Friday, February 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅእህል ይዞ የተገለበጠው ተሽከርካሪ

እህል ይዞ የተገለበጠው ተሽከርካሪ

ቀን:

የእርዳታ እህል ጭኖ መስከረም 24 ቀን 2009 ዓ.ም. በሐረር መንገድ ሲያመራ የነበረው ከባድ ተሽከርካሪ ከነተሳቢው ሒርና ከተማ መግቢያ ላይ የመገልበጥ አደጋ ደርሶበት ነበር፡፡

ፎቶ በታምራት ጌታቸው

  **********************

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ማነስ

የቀኗ ጀንበር አዘቅዝቃ

አፍታ እንኳን ሳይሆን ከሰማዩ ሥር ጠልቃ፤

ካድማስ ወዲያ ማዶ ባፍላው ምሽት ደምቃ

ከወትሮ መጠኗ ልቃ

ዝርግ ሰፌድ አህላ ያቺ ለጋዋ ጨረቃ፤

የርምጃዋን ምት ጠብቃ በዝግታ ዜማ ተጉዛ

ከሰማዩ እምብርት ደርሳ የኳስን ቅርፅ ይዛ፤

በትናንሽ ክዋክብት አጀብ ከነበራት መጠን ቀንሳ

ሊያነጋጋ አቅራቢያ ብትታየኝ በእጅጉ አንሳ

አስታወስሁ እራሴን፤

ልክ እንደ ጨረቃ

እያደር-ማነሴን፡፡

  • ፋሲል ተካልኝ አደሬ “ጡዘት” (2008 ዓ.ም.)

*****************

            የየቀኑን እራታቸውን የሚያበስሉት ቢልየነሩ ቢል ጌትስ

በዓለም ሃብታም ከሆኑ ሰዎች በቀዳሚነት የሚታወቁት  የማይክሮሶፍት መስራቹ ቢል ጌትስ፣ ምግባቸውን አብስለው ይመገባሉ ቢባል ቀልድ ይመስላል፡፡ ሆኖም ሲኤንቢሲ የማብሰልን ጥቅም አስመልክቶ ይዞት በወጣው ዘገባ፣ ቢል ጌትስ ምግባቸውን ማብሰል ከመውደዳቸውም በተጨማሪ፣ ሁልጊዜ በሚባል መልኩ ማታ ላይ ቤተሰቦቻቸው ለመመገብ የተጠቀሙባቸውን ሰሃንና መጠጫዎች ያጥባሉ፡፡ አንድ ወቅት ላይ “ሰዎች ከእርሶ የማይጠብቁት ግን የሚያስደስትዎት ሥራ ምንድነው?” ተብለው የጠየቁት ቢልጌትስ፣”በየቀኑ ምሽት ምግብ አበስላለሁ፡፡ ሌሎች ሰዎች ይህንን በበጎ ፈቃድ ሲሠሩት ይችላሉ፣ እኔ ግን ስለምወደው ነው” ብለው ነበር፡፡

በቅርቡ የወጡ ጥናቶች፣ ምግብን ማብሰልም ሆነ የተመገቡበትን ዕቃ ማጠብ ጭንቀት እንደሚቀንስና ፈጠራን እንደሚያጎለብት አስፍረዋል፡፡

ፍሎሪዳ ስቴት ዩኒቨርስቲ፣ የመመገቢያ ዕቃዎችን እንዲያጥቡ ያደረጋቸው ተማሪዎች የነበረባቸው ጭንቀት መቀነሱንና ለመስራት ያላቸው ፍላጎት መነሳሳቱን አስታውቋል፡፡ ዕቃ በሚታጠብበት ውኃ ውስጥ ትኩረት ማድረግና የማጠቢያ ሳሙናዎችን ማሽተት አዕምሮ እንደሚያነቃቃም ገልጸዋል፡፡

ዮኒቨርስቲ ኦፍ ካሊፎርኒያ በበኩሉ፣ ብዙ የማያጨናንቁ ሥራዎችን መስራት አእምሮ  አዳዲስ ነገሮችን እንዲፈጥርና ችግር ፈቺ ሐሳቦችን እንዲያፈልቅ ያስችላል ብሏል፡፡

*********

አስፋልት ያቋረጠች ዶሮ

ለወትሮው የስኮትላንዷ ዳንዲ ከተማ የትራፊክ ፍሰት በተሽከርካሪዎችና እግረኞች ይሞላ ነበር፡፡ ከሰሞኑ ግን ባልተጠበቀ ሁኔታ አንዲት ዶሮ የዳንዲ ከተማን ጎዳና መሻገሯ ተሰምቷል፡፡ እንደ ሚረር ዘገባ፣ ዶሮዋ በጎዳናው ላይ እየተጎማለለች ስትሻገር የተመለከቱ አሽከርካሪዎች ወዲያው ለፖሊስ አሳውቀዋል፡፡ በጎዳናው ስትመላለስ ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት በመፈጠሩ፣ ለደኅንነቷ የሠጉ ፖሊሶች በአፋጣኝ ቦታው ላይ ደርሰው ዶሮዋን ወደ ፖሊስ ጣቢያ ወስደዋታል፡፡

በመቀጠልም ፖሊሶቹ በፌስቡክ ላይ ማስታወቂያ በማውጣት የዶሮዋን ባለቤት ማፈላለግ ጀመሩ፡፡ ማስታወቂያው በደቂቃዎች ውስጥ ከ1,000 በላይ ተመልካች ከማግኘቱ ባሻገር፣ የከተማዋ ነዋሪዎችም ስለ ጉዳዩ አስተያየታቸውን በፌስቡክ ሰጥተዋል፡፡ ፖሊሶች የዶሮዋ ባለቤት እስከሚገኝ ድረስ ዶሮዋን መንከባከብ ግዴታቸው ሆኗል፡፡

                  **********************

ለ200 ቦታዎች 250 ሺህ ያመለከቱበት አካዳሚ

በህንድ ፕራዲሽ ስቴት የሚገኘው ቪድያጊያን ሊደርሽፕ አካዳሚ በየዓመቱ በጣም ደሃ ግን በትምህርታቸው ጎበዝ ለሆኑና በገጠራማ የአገሪቱ ክልሎች ለሚኖሩ ተማሪዎች ነፃ የትምህርት ዕድል ይሰጣል፡፡

አዳሪ ትምህርት ቤቱ የሚገቡት በሙሉ የሃብታም ልጆች ቢሆኑም፣ አካዳሚው በየዓመቱ ለ200 ድሃ ተማሪዎች ምግብ፣ አልባሳት፣ የትምህርት ቁሳቁስና ሌሎች ሙሉ ወጪዎችን በማሟላት በማስተማር ይታወቃል፡፡

ቢቢሲ እንዳሰፈረው፣ አካዳሚው ለ200 ተማሪዎች ነፃ ዕድል ለመስጠት ላወጣው ማስታወቂያ፣ 250 ሺህ አመልካቾች ቀርበዋል፡፡ ከእነዚህ አመልካቾች 125 ሺህ ለፅሁፍ ፈተና የቀረቡ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ ከቤተሰቦቻቸው ድህነት የተነሳ ለትራንስፖርት መክፈል ባለመቻላቸው ሳይፈተኑ ቀርተዋል፡፡ ከተፈተኑት ውስጥ 6ሺህ ያህሉ የመጀመሪያውን ፈተና ያለፉ ሲሆን፣ ቀጣይ ፈተናና ቤተሰቦቻቸው የሚገኙበት የድህነት መጠን ታይቶ 200 ተማሪዎች የትምህርቱን ዕድል አግኝተዋል፡፡

የሚወደውን መኪና በሃሪኬን ማቲው  ምክንያት ያልተለየ

በአሜሪካ ፍሎሪዳ ኮስት የተከሰተውን ሃሪኬን ማቲው ማለትም ከፍተኛ አውሎ ንፋስ የቀላቀለ ዝናብ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመሸሽ የአካባቢው ነዋሪዎች ከሥፍራው ለመልቀቅ ተገደው ነበር፡፡ በፖርት ሴንት ሉዊስ የሚኖረው ራንዲ ኝላል ግን፣ ከምንም በላይ የሚወደውን ቢኤም ደብሊው ኤም 3 መኪናውን ግቢ ውስጥ ማቆም አልመረጠም፡፡ ቤቱን ትቶም ወደሌላ ሥፍራም አልተጓዘም፡፡ የመኖሪያ ቤቱ በር መኪናውን እንደሚያስገባለት ካረጋገጠ በኃላ፣ ከአባቱ ጋር በመተጋገዝ መኪናውን ነድፎ ቤት ውስጥ ማስገባት ችሏል፡፡

ኤምኤስኤን እንዳሰፈረው፣ ጃላል መኪናውን ያደረገበት ክፍል መመገቢያው፣ መተኛውም ነበር፡፡

“ጓደኞቼ መኪናዬን ምን ያህል እንደምወድ ያውቃሉ፡፡ በሕይወቴ የምመኘው መኪናዬ ላይ አደጋ እንዳይደርስ ነው” ብሏል፡፡

በቤት ውስጥ ከመኪና ጋር ሆኖ የተነሳውን ፎቶ በኢንስታግራም ከለቀቀ በኃላ፣ በመኪናው ዙሪያ ህትመት ያላቸው ኩባንያዎች ፎቶዎቹን ኦንላይን እያስቀመጡ ነው፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ የካቤኔ አባል የሆኑት አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያዳመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል...

የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት የፈጠሩት አምቧጓሮ

ባለፈው ቅዳሜና እሑድ በአዲስ አበባ የተካሄደው የአፍሪካ ኅብረት 37ኛው...

የብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ትግበራ የፈጠራቸው አሉታዊና አዎንታዊ ጎኖች

የአገሪቱ ንግድ ባንኮች በዓመት የሚሰጡት የብድር መጠን ላይ የኢትዮጵያ...

ቱግ ቱግ!

የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ ለመታደም የመጡ እንግዶችን ሸኝተን ከፒያሳ ወደ...