድ ሁለት ብዬ ልቆጥራቸው የምችላቸው...

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል በሕግ አምላክ ይላል

በገነት ዓለሙ የአገራችንን ሰላም፣ የመላውን ዓለም ሰላም ጭምር የሚፈታተነውና አደጋ...

በሽግግር ፍትሕ እንዲታዩ የታሰቡ የወንጀል ጉዳዮች በልዩ ፍርድ ቤት ሳይሆን በልዩ ችሎት እንዲታዩ ተወሰነ

የኤርትራ ወታደሮች በሌሉበትም ቢሆን ይዳኛሉ ተብሏል በፅዮን ታደሰ የሽግግር ፍትሕ የባለሙያዎች...