Monday, December 5, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊየአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻዎችን ለግል አልሚዎች ለመስጠት መመርያ ተዘጋጀ

  የአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻዎችን ለግል አልሚዎች ለመስጠት መመርያ ተዘጋጀ

  ቀን:

   የአዲስ አበባ ከተማ ወንዞች፣ የወንዝ ዳርቻዎች ልማትና የአየር ንብረት ለውጥ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት፣ የወንዞች ዳርቻዎችን የግል ኩባንያዎች እንዲያለሙ የሚያደርግ መመርያ አዘጋጅቶ ለቦርድ አቀረበ፡፡

  በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ የሚመራው የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ ሥራ አመራር ቦርድ ይህን መመርያ ከተቀበለ የግል ኩባንያዎች፣ የቤት ሥራ ማኅበራት፣ ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማትና ግለሰቦች ከፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ የወንዝ ዳርቻዎችን ተረክበው ማልማት የሚችሉበት ዕድል ይፈጠራል፡፡

  በአዲስ አበባ ከተማ ሰባት ዋና ዋና ወንዞች ይገኛሉ፡፡ እነሱም ቡልቡላ፣ ቀበና፣ ሶርአምባ፣ ለኩ፣ ባንች፣ ይቀጡና ጎርደሜ ናቸው፡፡ እነዚህ ሰባት ወንዞች 65 ገባር ወንዞች አሏቸው፡፡ በአጠቃላይ እነዚህ ወንዞች 607 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያላቸው ሲሆን፣ ከ2,000 ሔክታር በላይ መሬት በዙሪያቸው ይገኛል፡፡

  የአዲስ አበባ ወንዞች፣ ወንዝ ዳርቻዎችና አየር ንብረት ለውጥ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ደበላ ብሩ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በዚህ ዓመት 14 ያህል ፕሮጀክቶችን በ180 ሚሊዮን ብር የማልማት ዕቅድ ይዟል፡፡

  ‹‹እኛ የምናለማው በፓይለት ፕሮጀክት ደረጃ ነው፡፡ ከፓይለት ፕሮጀክቶቹ በመነሳት የተቀሩትን የወንዝ ዳር ልማቶች የግሉ ዘርፍ እንዲያለማ ዕድሉን እንፈጥራለን፤›› ሲሉ አቶ ደበላ ገልጸዋል፡፡

  ፕሮጀክቶችን ለግሉ ዘርፍ ለመስጠት መመርያ የሚያስፈልግ በመሆኑ፣ የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ መመርያውን አዘጋጅቶ ለቦርድ ማቅረቡን አቶ ደበላ አስረድተዋል፡፡ የአዲስ አበባ ወንዞች በሙሉ በትንሹና በትልቁ አቃቂ ወንዞች ተጠቃለው በመጨረሻ ሙሉ በሙሉ አባ ሳሙኤል ሐይቅ ይገባሉ፡፡

  እነዚህ ወንዞች ከመኖሪያ ቤት፣ ከሆስፒታሎችና ከኢንዱስትሪዎች በሚወጡ ፍሳሽ ቆሻሻዎች የተበከሉ በመሆናቸው ሙሉ በሙሉ ሕይወት አልባ ሆነዋል፡፡ የትኞቹም ዓይነት ነፍሳት በወንዞቹ ውስጥ መኖር የማይችሉ ከመሆናቸው በተጨማሪ፣ በተለይ የኢንዱስትሪ ብክለቱ የጎላ ድርሻ ያለው በመሆኑ ወንዞቹ ለአትክልትና ፍራፍሬ ልማት መዋል የማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ጥናታዊ ጽሑፎች ያስረዳሉ፡፡

  ወንዞቹን የሚጠቀሙ ዜጎችና እንስሳት ለተለያዩ በሽታዎች እየተጋለጡ መሆናቸውም በጥናታዊ ጽሑፎች ላይ ተገልጿል፡፡ አዲሱ የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት አደገኛ ፍሳሾች በወንዞቹ ውስጥ እንዳይገቡ ከውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን፣ ከአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን፣ እንዲሁም ከደንብ ማስከበር ጽሕፈት ቤት ጋር በጋራ እንደሚሠራ አቶ ደበላ አክለዋል፡፡

  ወንዞቹ ዳግም ሕይወት እንዲዘሩና ዳርቻዎቹም ለመዝናኛና ለተለያዩ አገልግሎቶች እንዲውሉ ለማድረግ፣ የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ የአምስት ዓመት ዕቅድ አውጥቷል፡፡

  ይህ ሥራ ዘለቄታ እንዲኖረው የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱን በቢሮ ደረጃ ለማዋቀር የከተማው አስተዳደር ጥናት እያካሄደ መሆኑም አቶ ደበላ ጠቁመዋል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ዳግም ነፍስ የዘራው የተማሪዎች ማርች ባንድ

  የሙያው ፍቅር ያደረባቸው ገና በልጅነታቸው ነው፡፡ በ1970ዎቹ መጀመርያ፣ ለቀለም...

  በስንደዶና ሰበዝ የተቃኘው ጥበብ

  በአንዋር አባቢ ተወልዳ ያደገችው መሀል አዲስ አበባ አራት ኪሎ ነው፡፡...

  አዲስ ጥረት የሚጠይቀው  ኤችአይቪ  ኤድስን  የመግታት  ንቅናቄ

  ‹‹ኤችአይቪ በመላው ዓለም  በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያጠቃ ዋነኛ የሕዝብ...

  የኅትመት ብርሃን ያየው ‹‹የቃቄ ወርድዎት›› ቴአትር

  ከአራት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ ይታይ...