Wednesday, September 28, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዝንቅቄንጠኛው የመጥረጊያና የመወልወያ ገበያ ሲኤምሲ የጋራ መኖሪያ ቤቶች አቅራቢያ

  ቄንጠኛው የመጥረጊያና የመወልወያ ገበያ ሲኤምሲ የጋራ መኖሪያ ቤቶች አቅራቢያ

  ቀን:

  ኢትዮጵያዊ ነኝ!

               (በድሉ ዋቅጅራ)

  ኢትዮጵያዊ ነኝ!
  በላሊበላ አስቀድሼ፣ ሸህ ሁሴን ባሌ የተገኘሁ፤
  በአባ ገዳ ተመራርቄ፣ መካ ላይ እርስቅ ያገኘሁ፡፡
  ይርጋለም ያጋጥኳትን ላም፣ ወለጋ ላይ አሰርሬ፤
  ትኩስ እንገርዋን የጠጣሁ፣ አክሱም ላይ ጥገት አስሬ፤
  ሰሜን ያለብኩትን ወተት፣ በአርሲ ጮጮ የሞላሁ፤
  ጋምቤላ ወተቱን ንጬ፣ የሀረሪ ቆንጆ የቀባሁ፡፡
  ወሰን የለሽ እግረ ፌንጣ፣
  ሞተ ሲሉኝ ብን – ትር የምል፣ ሄደ ሲሉኝ የምመጣ፤
  የቅዠት ምች፣ ህልም ፈቺ . . . ዳነ ሲሉኝ የማገረሽ፤
  ወሰን አልባ እግረ ሞረሽ፡፡
  ኢትዮጵያዊ ነኝ!!

  ***********

  የሰዎችን ስሜት የሚያነብ መሣሪያ

  ኮምፒተርዎ አልያም ሞባይል ስልክዎ ስሜትዎን መንገር ቢችልስ? በማሳቹሴትስ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች በዋየርለስ ሲግናል የሰዎችን ስሜት ማንበብ የሚችል መሣሪያ መሥራታቸውን የአሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል፡፡ መሣሪያው በዋነኝነት የሰዎችን የልብ ምት በማወቅ የሰዎቹ ስሜት ሐዘን ወይስ ደስታ የሚለውን ይተረጉማል፡፡ ተመራማሪዎቹ እንዳሉት የሠሩት መሣሪያ 87 በመቶ ትክክል ነው፡፡ የልብ ምት ፍጥነትን በመለካት የተለያዩ የሰውነት ክፍሎች በተወሰነ የልብ ምት ውስጥ እንዴት እንደሚሆኑ በማወቅ ሰዎች እየተሰማቸው ያለው ደስታ፣ ሐዘን፣ ቁጣ ወይስ ሌላ የሚለውን መሣሪያው ያውቃል፡፡

  *********

  የስድስት ዓመቱ ሕፃን ለኦባማ ደብዳቤ ጻፈ

  ከጥቂት ሳምንታት በፊት መገናኛ ብዙኃንና ሶሻል ሚዲያ ላይ ሰፊ ሽፋን አግኝቶ የነበረው የሶሪያውን ሕፃን አምራን ዳክኒሽን ቢልኩለት ከቤቱ እንደሚያኖረው በመግለጽ የስድስት ዓመቱ ሕፃን ለኦባማ ደብዳቤ መጻፉን ዘ ኢንዲፔንደንት ዘገበ፡፡ የአምስት ዓመቱ ዳክኒሽ ሁኔታ በጦርነት ሰላማዊ ዜጎች ምን ድረስ ሊሰቃዩ እንደሚችሉ ምስክር ነው፡፡ በአሌፖ ከፈራረሰ የአንድ ቤተሰብ መኖሪያ ቤት ፍርስራሽ ስር የወጣውና ፊቱ በደምና በአቧራ የተሸፈነው ሶሪያዊ ሕፃን ፎቶግራፍ በወቅቱ በማኅበራዊ ድረገጽ በብዙዎች ሼር ተደርጎ ነበር፡፡ ሕፃኑ አሌክስ ደግሞ ለኦባማ በጻፈው ደብዳቤ ‹‹ቤተሰብ እንሰጠዋለን የእኛ ወንድምም ይሆናል›› ብሏል፡፡ ኦባማም ሕፃኑን (አሌክስ) ሰዎችን በመጡበት ቦታ፣ በገፅታቸው ወይም በሌላ መልኩ እንዲጠራጠር ወይም እንዲፈራ ይህቺ ዓለም ያላስተማረችው ብለውታል፡፡

  ********

  ኮንዶም የእጅ ጌጥ ሆነ

  በኡጋንዳ አኮኮሮ ጤና ማዕከል የሴቶች ኮንዶምን ለአካባቢው ኗሪዎች ቢያከፋፍሉም ኗሪዎቹ የኮንዶሙን ጫፍ እየቆረጡ የእጅ ጌጥ ማድረጋቸውን ዴይሊ ሞኒተር ዘግቧል፡፡ የአኮኮሮ ጤና ማዕከል ነርስ ‹‹ኮንዶሙን እንደሚገባው ከመጠቀም ይልቅ ሴቱም ወንዱም ለእጅ ጌጥ እየተጠቀመበት ነው›› በማለት ተናግሯል፡፡ ባለፉት አራት ወራት በአኮኮሮ ግዛት 200 የሴት ኮንዶሞች ለተጠቃሚዎች መሠራጨታቸውንም ዘገባው አመልክቷል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ‹‹ለሰላምና ለዕርቅ መሸነፍ የለብንም›› ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ

  የሰው ልጅ ጠብን በዕርቅ፣ በደልን በይቅርታ፣ ድህነትን በልማት፣ ክህደትን...

  መፍትሔ አልባ ጉዞ የትም አያደርስም!

  ኢትዮጵያ ችግሮቿን የሚቀርፉ አገር በቀል መፍትሔዎች ላይ ማተኮር ይኖርባታል፡፡...

  ጦርነቱና ውስጣዊ ችግሮች

  መስከረም 14 ቀን 2015 ዓ.ም. የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ባወጣው...