ከአጋዘን ዘር የሚመደበው ሮ አጋዘን፣ የምዕራባውያን አጋዘን በመባልም ይታወቃል፡፡ ወንድ ሮ አጋዘን ቀንዱ ቅርንጫፍ ያለው ሲሆን፣ አንድ ትልቅ ሮ አጋዘን ቁመቱ ከ64 እስከ 89 ሴ.ሜ ሊደርስ ይችላል። ክብደቱ ደግሞ ከ17 እስከ 23 ኪሎ ግራም ይመዝናል። ሮ አጋዘን ሳር በል እንስሳ ሲሆን፣ ከሌሎች ጋር ሲነፃፀር ትንሽ ነው፡፡ መርቃማ ቀይና ወደ ግራጫ ያደላ ቡናማ ቀለምም አለው፡፡
ሮ አጋዘን በአውሮፓ፣ በሜዲትራኒያንና በስካንዲኔቪያን አገሮች፣ በተለይም ቀዝቃዛ የአየር ንብረት ባላቸው በብዛት ይገኛል፡፡ እንደ ውሻ ዓይነት ድምፅ ያለው ሮ አጋዘን፣ የመኖር ዕድሜው እስከ አሥር ዓመት ነው፡፡