Wednesday, February 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መማር ማስተማር ተቋረጠ

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መማር ማስተማር ተቋረጠ

ቀን:

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መማር ማስተማር ሙሉ በሙሉ መቋረጡ ታወቀ፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሐረጓ ማሞ ዓርብ ታኅሳስ 13 ቀን 2010 ዓ.ም. ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መማር ማስተማር ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል፡፡

ወ/ሮ ሐረጓ እንዳሉት፣ በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ድንጋይ ውርወራና ጩኸት ተከስቷል፡፡ በተፈጠረው ሁከት የተጎዳ ተማሪ መኖሩንና አለመኖሩን የተጠየቁት ወ/ሮ ሐረጓ፣ ‹‹ድንጋይ ውርወራ ካለ ሊመታ የሚችል ተማሪና ቁስ የለም ማለት አይቻልም፤›› ብለዋል፡፡

በተፈጠረው ሁከትና ትምህርት መቋረጥ ምክንያቱ ገና በመጣራት ላይ መሆኑንም አክለው ገልጸዋል፡፡ ጉዳዩን ለማረጋገጥም ከተማሪዎች ጋር ውይይት ለማድረግ ሙከራ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ተማሪዎችን ለማሳመን ብቻ ሳይሆን፣ የሚያነሷቸው ጥያቄዎች በአግባቡ ለመመለስ ከአመራሩ ጋር ውይይት መደረጉንም ጠቁመዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በተመሳሳይ ከረቡዕ ታኅሳስ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረ ሁከት አብዛኛዎቹ ተማሪዎች ከግቢ ወጥተው መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡ ‹‹ነገር ግን ሁከት የሚፈጥሩ ተማዎችን የማጣራት ሥራ ተሠርቶ ተማሪው ወደ ትምህርቱ ገብቷል፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹ድንጋይ መወርወር ባይኖርም ከተመገቡ በኋላ ከግቢ በመውጣት፣ ክፍል ያለመግባት ችግሮች ተከስተው ነበር፤›› ብለዋል፡፡

ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የማስተማር ሥራቸውን አቋርጠው ከነበሩት 19 ዩኒቨርሲቲዎች መካከል፣ አብዛኛዎቹ ወደ ቀድሞ ሥራቸው መመለሳቸውን ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡

በአምቦ፣ በመቱና በወለጋ ዩኒቨርሲቲዎች ተቋርጦ የነበረው የማስተማር ሥራ መጀመሩንም ገልጸዋል፡፡ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ትርምስ እንዲፈጠር የሚፈልግ ኃይል እንዳለ የጠቆሙት ዳይሬክተሩ፣ ችግሩን ተሸካሚ የሆኑ ተማሪዎችም ሆኑ ከተማሪዎች ጋር ተመሳስሎ ወደ ግቢ የሚገባ ኃይል የለም ማለት እንደማይቻል ጠቁመዋል፡፡

በአገሪቱ የመማር ማስተማር ሥራ ተቋርጦባቸው በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት ለመጀመር ስምምነት በመፍጠር፣ ሥራ የመጀመር ሒደት ላይ መደረሱን ገልጸዋል፡፡ ‹‹በአብዛኛው ዩኒቨርሲቲዎች ማለት ይቻላል የማስተማር ሥራ ተጀምሯል፡፡ ይህ ማለት ግን የተንጠባጠቡ ተማሪዎች የሉም ማለት አይቻልም፤›› ብለዋል፡፡

በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ሥራ ከሞላ ጎደል መጀመሩን የጠቆሙት ወ/ሮ ሐረጓ፣ በኢንጂነሪንግ ካምፓስ እስካሁን እንደተቋረጠ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

‹‹በመቱ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መሉ በሙሉ ገብተው እየተማሩ ነው ባይባልም፣ መምህራን ግን እያስተማሩ ነው፤›› ብለዋል፡፡

በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ብሔር ተኮር ግጭት ተቀስቅሶ የአንድ ተማሪ ሕይወት ካለፈ በኋላ፣ በአሥራ ዘጠኝ ዩኒቨርሲቲዎች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የማስተማር ሥራ ተቋርጦ እንደነበር መዘገባችን አይዘነጋም፡፡

ባለፈው ሳምንት ተመሳሳይ ግጭት ተከስቶ የተማሪ ሕይወት ባይጠፋም፣ በድሬዳዋና በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ሌላ አዲስ ተቃውሞ ታይቷል፡፡ በተለይ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በተቀሰቀሰው ሁከት በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በአዲግራት፣ በመቱ፣ በወልዲያ፣ በአምቦና በወለጋ ዩኒቨርሲቲዎች የማስተማር ሥራ እንደተጀመረ እየተነገረ ቢሆንም፣ አብዛኛዎቹ ተማሪዎች ወደ ክፍል ገብተው ትምርታቸውን እየተከታተሉ እንዳልሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

በአምቦ፣ በመቱና በወለጋ ዩኒቨርሲቲዎች ይማሩ የነበሩ ከአራት መቶ በላይ የትግራይ ብሔር ተወላጅ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው እንደወጡና ለትምህርት ሚኒስቴር ጥያቄ ማቅረባቸውን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን፣ ተማሪዎቹ ወደ ዩኒቨርሲቲዎቻቸው በመሄድ ትምህርት እንዳልጀመሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ከአዲግራት፣ ከወልዲያ፣ ከመቱ፣ ከአምቦና ከወለጋ ዩኒቨርሲቲ በመውጣት ወደ የአካባቢያቸው እየተመለሱ ያሉ ተማሪዎች እንዳሉ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ወደ ቤተሰቦቻቸው ሄደው የነበሩ ተማሪዎች እንዲመለሱ በቴሌቪዥን፣ በሬዲዮና በጋዜጣ መልዕክት ለማስተላለፍ በዝግጅት ላይ እንደሆነ ወ/ሮ ሐረጓ ተናግረዋል፡፡

 

  

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...