‹‹የዴሞክራሲ ሒደቱ የበለጠ እንዲጠናከር ከመሥራት ይልቅ ገዢው ፓርቲ መንግሥታዊ ሥልጣኑን አስጠብቆ ለመቀጠል፣ ተቃዋሚው ጎራ ደግሞ መንግሥታዊ ሥልጣን በማግኘት ላይ ብቻ በማተኮራቸው፤ የተገኘውን ውጤት ሁሉ በዜሮ የሚያባዛ ክስተት ተፈጠረ፡፡›› የቀድሞው የኢዴፓ ሊቀመንበር (አሁን የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል) አቶ ልደቱ አያሌው፣ በወቅታዊ የአገሪቱ ጉዳይ ዙርያ በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጥቅምት 6 ቀን 2009 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ በተዘጋጀው መድረክ ‹‹አገራችን የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚና በእስካሁኑና በወደፊቱ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሒደት›› በሚል ርዕስ ካደረጉት ዲስኩር የተወሰደ፡፡