አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
- ግማሽ ኪሎ ፓስታ
- 2 የሾርባ ማንኪያ የደቀቀ ነጭ ሽንኩርት
- 4 የሾርባ ማንኪያ (100 ግራም) የገበታ ቅቤ
- ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጨው
- ግማሽ የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ
- 2 የደቀቀ ቃሪያ
አዘገጃጀት
- ፓስታውን ለብቻ መቀቀል፣
- ቅቤ መጥበሻ ላይ ማቅለጥ፣
- በላዩ ነጭ ሽንኩርት መጨመር፤
- ትንሽ አቁላልቶ ፓስታውን መጨመርና ጨውና ቁንዶ በርበሬውን አስከትሎ ከለወሱ በኋላ ቃሪያውን ነስንሶ በትኩሱ ማቅረብ
- ከደብረወርቅ አባተ (ሱ ሼፍ)፣ የውጭ ምግቦች አዘገጃጀት