Monday, October 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ሥነ ፍጥረትየዱር ድመት

የዱር ድመት

ቀን:

ድመትን የቤት አውሬ፣ ለማዳ የሚሏት አሉ፡፡ ዓይኗ ልዩ በመሆኑም ድብርቅ ዓይን፣ ያይጥ ጠላት የሚላት መዝገበ ቃላቱ፣ ዐይጥን የሚያስደምም፣ የሚያስፈራ፣ የሚያፈዝ፣ ዐይጥ ለመያዝ፣ ዝም፣ ጸጥ የሚል ሲልም ያክልበታል፡፡ ዐይነ ምድሩን መሬት ቆፍሮ የሚቀብር፣ ነገዱ ያንበሳ የነብር ነው፡፡ ከቤት የማይለይ፣ ከሰው ዘንድ ከሚኖረው ለማዳ ድመት ሌላ በበረሃ የሚኖር ፍጹም አውሬ የሆነ የዱር ድመት አለ፡፡

መጠኗ አነስተኛ የሆነ የዱር ድመት በሰሜን አፍሪካ፣ በደቡብ ምዕራብና መካከለኛ እስያ ውስጥ እንደምትኖር ድርሳናት ያመለክታሉ፡፡

‹‹ሳንድ ካት›› የምትባለው የዱር ድመት፣ በአገርኛ ብሂል ‹‹ቀን ቀን ለሠራዊት ማታ ማታ ለአራዊት›› እንደሚባለው፣ የዱር ድመቷ ግዛቷ ሌሊት ነው፡፡

በጄ ደብሊው ዶት ኦርግ ድረ ገጽ እንደተጻፈው፣ ቀለቧን የምትሠፍረው ሌሊቱን ሙሉ በማደን ነው፡፡ በአሸዋማ መሬት ላይ እየተመላለሰች የዐይጥ ዝርያዎችን ታንቃቸዋለች፡፡ የምትበላውን በልታ ስትጠግብ የተራረፉትን አሸዋ ውስጥ ትቀብራለች፡፡ ድረ ገጹ የዚህችን የዱር ድመት አንዳንድ አስደናቂ መረጃዎች እንደሚከተለው ገልጾታል፡፡  

  • ጆሯቸው ከሩቅ ስለሚሰማ የሚያድኑት እንስሳ ከመሬት በታች ቢሆንም እንኳ ሊያገኙት ይችላሉ
  • ተባዕቱ ድመት ተጓዳኝ ለማግኘት ቀጭን የሆነ ኃይለኛ ጩኸት ያሰማል። እንስቷም ይህንን ድምፅ ከረጅም ርቀት መስማት ትችላለች
  • መዳፎቻቸው በፀጉር የተሸፈኑ ናቸው፤ ይህም በሚሄዱበት ጊዜ አሸዋ ውስጥ እንዳይሰምጡ የሚረዳቸው ከመሆኑም ሌላ፣ መዳፋቸውን ቅዝቃዜም ሆነ ሙቀት እንዳይጎዳው ይከላከልላቸዋል
  • የጆሮዎቻቸው ውስጠኛ ክፍል ጥቅጥቅ ባለ ነጭ ፀጉር የተሸፈነ መሆኑ፣ ነፋስ በሚኖርበት ጊዜ አሸዋ ጆሯቸው ውስጥ እንዳይገባ ይከላከልላቸዋል
  • የእነዚህ ድመቶች መዳፍ ጥቅጥቅ ባለ ፀጉር የተሸፈነ በመሆኑ፣ ዱካቸውን ተከታትሎ ማግኘት አስቸጋሪ ነው
  • እነዚህ ድመቶች ከሚበሉት እንስሳ በሚያገኙት ውኃ ብቻ መኖር ይችላሉ
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...