Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየህዳሴውን ግድብ የሚያጠኑ ሁለት የፈረንሣይ ኩባንያዎች ስምምነት ፈረሙ

የህዳሴውን ግድብ የሚያጠኑ ሁለት የፈረንሣይ ኩባንያዎች ስምምነት ፈረሙ

ቀን:

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማጥናት የኢትዮጵያ፣ የግብፅና የሱዳን ባለሥልጣናት ለዓመታት ያደረጉት ውይይት ተጠናቆ ግድቡን የሚያጠኑት ኩባንያዎች ስምምነት ፈረሙ፡፡

ጥናቱን ለማከናወን የተመረጡት ቢአርኤል ኢንጂነርስና ኤርቴሊያ የተባሉት ሁለቱ የፈረንሣይ ኩባንያዎች ከሦስቱ አገሮች ብሔራዊ የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች ስምምነት፣ ማክሰኞ መስከረም 11 ቀን 2008 ዓ.ም. በሱዳን ካርቱም መፈራረማቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በኢትዮጵያ በኩል ስምምነቱን የፈረሙት የህዳሴውን ግድብ በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግሥት የቴክኒክ አማካሪና የብሔራዊ የቴክኒክ ኮሚቴው ሰብሳቢ ኢንጂነር ጌድዮን አስፋው ናቸው፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ስምምነቱን የሦስቱም አገሮች የውኃ ጉዳይ ሚኒስትሮች በእማኝነት እንደታዘቡት ለማወቅ ተችሏል፡፡ ቢአርኤል ኢንጂነርስ ዋነኛው ተዋዋይ ሲሆን ጥናቱን በተመለከተ ሕጋዊ ተጠሪነት እንዳለበትም ለማወቅ ተችሏል፡፡ አርቴሊያ የተባለው ሌላው የፈረንሣይ ኩባንያ የጥናቱን 30 በመቶ ብቻ በማከናወን ሪፖርቱን ለዋናው ኩባንያ ያቀርባል፡፡

ሁለቱ ኩባንያዎች በጋራ የሚያጠኑት የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውኃ አያያዝና አለቃቀቅና የግድቡ መገንባት በሱዳንና በግብፅ ላይ የሚኖረውን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ መገምገም ነው፡፡

ጥናቱ ከተጓተተባቸው ምክንያቶች አንዱ የግድቡ በግብፅ ግብርና ላይ የሚያደርሰው ተፅዕኖ የጥናቱ አካል እንዲሆን ግብፅ በመጠየቋና ኢትዮጵያ ደግሞ ይህንን በመቃወሟ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በመጨረሻ ላይ ግን የኢትዮጵያ ተቃውሞ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ ሁለቱ ኩባንያዎች በ12 ወራት ውስጥ አጠናቀው በሚያቀርቡት ጥናት 4.5 ሚሊዮን ዶላር እንደሚከፈላቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...