Friday, December 2, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisment -
  - Advertisment -

  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈጻጸም ልዩ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል!

  ሰሞኑን መንግሥት ለስድስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደንግጓል፡፡ በአገሪቱ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 93 መሠረት በሚኒስትሮች ምክር ቤት የተደነገገው ይኼ አዋጅ፣ የማስፈጸሚያ ደንብና መመርያ ይወጡለታል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲወጣ ምክንያት የሚሆኑ የተለያዩ ክስተቶች ይኖራሉ፡፡ አሁን ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱንና አገሪቱን አደጋ ላይ የሚጥልና በተለመደው የሕግ ማስከበር ሥርዓት ለመቋቋም የሚያስችል ችግር በመፈጠሩ አዋጁ መደንገጉን መንግሥት አስታውቋል፡፡ በተለይ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ሥፍራዎች ለሰዎች ሕይወት መጥፋትና ለመጠነ ሰፊ የአገር ሀብት ውድመት መንስዔ የሆነው ሥጋት ነው ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መውጣት ምክንያት የሆነው፡፡ በሕገ መንግሥቱ መሠረትም አዋጁ ተደንግጓል፡፡ የአዋጁ አፈጻጸም ደረጃ በደረጃ የሚታወቅ ቢሆንም፣ በሕገ መንግሥቱ ዋስትና ያገኙ መሠረታዊ የሚባሉ መብቶች ስለሚታገዱ፣ የጥንቃቄ ጉዳይ የብዙዎች ጥያቄ ይሆናል፡፡

  መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የአገሪቱን ሰላምና ደኅንነት በማስጠበቅ ሒደት ውስጥ የዜጎችን ሰብዓዊ መብቶች እንደሚያስከብር ሲገልጽ፣ በሌላ በኩል ለፀጥታ ኃይሎች ከሚሰጠው ተጨማሪ ሥልጣን በመነሳት ልዩ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ ዜጎች ያሳስባሉ፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለአገሪቱ ሥጋት የሆኑ ችግሮችን ለመቀልበስ ሥራ ላይ ሲውል በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጡ መሠረታዊ መብቶች ለጊዜው ቢታገዱም፣ በተቻለ መጠን ከአገርና ከሕዝብ ዘለቄታዊ ጥቅም አንፃር ሊመዘኑ ይገባል፡፡ በአዋጁ አፈጻጸም ወቅት የፀጥታ ኃይሎች ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተጠርጣሪዎችን ሲይዙ፣ የመኖሪያ ቤቶችን ሲፈትሹ፣ ወንጀል ሊፈጽሙ ይችላሉ የሚባሉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር ሲያውሉ፣ መንገዶችን ሲዘጉ፣ ሰዎችን ለተወሰነ ጊዜ ይዘው ሲያቆዩም ሆነ ተመሳሳይ ተግባራትን ሲፈጽሙ የመብት ጥሰት ክፍተቶች እንዳይከሰቱ መደረግ አለበት፡፡ በቂም በቀልና በጥላቻ በሚፈበረኩ ክሶች ንፁኃን እንዳይንገላቱ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያሻል፡፡

  የፀጥታ ኃይሎች ሥራቸውን በሚያከናውኑበት ወቅት ከፍተኛ ሥነ ምግባርና ትህትና ሊኖራቸው ይገባል፡፡ በአገራችን ለሕግ የበላይነት የሚሰጠው ክብር ከፍተኛ በመሆኑ ሁሌም የሚባለው በሕግ አምላክ ነው፡፡ የሕጎች ሁሉ የበላይ የሆነው ሕገ መንግሥት በሚያዘው መሠረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተግባራዊ ሲሆን፣ የአገርና የሕዝብ ሰላም ከማስከበር በላይ የግለሰቦች ፈቃድ መፈጸሚያ እንዳይሆን ብርቱ ቁጥጥር ያስፈልጋል፡፡ አዋጁን በተለያዩ ሥፍራዎች የሚያስፈጽሙ ሰዎች ኃላፊነታቸውን ዘንግተው ኢሰብዓዊ የሆነ አያያዝና የኃይል ዕርምጃ የሚጠቀሙ ከሆነ፣ ዜጎች በሕግ የበላይነት ላይ ያላቸው እምነት ይጠፋል፡፡ የሕግ የበላይነት ተግባራዊ ሲደረግ መተማመኑ ይጨምራል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአስፋልት ላይም ሆነ በፒስታ መንገድ ላይ እንደሚነዳ መኪና ቢታሰብ፣ ማርሽ ይቀየርለታል እንጂ ሞተር እንዲጠፋ አይደረግም፡፡ ሕዝብ ሁሌም የሚተማመነው በሕግ ነው፡፡ ሕገ መንግሥቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በተመለከተ ያሠፈራቸው ነጥቦች  ሊከበሩ ይገባል፡፡

  አዋጁ ተግባራዊ ሲደረግ አጥፊ በሚባሉ ተጠርጣሪዎች ላይ የሚወሰዱ ተመጣጣኝ ዕርምጃዎችና የሕግ ዕርምጃዎች ይኖራሉ፡፡ እነዚህን እንቅስቃሴዎች የሚቆጣጠር ሰባት አባላት ያሉት ቦርድ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከራሱና ከሕግ ባለሙያዎች እንደሚያቋቁም ይታወቃል፡፡ ይህ ቦርድ አዋጁ በሕገ መንግሥቱ መሠረት እንዲፈጸም የሚከታተልና የሚቆጣጠር ነው ተብሏል፡፡ ዜጎች በዚህ መሠረት አዋጁ ተግባራዊ እንዲሆን ጥሪ ሲቀርብላቸው፣ ከምንም ነገር በላይ የሆነው ሕግና ሕጋዊነት እንዳይሸራረፍ ተገቢው ጥንቃቄ ይደረግ፡፡ በአፈጻጸሙ ሒደት የሚያጋጥሙ አስቸጋሪ ሁኔታዎችም ሆኑ መልካም አጋጣሚዎች ለሕዝቡ ተደራሽ መሆን አለባቸው፡፡ በተቻለ መጠን የሕዝብ አመኔታና ተቀባይነት ያገኙ አፈጻጸሞች ከጉዳታቸው ይልቅ ጠቀሜታቸው ስለሚያመዝን፣ መንግሥት እነዚህን ጉዳዮች አፅንኦት ሊሰጥባቸው ይገባል፡፡ በጥንቃቄ የሚከናወኑ አሠራሮች ብዙ ጉዳት ቀንሰው ውጤት ያስገኛሉ፡፡

  በሌላ በኩል ከሕግ ማስከበር ተልዕኮው ጋር ፈጽሞ መዘንጋት የሌለበት በአገሪቱ ውስጥ የተከሰቱ ነውጦችን ከማስቆም በተጨማሪ፣ ለሕዝብ መሠረታዊ ጥያቄዎች የሚሰጠው ምላሽ ጉዳይ ነው፡፡ የሕዝብ ጥያቄዎች በሰላማዊ መንገድ ምላሽ እንዲያገኙና በአገሪቱ ውስጥ ያለው የተቆላለፈ የፖለቲካ ምኅዳር እንዲከፈት ብሔራዊ ድርድርና ውይይት የግድ ነው፡፡ በአገሪቱ ሰላማዊ ውይይትና ክርክር በሠለጠነ መንገድ ሲካሄድ መፍትሔዎችን ለማመንጨትና የተሻለች አገር ለመገንባት ያግዛል፡፡ ከብጥብጥ ይልቅ በሰላማዊ መንገድ የሚቀርቡ ፖለቲካዊ መፍትሔዎች ይጠናከሩ፡፡ በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ፣ የሙያ ማኅበራትና የመሳሰሉት በነፃነት የሚንቀሳቀሱበት ማዕቀፍ ያስፈልጋል፡፡ አንድ መቶ ሚሊዮን ሕዝብ ባለበት አገር ውስጥ የተለያዩ ፍላጎቶችን የሚያማክል ሥርዓት መፍጠር ሲገባ፣ በአንድ አስተሳሰብ ብቻ የሚመራ ሥርዓተ መንግሥት ከሰላም ይልቅ ለጠብ የቀረበ ይሆናል፡፡ በዚህ ምክንያት ሕዝብ ጥያቄ ሲያቀርብ ምላሽ የሚሰጥበት ሥርዓት ደካማ በመሆኑ ላለፈው አንድ ዓመት ያህል ሰላም ደፍርሷል፡፡ በርካቶች ሞተዋል፡፡ በርካቶች ለአካል ጉዳት ተዳርገዋል፡፡ ከፍተኛ የሆነ የአገር ሀብት ወድሟል፡፡ ከእንዲህ ዓይነቱ አሥጊ አረንቋ ውስጥ የሚያወጣ ምኅዳር መፈጠር አለበት፡፡ የግድ ነው፡፡

  የሪፐብሊኩ ፕሬዚዳንት በፓርላማ መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር በአገሪቱ የፍላጎቶችን ብዝኃነት በመገንዘብ የአብላጫ ድምፅ የምርጫ ሥርዓትን የሚቀይር ዕርምጃ እንደሚወሰድ ገልጸዋል፡፡ ከገዥው ፓርቲ በተለየ ጥቅምና ፍላጎት ያላቸውን ማኅበረሰቦች የሚወክሉ ፓርቲዎች በምክር ቤቶች ተሳታፊ እንዲሆኑና የተለያዩ ድምፆችም እንዲሰሙባቸው ለማድረግ የሚረዳ የሕግ ማዕቀፍ እንደሚኖር ተሰምቷል፡፡ ይህ መልካም ዕርምጃ ነው፡፡ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብትን ጨምሮ ሌሎች መሠረታዊ መብቶች የተከበሩባት አገር ታስፈልጋለች፡፡ ዴሞክራሲ ሥርዓት ሆኖ በተግባር የሚሰፍነው የአገር ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ዜጎች በሰላማዊ መንገድ መነጋገርና መደራደር ሲጀምሩ ነው፡፡ አገር የምትበለፅገው፣ ሰላም የሚኖራት፣ ዜጎች በነፃነት አንገታቸውን ቀና አድርገው የሚራመዱት፣ ፍትሐዊ የሀብትና የሥልጣን ክፍፍል የሚኖረው፣ ዴሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶች የሚከበሩት፣ የሕግ የበላይነት የሚሰፍነው፣ ወዘተ ዜጎች ብሔራዊ መግባባት ሲፈጥሩ ብቻ ነው፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተግባራዊ እየተደረገም ቢሆን ይኼ ጉዳይ ለአፍታም ቢሆን መዘንጋት የለበትም፡፡ እስከዚያው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈጻጸም ልዩ ጥንቃቄ ይደረግበት!

   

  በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

  አሜሪካ ሕወሓትን በማሳመንና በመጫን በሰላም ሒደቱ ትልቅ ሚና መጫወቷን የኢትዮጵያ ዋና ተደራዳሪ አስታወቁ

  የተመድና የአውሮፓ ኅብረት አበርክቶ አሉታዊ እንደነበር ጠቁመዋል በመንግሥትና በሕወሓት መካከል...

  አዋሽ ባንክ ለሁሉም ኅብረተሰብ የብድር አገልግሎት የሚያስገኙ ሁለት ክሬዲት ካርዶች ይፋ አደረገ

  አዋሽ ባንክ ለሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች በዘመናዊ መንገድ ብድር ማስገኘት...

  የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅን የሚተካ ረቂቅ ተዘጋጀ

  ከቫት ነፃ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል ገደብ ተቀመጠለት የገንዘብ ሚኒስቴር ከሃያ...

  በፍላጎት ላይ የተመሠረተ ብሔራዊ አገልግሎት የተካተተበት አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ

  የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ወይም የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ወጣቶች በፈቃደኝነት...
  - Advertisment -

  ትኩስ ፅሁፎች

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...

  የጉድለታችን ብዛቱ!

  ከፒያሳ ወደ ሜክሲኮ ልንጓዝ ነው። ጎዳናውን ትውስታ እየናጠው ሁለትና...
  spot_img

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  ለዘመኑ የማይመጥን አስተሳሰብ ዋጋ ያስከፍላል!

  በኳታር እየተከናወነ ያለው የዓለም ዋንጫ በእግር ኳስ ጨዋታ ውስጥ ያልተጠበቁ ማራኪ ቴክኒኮችንና ታክቲኮችን ከአስገራሚ ውጤቶች ጋር እያስኮመኮመ፣ ከዚህ ቀደም በነበረ ችሎታና ዝና ላይ ተመሥርቶ...

  መንግሥት ለአገር የሚጠቅሙ ምክረ ሐሳቦችን ያዳምጥ!

  በሕዝብ ድምፅ የተመረጠ መንግሥት ለሕዝብ የሚጠቅሙ ሐሳቦችን የማዳመጥ ኃላፊነት አለበት፡፡ ሥራውን ሲያከናውንም በግልጽነት፣ በተጠያቂነትና በኃላፊነት መርህ መመራት ይኖርበታል፡፡ እያንዳንዱ ዕርምጃው በሕግ ከተሰጠው ኃላፊነት አኳያ...

  የሰላም ስምምነቱ ተግባራዊ ይደረግ!

  የሰላም ስምምነቱ ‹‹ታጥቦ ጭቃ›› ሊሆን የሚችልባቸው ምልክቶች እየተስተዋሉ ነው፡፡ ሚሊዮኖችን ለዕልቂት፣ ለመፈናቀል፣ ለከፍተኛ ሰብዓዊ መብት ጥሰትና መሰል ሰቆቃዎች የዳረገው አውዳሚ ጦርነት በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት...