Thursday, December 1, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊየአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣንን በአዲስ መዋቅር ለማደራጀት የቀረበው ጥያቄ ይሁንታ አገኘ

  የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣንን በአዲስ መዋቅር ለማደራጀት የቀረበው ጥያቄ ይሁንታ አገኘ

  ቀን:

  የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣንን እንደ አዲስ ለማዋቀር የቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት በማግኘቱ፣ በተዘጋጀው አዲሱ መዋቅር መሠረት ማደራጀት ሊጀመር ነው፡፡

  ከባለሥልጣኑ የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው፣ የባለሥልጣኑን አሠራሮች የተሻለ እንደሚያደርግና የመንገድ አስተዳደሩን በቅርበት ለመከታተል ጥሩ ዕድል ይሰጣል የተባለውን አዲሱ መዋቅር ተግባራዊ እንዲሆን ውሳኔ የተሰጠው፣ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ነው፡፡ በባለሥልጣኑ ማኔጅመንት ተጠንቶ የቀረበውን አዲሱ መዋቅር ሥራ ላይ እንዲውል ውሳኔ የሰጠው ባለሥልጣኑን በበላይነት የሚመራው ቦርድ ነው፡፡

  በአዲሱ መዋቅር እንደ ዋነኛ ለውጥ ተደርጎ የሚወሰደው ባለሥልጣኑ ራሳቸውን ችለው በሚንቀሳቀሱ አምስት ቅርንጫፎች የሚደራጅ መሆኑ ነው፡፡ እያንዳንዱ ቅርንጫፍ የራሱን በጀት በከተማው ውስጥ በሚሸፍናቸው ሥፍራዎች ያሉትን መንገዶች መንከባከብ፣ ጉዳት ሲደርስባቸው መጠገንና የመሳሰሉትን ሥራዎች ያከናውናል፡፡ አምስቱ ቅርንጫፎች የአዲስ አበባ ከተማን አምስት ቦታ በመከፋፈል የሚደራጁ መሆናቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

  ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ወደ እንቅስቃሴ እንዲሸጋገር ይሁንታ ያገኘውን አዲሱን መዋቅር ወደ ተግባር ለመለወጥ ያስችላሉ የተባሉት የቅርንጫፍ ማደራጀት ሥራዎችም፣ በቅርቡ ተጀምረው የበጀት ዓመቱ አጋማሽ ድረስ ለማጠናቀቅ ታስቧል፡፡

  ባለሥልጣኑ በአሁኑ ወቅት ከ900 በላይ ሠራተኞች አሉት፡፡ አዲሱን መዋቅር ተግባራዊ ለማድረግና አደረጃጀቱን ለማጠናከር አዳዲስ የባለሙያዎች ቅጥር ያከናውናል ተብሎም ይጠበቃል፡፡

  አዲስ አበባን አምስት ቦታ በመከፋፈል የሚመሠረቱት ቅርንጫፎች ምሥራቅ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ በሚል ስያሜ ወደ ሥራ ይገባሉ፡፡ እነዚህን ቅርንጫፎች ባለሥልጣኑ በማዕከል ያስተዳድራል፡፡

  በአዲስ አባ ከተማ ከ6,000 በላይ ኪሎ ሜትር መንገዶች ሲኖሩ፣ ከዚህ ውስጥ ከ40 በመቶ የሚሆነው መንገድ በአስፋልት ኮንክሪት የተገነባ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ከ250 በላይ የሚሆኑ በሒደት ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች እንዳሉ ተገልጿል፡፡ ባለሥልጣኑ በ2009 በጀት ዓመት ለማከናወን ላቀዳቸው ሥራዎቹ የከተማው አስተዳደር 6.6 ቢሊዮን ብር በጀት የፈቀደለት ሲሆን፣ በበጀት ዓመቱ ለሚከናወኑ የመንገድ ጥገና ሥራዎች ተጨማሪ በጀት ማግኘቱም ታውቋል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...