Sunday, June 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናፓርላማው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በማፅደቅ መርማሪ ቦርድ ሰየመ

ፓርላማው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በማፅደቅ መርማሪ ቦርድ ሰየመ

ቀን:

መስከረም 30 ቀን 2009 ዓ.ም. የሥራ ዘመኑን የጀመረው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ከመስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም. ተግባራዊ የሆነውንና ለሕዝብ መስከረም 29 ቀን 2009 ዓ.ም ይፋ የተደረገውን የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሙሉ ድምፅ አፀደቀ፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አፈጻጸም የመርማሪ ቦርድ አባላትም ተሰየሙ፡፡

ፓርላማው አዋጁን ካፀደቀ በኃላ በሕገ መንግሥቱ ድንጋጌ መሠረት የአስቸኳይ አዋጁን አፈጻጸም የሚከታተል የአስቸኳይ ጊዜ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አባላትን፣ ሐሙስ ጥቅምት 10 ቀን 2009 ዓ.ም. ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ሰይሟል፡፡

ምክር ቤቱ በዕለቱ ባደረገው ስብሰባ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከመፅደቁ ቀደም ብሎ  የመንግሥት ረዳት ተጠሪው አቶ አማኑኤል አብረሃ የሰነዱን ማብራርያ በንባብ  አቅርበዋል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 93(5) መሠረት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እንደሚደራጅ ካስረዱ በኋላ፣ የመርማሪ ቦርዱን ተግባርና ኃላፊነት በመዘርዘር አብራርተዋል፡፡

መርማሪ ቦርዱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚያስፈጽመው ኮማንድ ፖስት የሚወስዳቸውን ዕርምጃዎች ሕጋዊነት፣ ኢሰብዓዊ መሆንና አለመሆን በመከታተል ለምክር ቤቱ  ሪፖርት እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡

የምክር ቤቱ አባላት በቀረበላቸው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ መጠነኛ ውይይት አድርገዋል፡፡ በአባላቱ ለተነሱ ጥያቄዎች ደግሞ የፌዴራል ዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አቶ ጌታቸው አምባዬ ማብራሪያዎችን ሰጥተዋል፡፡ የኮማንድ ፖስቱ አወቃቀር በክልልም በተመሳሳይ የሚወርድ መሆኑን፣ የአስፈጻሚ አካላት ከመደበኛ ሥራቸው ጋር እንደሚወጡት አስረድተዋል፡፡ አዋጁ ከፀደቀ በኋላ የፓርላማው አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ መርማሪ ቦርዱን ለመሰየም ያቀረቡትን የውሳኔ ሐሳብ በማንበብ የቦርዱን አባላት ዝርዝር አቅርበዋል፡፡

ፓርላማው በአፈ ጉባዔው የቀረቡለትን አባላት በሙሉ ድምፅ ያፀደቀ ሲሆን፣ ከ38 ዓመታት በላይ በተለያዩ ቦታዎችና የሥራ መስኮች በባለሙያነትና በአመራርነት በመሥራት የዳበረ ልምድ አካብተዋል የተባሉትን፣ በምክር ቤቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ታደሰ ሆርዶፋን የመርማሪ ቦርዱ ዋና ሰብሳቢ በማድረግ ሾሟል፡፡ አቶ ታደሰ በሥራ አመራር የመምሪያ ዲግሪ እንዳላቸው ተገልጿል፡፡

እንዲሁም የምክር ቤቱ የበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ገነት ታደሰን የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ እንዲሆኑ በዕጩነት ቀርበው ምክር ቤቱ አፅድቋል፡፡ የ47 ዓመቷ ወይዘሮ ገነት ላለፉት 25 ዓመታት በተለያዩ ቦታዎችና የሥራ መስኮች ውጤት ማስመዝገባቸውን አፈ ጉባዔው በውሳኔ ሐሳቡ ያቀረቡ ሲሆን፣ በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪና በሥራ አመራር ሁለተኛ ዲግሪ እንዳላቸው ጨምረው ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም በዚሁ ምክር ቤት የሥራና ከተማ ልማት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዋ ወይዘሮ ሙና አህመድና በምክር ቤቱ የአማካሪ ኮሚቴ አባል ወ/ሮ ኑሪያ አብዱራህማን ከምክር ቤቱ የተወከሉ የመርማሪ ቦርዱ አባል በመሆን ተሹመዋል፡፡

ሰባት አባላት ላሉት የመርማሪ ቦርድ በዕጩነት ቀርበው ሹመታቸው የፀደቀላቸው ሦስት ቀሪ አባላት ከፍትሕ አካሉ መወከላቸውን አፈ ጉባዔው ባቀረቡት የውሳኔ ሐሳብ ገልጸዋል፡፡ ከተሿሚዎቹ ውስጥ አቶ ክፍለጺዮን ማሞ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛና የሕገ መንግሥት አጣሪ ጉባዔ አባል ሲሆኑ፣ አቶ ሀብቴ ፍላቻ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምክትል ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ እንዲሁም አቶ ሰዒድ ሐሰን የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አስጨናቂው የኑሮ ውድነት ወዴት እያመራ ነው?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኑሮ ውድነት እንደ አገር ከባድ ፈተና...

‹‹ወላድ ላማቸውን አርደው ከደኸዩት ወንድማማቾች›› ሁሉም ይማር

በንጉሥ ወዳጅነው   የዕለቱን ጽሑፍ በአንድ አንጋፋ አባት ወግ ልጀምር፡፡ ‹‹የአንድ...

የመጋቢቱ ለውጥና ፈተናዎቹ

በታደሰ ሻንቆ ሀ) ችኩሎችና ገታሮች፣ መፈናቀልና ሞትን ያነገሡበት ጊዜ እላይ ...

ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ሳይዘረጉ አገልግሎት ለመስጠት መነሳት ስህተት ነው!

በተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ውስጥ ተገልጋዮች በከፈሉት ልክ የሚፈልጉትን...