Thursday, October 6, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊጠጥቶ ማሽከርከርን ለማስቆም ዘመቻ ተጀመረ

  ጠጥቶ ማሽከርከርን ለማስቆም ዘመቻ ተጀመረ

  ቀን:

  በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ ለሚከሰቱ 1.2 ሚሊዮን አደጋዎች አምስት ምክንያቶች ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ በተለይ ሁለቱ በፍጥነት ማሽከርከርና ጠጥቶ ማሽከርከር ናቸው፡፡ እነዚህም በተጠናቀቀው 2008 ዓ.ም. በመላ አገሪቱ ለ4,358 ሰዎች ሕይወት መጥፋት ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው፡፡ በተለይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመሆን በሚቀጥሉት ሳምንታት ጠጥቶ ማሽከርከርን ለማስቆም ዘመቻ በይፋ መጀመሩን አስታውቋል፡፡ ባለፈው ዓርብ መስከረም 13 ቀን 2009 ዓ.ም. ጠጥቶ ማሽከርከር ለማስቆም ዘመቻ ለመጀመር ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡ በመግለጫው ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው፣ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዶ/ር ሰሎሞን ኪዳኔ፣ በአጋርነት የሚሠራው የቫይታል ስትራቴጂ ፕሬዚዳንትና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ማስተር ሆዙ ሉዋ ካስትሮን ጨምሮ በርካታ የባለድርሻ አካላት ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img