Monday, July 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ይድረስ ለሪፖርተርመንገዶቻችን መቅሰፍት ከመሆን ይታገዱ

መንገዶቻችን መቅሰፍት ከመሆን ይታገዱ

ቀን:

የአዲስ አበባ መንገዶች በአብዛኛው ለአደጋ የሚዳርጉ እየሆኑ የሰው ሕይወት እየቀጠፉና ጉዳት እያደረሱ እንዲሁም ንብረት እንዲወድም ሰበብ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡

የመንገዶቻችን አደገኛነት ይበልጥ የሚጨምረውና የሚከፋው ደግሞ በክረምቱ ወራት ወቅት መሆኑ ለዘመናት አብሮን የኖረ እውነታ ነው፡፡ ክረምት በመጣ ቁጥር ውኃ አቁረው፣ ውኃ እየተፉ መንገድ የሚዘጉ ጎርፎች እንደልብ ናቸው፡፡ የጎርፍ መጥለቅለቅ ለሰው ሕይወት መጥፋት ሰበብ መሆኑ ቢታወቅም በያመቱ ቀድሞ ለመከላከል የሚደረጉ ጥረቶች ችግር አለባቸው፡፡ ዝግጅቶች ስለማይደረጉ፣ አደጋ ደርሶ እንኳ የሰው ሕይወት በፍጥነት ለመታደግ አሁንም ሽቅብ ሽቅብ የሚያሰኙ ችግሮች አሉብን፡፡ መቼ እንደሚቀረፉ ማሰብም ይከብዳል፡፡

ጎርፍም ከባድና ሞገደኛ ዝናብም ተፈጥሯዊ ክስተቶች ናቸው፡፡ ማስቀረት አይቻልም፡፡ ይሁንና እንዳመጣጣቸው ለመቋቋም የሚያስችል ሥርዓት ግን መፍጠር ይቻላል፡፡ አገሪቱ እንዳዲስ ያደራጀችው ብሔራዊ የአደጋና የስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ብዙ ምላሽና መፍትሔ እንደሚኖረው ይታመናል፡፡ ሌሎችም በየፈርጁ ያሉ ተቋማት ሚናቸው እንደሚጎላ እናምናለን፡፡ ይሁንና በጎርፍ መጥለቅለቅና መቸገራችን እየባሰበት ይገኛል፡፡

በየክልሎች የሚደርሰው አደጋና የሚከሰተው ሞት፣ የሚደርሰው የንብረት ውድመትና ጥፋት የሚደርሰው የመንደሮች መጥለቅለቅና የእርሻ ማሳያዎች ውድመት ከምና ካቻምና እየበሳሰበት መጥቷል፡፡ ይህንን መመከትም መከላከልም የመንግሥት ዋና ተልዕኮ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ተግባራዊ ዕርምጃው ግን ይናፈቃል፡፡

የክልሎቹን እዚህ ላይ እናቆየውና አዲስ አበባን በጥቂቱ እንቃኝ፡፡ የሚጠግናቸው ያጡ፣ እዚህም እዚያም የተቦዳደሱና የተቦረቦሩ መንገዶች ተበራክተዋል፡፡ በእነዚህ መንገዶች ምክንያትም አደጋ ይባባሳል፡፡ መኪኖች መንገድ ጥሰው ይወጣሉ፡፡ ይገለበጣሉ፡፡ ለዚህ ጉዳይ አስቸኳይ መፍትሔ በመስጠት መንገዶቹን ማሻሻልና መጠገን አዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ቢሆንም ተቋሙ ቸል ያለ ይመስላል፡፡ ጎርፍ ከሚሸረሽራቸው ይበልጡን ደግሞ በሕንጻ ግንባታ ሰበብ የሚታጠሩ የእግረኛና የመኪና መንገዶች ላይ የሚደርሰው አደጋም እየበዛ መጥቷል፡፡ ይህንንም ባለሥልጣኑ ሊያስከብር እንዳልቻለ እያየን፣ እየታዘብን እንገኛለን፡፡ በኪሎ ሜትር ስንትና ስንት ሚሊዮን ብር የሚፈስባቸው መንገዶች ዓመት ሳይቆዩ ውኃና ጭቃ አበላሽቶ ሲጥላቸው የሚገደው አካል ጠፍቷል፡፡

የጎርፍን ነገር ካነሳን የፍሳሽ ማስተላለፊያ ቦዎች መደፈን፣ በየጊዜው በቆሻሻ እየተዘጉና ተንከባካቢ አጥተው የሚበላሹ ፍሳሽ ማስወገጃዎች በሚፈጥሩት መጥፎ ጠረንና በሚያስከትሉት ድንገኛ ጎርፍ ምክንያት ተጎጂ ከሆኑን መካከል አንዱና ቦሌ አካባቢ የሚገኝ ትልቅ ሆቴል ላይ ሰሞኑን የተከሰተው ጎርፍ አስገራሚ ነበር፡፡ ባለኮከብ የሆነው ሆቴል የውጭ እንግዶች የሚያርፉበት ትልቅ ሆቴል ቢሆንም በከተማው እምብርት መካከል በተፈጠረ ጎርፍ ጉዳት ደርሶበት በድንገኛ አደጋ ሠራተኞች ታግዞ ከደረሰበት መጥለቅለቅ እንዲተርፍ የተደረገው በስንት አበሳ ነበር፡፡

እንዲህ ያሉ ጉዳትና አደጋዎች እንዲህ ባሉ ተቋማት ላይ መድረሳቸው የከተማውንና የአገሪቱን ገጽታ በቀላሉ ስለሚያበለሽ መንግሥት፣ የሕዝቡም መጎዳትና መጉላላት ታይቶት በቶሎ መፍትሔና እርምርት እንዲሰጥበት ይጠየቃል፡፡

(ማን ያህል ቸኮል፣ ከአዲስ አበባ)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሚዲያው በሕዝብ የህሊና ችሎት ከተዳኘ በቂ ነው!

መሰንበቻውን ድንገት ሳይታሰብ ያለ ማስጠንቀቂያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ...

የባህር በር ጉዳይ

በታምሩ ወንድም አገኘሁ ድሮ ድሮ ገና ልጅ ሆኜ ፊደል እንደቆጠርኩ...

አገሩ ፖለቲካዊ ስክነትና መደማማጥ ያስፈልገዋል

በንጉሥ ወዳጀነው    ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ ቤት ነች፡፡ ‹‹ጥያቄዬ ተመለሰልኝ››፣...

የመንግሥት የሰብዓዊ መብት ተቋም ለምን የመንግሥት ሚዲያን ማስተማር አቃተው

በገነት ዓለሙ የአገራችን የ2016 የበጀት ዓመት መሰናበቻና የአዲሱ የ2017 በጀት...