Monday, February 6, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የፀጥታ ቁጥጥሩን አጠናክሬያለሁ አለ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የፀጥታ ቁጥጥሩን አጠናክሬያለሁ አለ

ቀን:

– ቁጥራቸው ባልታወቀ ግለሰቦች ላይ ምርመራ እያካሄደ ነው

በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገኙ የኦሮሚያ ከተሞች ተቃውሞ ከተቀሰቀሰ በኋላ  የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በከተማዋ ሊከሰት የሚችል ተቃውሞን ለመቆጣጠር፣ የፀጥታ ሥራውን ከመደበኛው አሠራር በተጠናከረ መንገድ እያከናወነ መሆኑን ገለጸ፡፡  

የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ፋሲካ አስፋው ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ተቃውሞ ወደ አዲስ አበባ እንዳይዛመት ከፌዴራል ፖሊስ ጋር በመጣመር ቁጥጥሩ ጠብቋል፡፡ በሦስት ፈረቃ የነበውን የፀጥታ ሥምሪት ወደ አንድ ፈረቃ እንዲሆን መደረጉን አስረድተዋል፡፡ በከተማዋ ነዋሪዎች ተቃውሞው ከኦሮሚያ ከተሞች ወደ አዲስ አበባ ይዛመታል የሚል ሥጋት በስፋት ቢስተዋልም፣ በፀጥታ ኃይሎች ጥረት ሊገታ እንደተቻለም አክለዋል፡፡

እስካሁንም በከተማዋ በንብረት ላይም ሆነ በሰዎች ደኅንነት ላይ አደጋ ያስከተለ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ አለመከሰቱንም ኮማንደር ፋሲካ አስረድተዋል፡፡

ነገር ግን አንዳንድ ግለሰቦች ለተቃውሞ ለመንቀሳቀስ ሲሞክሩ በተለያዩ ሥፍራዎች ከሕዝብ በመጡ ጥቆማዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ጨምረው ገልጸዋል፡፡

በርከት ያሉ ተጠርጣሪዎች የተያዙት በመርካቶ አውቶቡስ ተራ አካባቢ እንደሆነ የገለጹት ኮማንደር ፋሲካ፣ ለአብነት ያህል አንድ ማንነቱ ያልተገለጸ ግለሰብ አውቶቡስ ተራ መናኸሪያው አካባቢ የኦነግን ሰንደቅ ዓላማ ሲያውለበልብ መያዙን ጠቁመዋል፡፡

እስካሁን በቁጥጥር ሥር የዋሉ ግለሰቦችን ብዛት ለጊዜው መግለጽ እንደሚያስቸግራቸው የገለጹት ኃላፊው፣ ካለፈው ማክሰኞ መስከረም 24 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ ከተያዙት ተጠርጣሪዎች የተወሰኑት ማጣራት ተደርጎ መለቀቃቸውንና በቀሪዎቹ ላይ ምርመራ መቀጠሉን ጨምረው ገልጸዋል፡፡

የፀጥታ ቁጥጥሩ የሚቀጥል በመሆኑ ኅብረተሰቡ ሥጋት ላይ የሚጥሉትን አሉባልታዎችን ወደጎን በማለት፣ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴውን ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡

አዲስ አበባ ከተማን  በዙሪያው ካሉት የኦሮሚያ ከተሞች የሚያገናኙ አካባቢዎች ላይ ፖሊስ የተጠናከረ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቤተክህነት ባቀረበችው የይግባኝ አቤቱታ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለዕሮብ ተቀጠረ

የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሀገወጥ ነው በተባለው አዲሱ ሲኖዶስና...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...