Friday, September 29, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -

ሽኮኮ

ቀን:

ሽኮኮ ፅድ በሞላባችው ደኖች ውስጥ በብዛት ይገኛል። እንስሳው ረጅምና ፀጉራም በሆነው ጭራው በቀላሉ ይታወቃል። ፀጉሩ በክረምት ወቅት ቀይና ቡናማ ዓይነት ሲሆን፣ በበጋ ወቅት አመድማ ነጭ ይሆናል። ፍራፍሬና ተክሎች የሚመገብ ቢሆንም፣ ጫጩቶችንና የአዕዋፍ እንቁላል ሊበላ ይችላል። ክብደቱ እስከ ሁለት ኪሎ ግራም አካባቢ ይመዝናል።

የሽኮኮ ጆሮዎች ክብና ትንንሽ ሲሆኑ፣ እግሮቹ ደግሞ አጫጭር ናቸው። ይህ ትንሽ እንስሳ የሚኖረው አለታማ በሆኑ አካባቢዎች ነው። ከፍተኛ የማየት ችሎታ ያለው መሆኑ ጠላቶቹን ከርቀት ለመለየት ያስችለዋል። አለታማ በሆነው መኖሪያው ያሉት ጉድጓዶችና ስንጥቆች ደግሞ ከጠላቶቹ መሸሸጊያ ናቸው። ሽኮኮዎች በርከት ብለው አንድ ላይ መኖራቸው በጠላቶቻቸው እንዳይደፈሩ የሚረዳቸው ከመሆኑም በላይ በክረምት ወራት እርስ በርስ ለመሟሟቅ ይረዳቸዋል፡፡

የመኖር ዕድሜያቸውን ከስድስት እስከ አሥር ዓመት እንደሆነ፣ ‹‹ስሚዝሶኒያን ናሽናል ሙዝየም ኦፍ ሂስትሪ›› አስፍሯል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...