Monday, March 24, 2025
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናሰማያዊ ፓርቲ አዲስ ፕሬዚዳንት መረጠ

ሰማያዊ ፓርቲ አዲስ ፕሬዚዳንት መረጠ

ቀን:

spot_img

    ‹‹ጠቅላላ ጉባዔ አልተካሄደም›› ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት

ቅዳሜ መስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም. በመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ቅጥር ግቢ ውስጥ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው የሰማያዊ ፓርቲ አቶ የሺዋስ አሰፋን ፕሬዚዳንት አድርጎ መምረጡን የፓርቲው ኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በዕለቱ የምርጫ ቦርድ ተወካይ መገኘቱን የገለጹት የሰማያዊ ፓርቲ ኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን ሰብሳቢ አቶ አበራ ገብሩ፣ ‹‹የምርጫ ቦርድ ተወካይ እስከ መጨረሻው ተገኝተው ምልዓተ ጉባዔው መሙላቱን አረጋግጠዋል፡፡ እኛም ጉባዔያችንን በተገቢው መንገድ አካሂደናል፤›› በማለት ገልጸዋል፡፡

ጠቅላላ ጉባዔው የፕሬዚዳንትና የተጓደሉ የምክር ቤት አባላትን ምርጫ ከማከናወኑ አስቀድሞ የብሔራዊ ምክር ቤት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እንደተደረገበትም አቶ አበራ ገልጸዋል፡፡

የጠቅላላ ጉባዔው አጠቃላይ ቁጥር 226 ሲሆን፣ 114 እና ከዚያ በላይ አባላት ከተገኙ ምልዓተ ጉባዔ ይሟላል፡፡ በዚህ መሠረት በጠቅላላ ጉባዔው ላይ 120 አባላት መገኘታቸውን፣ ከእነዚህም መካከል 78 የሚሆኑት አባላት ድምፃቸውን ለአቶ የሺዋስ አሰፋ መስጠታቸውን አቶ አበራ ገልጸዋል፡፡

ከአቶ የሺዋስ አሰፋ ጋር ፓርቲውን በፕሬዚዳንትነት ለመምራት የተፎካከሩት ደግሞ አቶ ሰለሞን ተሰማና አቶ ስሜነህ ፀሐይ እንደነበሩም ተገልጿል፡፡

በጠቅላላ ጉባዔው ፕሬዚዳንት ከመመረጡም በላይ የተጓደሉ የምክር ቤት አባላትን ምርጫ መካሄዱን፣ በዚህ መሠረት በዕጩነት 20 ግለሰቦች ለውድድር መቅረባቸውን፣ በዚህም መሠረት ባገኙት ድምፅ መሠረት ከአንደኛ እስከ ሰባተኛ የወጡትን በመምረጥ ሰባት አባላት መመረጣቸው ተገልጿል፡፡

የፓርቲው ፕሬዚዳንት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት እንዲገኙ ጥሪ ማስተላለፋቸውን የገለጹት አቶ አበራ፣ ‹‹እሳቸው ግን ጠቅላላ ጉባዔው ላይ አልተገኙም፡፡ ለመምጣትም ፈቃደኛ አልነበሩም፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ ለሪፖርተር አስተያየታቸውን የሰጡት ኢንጂነር ይልቃይ ጌትነት፣ ‹‹የሰማያዊ ፓርቲ ደንብ በሚያዘው መሠረት ጠቅላላ ጉባዔ አልተካሄደም፤›› ብለዋል፡፡

በአጠቃላይ ውዝግብ ነበረ የሚሉት ኢንጂነር ይልቃል፣ ‹‹ምልዓተ ጉባዔው አልሞላም፡፡ ፕሬዚዳንት አግደናል ብለው ነው የሠሩት፡፡ ከምርጫ ቦርድ ጋር ሲጻጻፍ የነበረው የማይመለከተው ሰው ነው፡፡ እንዲሁም የገንዘብ ምንጩ አልታወቀም፤›› ሲሉ ጠቅላላ ጉባዔው በእነዚህ ምክንያቶች ተካሂዷል ብለው እንደማያምኑ ገልጸዋል፡፡

‹‹አባላት ከክፍለ አገር ባልመጡበት ሁኔታና እኔም ባልነበርኩበት የተከናወነ ነገር ጠቅላላ ጉባዔ ነው ማለት አይቻልም፡፡ ስለዚህ በእኔ እምነት ጠቅላላ ጉባዔ አልተካሄደም፤›› ብለዋል፡፡

አቶ የሺዋስ አሰፋ የፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ የነበሩ ሲሆን፣ ከሁለት ዓመታት በላይ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ ነበሩ፡፡ ከእስር የተፈቱት በቅርቡ ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም ኢኮኖሚ ከቀውስ ሥጋት የሚወጣው መቼ ነው? የኢትዮጵያስ እንዴት?

በጌታነህ አማረ የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ኢትዮጵያ ለምታበስረውና ለምትከውነው ትንሳዔ ይረዳ...

የንብረቶች ዋጋ ማሽቆልቆልና የምግብ ነክ ሸቀጦች ዋጋ ንረት ተቃርኖ የነገሰበት የአገራችን ገበያ

በኢትዮጵያ ገበያ ውስጥ ያልተቋረጠ የዋጋ ዕድገት እያሳዩ ሲጓዙ ከነበሩ...

ቀጣናዊ ቀውስ ሊፈጥር የሚችለው ውጥረት ይርገብ!

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በትግራይ ክልል ውስጥ በስፋት እየተስተዋለ ያለው...
error: