Thursday, June 8, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የዓለም ባንክ በስድስት ወራት ብቻ የ1.8 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ካሮሊን ተርክ ሐሙስ ታኅሳስ 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ከገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትሩ አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር) ጋር የ470 ሚሊዮን ዶላር ብድር ስምምነቶችን ሲፈርሙ እንደገለጹት፣ ባንኩ በተቻለው ፍጥነት የፋይናንስ ድጋፎችን ለማድረግ ካለው ፍላጎት በመነሳት እ.ኤ.አ. በ2017 ስድስት ወራት ውስጥ ብቻ የ1.8 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ለመስጠት ቃል ገብቷል፡፡

በመሆኑም ባንኩ ቃል የገባባቸውን የፋይናንስ ስምምነቶች በመጠበቅ የተሰጠው ድጋፍ ለታለመለት ሥራ እንዲውል ከሥር ከሥር እንደሚለቅ ሚስስ ተርክ ተናግረዋል፡፡ ከ470 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ 300 ሚሊዮን ዶላር ለትምህርት ሚኒስቴር የ”አጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም- ለትምህርት ፍትኃዊነት” ማስፈጸሚያ የሚውል ሲሆን፣ ቀሪው 170 ሚሊዮን ዶላር ለእስሳትና ዓሳ ሀብት ሚኒስቴር አዲስ ፕሮጀክት እንደሚውል ታውቋል፡፡

የዓለም ባንክ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በጋራ ለሚሠራቸው ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ በቅርቡ የአምስት ዓመት የአጋርነት ማዕቀፍ ሰነድ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ በዚህም መሠረት ለመጪዎቹ ሦስት ዓመታት የሚውል የአምስት ቢሊዮን ዶላር ብድርና ዕርዳታ እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች