‹‹ለኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት፣ የምድሪቱ ብሔር ብሔረሰቦች በድብብቆሽ ዲፕሎማሲ ሳይሆን በልብ ግልጽነት ፊት ለፊት ተገናኝተው በመደማመጥና በመቀራረብ፣ በንሥሐና በይቅርታ በመቀባበል በማያዳግም ሁኔታ ያለፈውን በመቅበር ለወደፊት በምሕረትና በጽድቅ ላይ የተመሠረተ በምድሪቷ ስፋት ከዳር እስከ ዳር የሰላም እጅ መዘርጋት ነው፡፡ ይህንን እጅ እግዚአብሔር የሰጠን ለሰላም እንጂ ለመዋጋት አይደለም፡፡››
ቄስ ዶክተር ቶሎሳ ጉዲና፣ በአትላንታ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ባለፈው ሳምንት በቤተ ክርስቲያን ለተገኙ ምዕመናን ስለወቅቱ የኢትዮጵያ ሁኔታ ከተናገሩት የተወሰደ፡፡ ቄስ ዶ/ር ቶሎሳ አያይዘውም እግዚአብሔር የሰየመን፣ መጽሐፍ ቅዱስ የሚጠራን የዓለም ሕዝብ የሚያውቀን ኢትዮጵያ ብሎ ነው ብለዋል፡፡