Wednesday, February 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

በኢሬቻ ዕለት ከአባገዳዎች ምርቃት በመቀበል የተጀመረ ትዳር መልካም ይሆናል ተብሎ ይታመናልና ቀድሞ በቦታው ብዙ ጥንዶች ይገኙ ነበር:: ዘንድሮ የተገኙት በጣት የሚቆጠሩ ጥንዶች አልተሞሸሩም

ትኩስ ፅሁፎች

   ምፀት

ሁላችንም ነን ወንድማማቾች፤

እንደቃየል እንደ አቤል

እንደ ሁለቱ የአዳም ልጆች፡፡

* * *

ዓመፅ

የረሃብ እስረኞች እጃችሁ ይፈታ፤

‹‹እሱ ያቃል!›› ብላችሁ ልባችሁ አያመንታ፡፡

ማወቁን እንደሆን እግዜሩም ትቶታል፤

ሙታን ዐመፁና ከእነሱ ይሟገታል፡፡

ወሬ ከሻታችሁ እንኩ አዳምጡኝ፤

ከሙታኑ ዓለም እንደደረሰኝ፤

ዐምፀው የተነሱት የዋሃኑ ናቸው፤

በምድር ባሉ ጊዜ የሰሙት ተስፋቸው፣

ከአርያም ሲወጡ ስላልሞላላቸው፣

በጥሞና እንዳይሆን በድናቸው ሰማና፣

ብድግ ብሎ አመጠ ነፍሱን ነጠቀና፡፡

  • ዮናስ አድማሱ ‹‹ጉራማይሌ›› (2006)

* * *

ዝመጽሐፍ

  • በፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ በተዘጋጀው ‹‹ከጉሬዛም ማርያም እስከ አዲስ አበባ የሕይወት ጉዞ እና ትዝታዬ›› መጽሐፍ ላይ ቅዳሜ መስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም.፣ ጥቁር አንበሳ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው ትራኮን ሕንፃ ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ውይይት ይደረጋል፡፡ እንዲሁም ‹‹መጻሕፍት እንደ መሠረታዊ ፍላጎት›› በሚል መሪ ቃል ቅዳሜና እሑድ የመጻሕፍት ዐውደ ርዕይ ይኖራል፡፡

* * *

  • የነፍስ ኄር ሙሉጌታ ሉሌ መጣጥፎችን ስብስብ የያዘው ‹‹ሰው ስንፈልግ ባጀን›› መጽሐፍ ቅዳሜ መስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም. ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን አዳራሽ ይመረቃል፡፡ በልጁ ኤዶም ሙሉጌታ ሉሌ በተደራጀው መጽሐፍ ላይ ዳሰሳ፣ እንዲሁም የጸሐፊውን የጋዜጠኛነት ሕይወትና ተሞክሮ የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም ሙት ዓመቱን አስመልክቶ እንደሚቀርብ ኢጋ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን አስታውቋል፡፡

* * *

  • በአቢሲኒያ ፊልም ፕሮዳክሽን ተዘጋጅቶ የቀረበውና የቤተሰብ ድራማ ዘውግ ያለው ‹‹ኑርልኝ›› ፊልም መስከረም 26 ቀን 2009 ዓ.ም. በ11 ሰዓት 22 ባታ ኮምፕሌክስ ሦስተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው አቤል ሲኒማ ይመረቃል፡፡

************

ወፍ ለበረራ መስተጓጎል ምክንያት ሆነ

በቬንዙላ ካራካስ ሲሞን ቦሊሻር ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ በመብረር ላይ ያለ አውሮፕላን አፍንጫ ውስጥ ወፍ ገብቶ በመሞቱ ፓይለቱ አውሮፕላኑን ለማሳረፍ መገደዱን የሜትሮ ዘገባ አመለከተ፡፡ ወፉ ከአውሮፕላኑ አፍንጫ ጋር የተላተመው በኃይለኛ ግፊት በመሆኑ በአውሮፕላኑ አፍንጫ ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡ ቢሆንም ፓይለቱ የከፋ ችግር ተፈጥሮ ተሳፋሪዎችም ሳይጎዱ አውሮፕላኑን ማሳረፍ ችሏል፡፡ ለምሳሌ እ.ኤ.አ. 2013 ላይ የእንግሊዝ ሲቪል አቪዬሽን ከ1535 በላይ የሚሆን የወፎች አውሮፕላን ኤንጅን ውስጥ የመግባት ኬዝን መዝግቧል፡፡ በተለይም ወፎቹ በኤንጅኑ ተይዘው ከቀሩ ሁኔታዎች አስቸጋሪ ይሆናሉ፡፡ በወፎች ምክንያት በቅርቡ ከተፈጠሩ የበረራ ችግሮች በቅርቡ ወንዝ ላይ ለማረፍ የተገደደው የአሜሪካው አውሮፕላን ኬዝ ይጠቀሳል፡፡

***********

በ102 ዓመታቸው እሥር ቤት የገቡት ባልቴት

በአሜሪካ በምትገኝ ሚዘሪ በተባለች ግዛት ነዋሪ የሆኑት የ102 ዓመቷ የዕድሜ ባለፀጋ በፖሊስ ካቴና ታስረው እሥር ቤት ገቡ፡፡ ኤዲ ሲምሥ የተባሉት ሴትየዋ እሥር ቤት የገቡት የፈጸሙት ወንጀል አልያም ሌላ ጥፋት ኖሮ አይደለም፡፡ ሕይወታቸው ከማለፉ በፊት ሊፈጽሙት ከሚገባ ነገሮች ዝርዝር መታሠር አንዱ በመሆኑ እንጂ፡፡ ያሆ አውስ ከሀፊንግተን ፖስት በተጋራው መረጃ መሠረት ኤዲ በካቴና ታስረው ወደ ፖሊስ ጣቢያው በሚሄዱበት ወቅት ከፊታቸው ላይ ከፍተኛ የደስታ ስሜት ይነበብ ነበር፡፡ ‹‹ማድረግ የለባችሁን ማንኛውንም ነገር ከማድረግ አትቦዝኑ፡፡ የተወሰነ ሰዓት ደግሞ ከጊዜያችሁ ላይ ቀንሳችሁ ነፃ አገልግሎት ስጡ፤›› ያሉት ሴትየዋ የተለያዩ ሰብዓዊ ድርጊቶችን እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡ ምኞታቸውን እንዲያሳኩ የረዳቸው የሴንት ሉዊስ ፖሊስ ተመሳሳይ ምኞት ያላቸውን ሰዎች መርዳት እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል፡፡

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች