Friday, April 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትኃይሌ ገብረሥላሴ ርቀት ለሕይወት ዘመን ስኬት የክብር ሽልማት ተመረጠ

ኃይሌ ገብረሥላሴ ርቀት ለሕይወት ዘመን ስኬት የክብር ሽልማት ተመረጠ

ቀን:

ዓለም አቀፍ ማራቶኖችና ረዥም ርቀት ውድድሮች ማኅበር ለኃይሌ ገብረሥላሴ የሕይወት ዘመን ስኬት የክብር ሽልማት ሊሰጠው እንደሆነ የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር (አይኤኤኤፍ) በድረ ገጹ አስታውቋል፡፡

ኃይሌ የክብር ሽልማቱን የሚያገኘው በ110 አገሮች በተደረጉ 410 ውድድሮች በሕይወት ዘመኑ ባስመዘገው ውጤት መሆኑም ተመልክቷል፡፡ ኃይሌ ከማኅበሩ አባላትና ከሌሎች አጋር አካላት ለክብር ሽልማት በመመረጡ ደስተኛ እንደሆነም ዘገባው አመልክቷል፡፡

ማኅበሩ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በሕይወት ዘመኑ ላስመዘገበው ስኬት ዕውቅና የሰጠበትን አግባብና በውሳኔውም ትልቅ ክብር እንደተሰማው የዓለም አቀፍ የማራቶኖችና የረዥም ርቀት ውድድሮች ማኅበር ፕሬዚዳንት ፓኮ ፖራዎ ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የኃይሌ ስኬት ለአፍሪካ ብቻ ሳይሆን ለዓለም ተምሳሌት በመሆኑ ሌሎችን ለማነሳሳት እንደሚያግዝ ጭምር ያላቸውን እምነትም ገልጸዋል፡፡

የዕውቅና ሽልማቱ ፕሮግራም ኅዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም. በግሪክ አቴንስ እንደሚካሄድም የአይኤኤኤፍ ድረ ገጽ አክሎ ዘግቧል፡፡

ኃይሌ እ.ኤ.አ. በ2006፣ 2007 እና 2008 በተከታታይ ለሦስት ዓመታት በማኅበሩ የዓመቱ ምርጥ አትሌት በመባል የክብር ሽልማት ማግኝቱ ይታወሳል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...