Friday, September 22, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ለሜትር ታክሲዎች ታሪፍ ወጣ

ተዛማጅ ፅሁፎች

ከቀረጥ ነፃ የገቡ ሜትር ታክሲዎች ታሪፍ ወጣላቸው፡፡ የፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ባለፈው ዓርብ ጥቅምት 11 ቀን 2009 ዓ.ም. ከባለንብረቶቹ ጋር ከመከረ በኋላ፣ አራት ሰው የመጫን አቅም ያላቸው ሊፋን ሳሎን ታክሲዎች በአንድ ኪሎ ሜትር አሥር ብር፣ እስከ ሰባት ሰው የመጫን አቅም ያላቸው አቫንዛ ታክሲዎች በአንድ ኪሎ ሜትር 13 ብር እንዲሆን ተወስኗል፡፡ መንግሥት በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ 1,163 ሜትር ታክሲዎች ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ በ26 አክሲዮን ማኅበራትና በሦስት የግል ኩባንያዎች የሚተዳደሩት ሜትር ታክሲዎች በጳጉሜን 2008 ዓ.ም. ወደ አገር ውስጥ ቢገቡም፣ እስካሁን ታሪፍ ስላልወጣላቸው በድርድር ዋጋ ሲሠሩ ቆይተዋል፡፡ አንድ ሊፋን ሳሎን ታክሲ ጠቅላላ ዋጋው 513,000 ብር ቢሆንም፣ መንግሥት ቀረጥ በማንሳቱ የአንዱ ዋጋ 228,000 ብር ነው፡፡ የንብረቶቹ ባለቤቶች 30 በመቶውን በመሸፈን ከብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክ ጋር ባደረጉት ውል ደግሞ 70 በመቶ ብድር ተመቻችቶላቸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች