አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
- 2 ትልልቅ የተቀቀለ ድንች
- 1 ፍሬ ነጭ ሽንኩርት የተፈጨ
- 1 የሾርባ ማንኪያ በደቃቁ የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት
- ቁንጥር ጨው
- 1 የስኳር ማንኪያ ፍርኖ ዱቄት
- ቁንጥር ቁንዶ በርበሬ
- ደረቅ የዳቦ ዱቄት
- ዘይት ለመጥበሻ
አዘገጃጀት
- ድንቹን በጎድጓዳ ሳህን አድርጎ መፍጨት
- ከላይ የተዘረዘሩትን ድንቹ ላይ ጨምሮ አንድ ላይ ማሸት
- መጥበሻ አግሎ ዘይት መጨመርና ማፍላት
- የተፈጨውን ድንች በእጃችን እየጠፈጠፍን በዳቦ ዱቄቱ ላይ በሁለቱም በኩል ማንከባለልና የፈላው ዘይት ላይ ጨምሮ በሁለቱም በኩል ቡኒ እስኪሆን ድረስ መጥበስ፡፡ ዘይቱ እንዲመጥ ስናወጣው ወፍራም ሶፍት ላይ ማስቀመጥ
- ለማባያ ለብቻው ካቻፕ [እንዳስፈላጊነቱ] አድርጎ ማቅረብ
- አዝመራ ካሳሁን ‹‹ከቤት እስከ ትምህርት ቤት›› (2008)