Saturday, June 10, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊወደ ሕዋ ሳተላይት ለማምጠቅ ጥናት መጀመሩ ተገለጸ

ወደ ሕዋ ሳተላይት ለማምጠቅ ጥናት መጀመሩ ተገለጸ

ቀን:

– በሕዋ የሳተላይት ማስቀጫ ቦታ ለማግኘት የቀረበው ጥያቄ ከጄኔቭ መልስ ይጠብቃል ተብሏል

ኢትዮጵያ ወደ ሕዋ የራሷን ሳተላይት ለማምጠቅ ጥናት እያካሄደች እንደምትገኝና ቴክኖሎጂው ካላቸው ኩባንያዎች ጋር በጋራ እየሠራች መሆኗን አስታወቀች፡፡

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና የኮሙዩኒኬሽንና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ አገሪቱ ወደ ሕዋ ሳተላይት ለማምጠቅ ጥናት በማካሄድ ላይ ስትሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሳተላይት ቴክኖሎጂ ባለቤት ከሆኑ ኩባንያዎች ጋር ቴክኖሎጂውን በጋራ በማበልፀግ የራሷን ሳተላይት ገጣጥማ ለማምጠቅ ዕቅድ ነድፋለች ብለዋል፡፡

ምንም እንኳ ይህ ዕቅድ በረጅም ጊዜ ውስጥ የሚከናወን ቢሆንም፣ ከወዲሁ ግን ቴክኖሎጂውን በአገር ውስጥ ዕውቀት ለመምራት የሚያስችል ጥናት እየተካሄደ እንደሚገኝና ከሁለት ዓመት በፊትም ለዓለም የቴሌኮሙዩኒኬሽን ማኅበር በሕዋ ላይ ሳተላይት ለማሳረፍ የሚያስችል ቦታ ለኢትዮጵያ እንዲሰጣት ጥያቄ ቀርቦ ምላሽ እየተጠበቀ እንደሚገኝ ዶ/ር ደብረ ጽዮን አስታውቀዋል፡፡ በርካታ አገሮች በሕዋ የሳተላይት ማሳረፊያ ቦታ እንዲሰጣቸው በመጠየቃቸው ምክንያት፣ ኢትዮጵያ ያቀረበችው ጥያቄ ከአምስት ዓመት በላይ ሊፈጅ እንደሚችል ገልጸዋል፡፡

ሳተላይት ከሚያመርቱ አገሮች ገዝቶ ማምጠቅ ቀላል ተግባር መሆኑን፣ ይህንን ለማድረግም የተመቻቹ ዕድሎች እንዳሉ ያብራሩት ሚኒስትሩ ከዚህ ይልቅ የኢትዮጵያ ትኩረት ሳተላቶችን አገር ውስጥ ከመገጣጠም ባሻገር እስከ መፈብረክ ባለው ደረጃ አብረዋት ሊሠሩ የሚችሉ ኩባንያዎችን በማፈላለግ፣ ቴክኖሎጂውን በጋራ ማበልፀግ ቅድሚያ እንደሚሰጠው ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ጎን የእንጦጦ የሕዋ ሳይንስ ማዕከል በርካታ ከሕዋ ምርምር ጋር የተያያዙ ሥራዎችን እንዲያከወናውን የሚያስችለውን እንቅስቃሴ ማካሄድ እንደጀመረ የጠቀሱት ዶ/ር ደብረ ጽዮን፣ አገሪቱ ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች እየተጠቀመችበት ያለው የሳተላይት ቴክኖሎጂ ከሌሎች አገሮች በኪራይ የተገኘ በመሆኑ ችግር እየፈጠረ እንደሚገኝ ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

በሕዋ ሳተላይት ያመጠቁ አገሮች በየጊዜው የኪራይ ዋጋ ጭማሪ በማድረግና ባሻቸው ጊዜም አገልግሎት እስከማቋረጥ የሚደርሱበት ሁኔታ ስላለ፣ ኢትዮጵያ የራሷን ሳተላይት ወደ ሕዋ ማምጠቋ የወደፊት ግቧ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በሌላ በኩል ከ30 በላይ አገሮች የተሳተፉበትና በአፍሪካ የሳተላይት ቴክኖሎጂና አገልግሎት ላይ ያተኮረ ጉባዔ በአዲስ አበባ መካሄድ የጀመረ ሲሆን፣ በአፍሪካ የራሳቸው ሳተላይት ካላቸው አገሮች መካከል አልጄሪያ፣ ናይጄሪያና ኬንያ እንደሚገኙበት የአፍሪካ ኅብረት አስታውቋል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አያሌ የውኃ “ጠርሙሶች”ን በጫንቃ

መሰንበቻውን በአይቮሪ ኮስት መዲና አቢጃን የምትኖር አንዲት ሴት፣ በሚደንቅ...

ወልቃይትን ማዕከል ያደረገው የምዕራባዊያን ጫና

በትግራይ ክልል የተከሰተው የዕርዳታ እህል ዘረፋ የዓለም አቀፍ ተቋማት...

ከቀጣዩ ዓመት በጀት ውስጥ 281 ቢሊዮን ብሩ የበጀት ጉደለት ነው ተባለ

ለቀጣዩ በጀት ዓመት ከቀረበው 801.65 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ በጀት...