Saturday, June 10, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበአዲስ አበባ የመንገዶች ባለሥልጣን የቀድሞ አመራሮች ላይ መንግሥት ማጣራት እንደሚጀምር ተጠቆመ

በአዲስ አበባ የመንገዶች ባለሥልጣን የቀድሞ አመራሮች ላይ መንግሥት ማጣራት እንደሚጀምር ተጠቆመ

ቀን:

ላለፉት በርካታ ዓመታት የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣንን ሲመሩ ቆይተው ከኃላፊነታቸው የተነሱ አመራሮች ስላከናወኗቸው ተግባራትና ለምን ከኃላፊነታቸው ሊነሱ እንደቻሉ፣ መንግሥት ማጣራት እንደሚጀምር ተጠቆመ፡፡

የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት መንግሥት ባለሥልጣኑን በሚመለከት ማጣራት እንደሚጀምር የገለጸው፣ ኢሕአዴግ በጥልቀት ለመታደስ ማድረግ ስለሚገባው ጉዳዮች አስመልክቶ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ሰብሳቢነት ለሦስት ቀናት በሚኒስትሮች ምክር ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ፣ ከፌዴራል ተቋማት ለተገኙ ተወካዮች ማብራሪያ በተሰጠበት ወቅት ነው፡፡

በተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ኃላፊ ሆነው የሚሾሙ ባለሥልጣናት  ከኃላፊናቸው ሲነሱም ሆነ በከፍተኛ ሹመት ወደ ሌላ ሲዘዋወሩ ለሕዝብ ለምን በግልጽ እንደማይነገር ከተሰብሳቢዎቹ ጥያቄ ከተነሳ በኋላ፣ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን አመራሮች ከኃላፊነታቸው ስለመነሳታቸው እንጂ፣ በምን ምክንያትና ስለቀጣዩ ዕርምጃ አለመገለጹ እንደማሳያ መነሳቱን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

ተሰብሳቢዎቹ ላነሱት ጥያቄ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም በሰጡት አስተያየት፣ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን አመራሮች ከኃላፊነታቸው ሲነሱ የምሥጋናና የውዳሴ ደብዳቤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰጣቸው ቢሆንም፣ መንግሥት ግን የማጣራት ሥራ እንደሚጀምር መናገራቸውን ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በደንብ ቁጥር 7/1990 መሠረት የተቋቋመ ተቋም ሲሆን፣ በወቅቱ የመንገድ ሽፋን 5.52 በመቶ ነበር፡፡ በ2007 በጀት ዓመት 19.8 በመቶ መድረስ ችሏል፡፡ ባለሥልጣኑን በዋና ሥራ አስኪያጅነት ኢንጂነር ፍቃዱ ኃይሌ ለ14 ዓመታት መርተውታል፡፡

ኢንጂነር ፍቃዱ ግልጽ ባልሆነ ምክንያት በነሐሴ ወር 2008 ዓ.ም. ከምክትል ሥራ አስኪያጁ አቶ ግደይ ህሽ ጋር ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አያሌ የውኃ “ጠርሙሶች”ን በጫንቃ

መሰንበቻውን በአይቮሪ ኮስት መዲና አቢጃን የምትኖር አንዲት ሴት፣ በሚደንቅ...

ወልቃይትን ማዕከል ያደረገው የምዕራባዊያን ጫና

በትግራይ ክልል የተከሰተው የዕርዳታ እህል ዘረፋ የዓለም አቀፍ ተቋማት...

ከቀጣዩ ዓመት በጀት ውስጥ 281 ቢሊዮን ብሩ የበጀት ጉደለት ነው ተባለ

ለቀጣዩ በጀት ዓመት ከቀረበው 801.65 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ በጀት...