Sunday, June 23, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ኤሌክትሪክ ኃይል ባለ 38 ፎቅ ዋና መሥሪያ ቤት ለመገንባት ከቻይናው ኩባንያ ጋር ተፈራረመ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

– የግንባታውን ወጪ 2.5 ቢሊዮን ብር ራሱ ይሸፍናል ተብሏል

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል 2.5 ቢሊዮን ብር በሚጠጋ ወጪ 38 ፎቆች ያሉት ዘመናዊ የዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ለማስገንባት፣ ከቻይናው ግዙፍ የግንባታ ኩባንያና ከአገር በቀል አማካሪ ድርጅቶች ጋር ስምምነት ተፈራረመ፡፡

ግዙፉን ሕንፃ በሦስት ዓመታት ውስጥ ገንብቶ ለማስረከብ የጨረታ አሸናፊ የሆነው፣ በቅርቡ የድሬዳዋ-ደወሌን የኤሌክትሪክ ባቡር መስመር ገንብቶ ያስረከበውና በግዙፍ ፕሮጀክቶች እየተሳተፈ ያለው ሲሲጂኦሲሲ ነው፡፡ የማማከር ሥራውን ደግሞ በማሸነፍ የስምምነት ፊርማቸውን ያኖሩት ኤምኤች ኢንጂነሪንግ ኮንሰልትና ጌረታ ኮንሰልት ናቸው፡፡

የግንባታ ውል ተዋዋይ ድርጅቶችን በመወከል ፊርማቸውን ያኖሩት ኤሌክትሪክ ኃይልን በመወከል ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ኢንጂነር አዜብ አስናቀ ሲሆኑ፣ በሲሲጂኦሲሲ በኩል ደግሞ የኩባንያው ዋና ሥራ አስኪያጅ ዋንግ ዌን ካይ ናቸው፡፡ እንዲሁም የኤምኤች ኢንጂነሪንግ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር መሰለ ኃይሌና የጌረታ ኮንሰልት ተወካይ በአማካሪ ድርጅቶች በኩል ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ኢንጂነር አዜብ ከፊርማው ሥነ ሥርዓት በኋላ ባደረጉት ገለጻ፣ ግንባታው በ48 ሺሕ ካሬ ሜትር ላይ ሜክሲኮ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው የድርጅቱ ቦታ ላይ ይከናወናል፡፡ ግንባታውን ሙሉ በሙሉ ገንብቶ ለመጨረስ 36 ወራት የሚፈጅ መሆኑን፣ የኤሌክትሪክ ኃይል የግንባታውን ወጪ 2.5 ቢሊዮን ብር በራሱ እንደሚሸፍንም አስረድተዋል፡፡

ሕንፃው ከወለል በታች አራት ፎቆች፣ ከወለል በላይ ደግሞ 34 ፎቆች ይኖሩታል፡፡ አንድ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል፣ ሁለት የንግድ ማዕከላትና ከ600 በላይ ተሽከርካዎች የሚስተናገዱበት ማቆሚያ ሥፍራ እንደሚኖረውም አብራርተዋል፡፡

የኮንትራክተሩ ተወካይ በበኩላቸው ሕንፃውን ከታሰበው ጊዜ በፊት በጥራት ገንብተው ለማስረከብ እንደሚጥሩ ገልጸዋል፡፡ ለሕንፃው 60 በመቶ የሚሆነውን የኃይል ፍላጎት ከፀሐይ ኃይል ማግኘት እንደሚያስችል ተደርጎ ለመሥራት መታቀዱም ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች