Wednesday, February 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናተቃዋሚ ፓርቲዎች በአንድነት እንዲሠሩ መድረክ ጥሪ አቀረበ

ተቃዋሚ ፓርቲዎች በአንድነት እንዲሠሩ መድረክ ጥሪ አቀረበ

ቀን:

ኢሕአዴግ ላለፉት 25 ዓመታት የሕዝቡን የተቃውሞ እንቅስቃሴ አፍኖ ሥልጣን ላይ እንዲቆይ ያስቻለው የፀረ አምባገነናዊ አገዛዙ ትግል የተበታተነና የተከፋፈለ ሆኖ መቆየቱ በመሆኑ፣ ሁሉም ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በአንድነት እንዲታገሉ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ጥሪ አቀረበ፡፡

የትግል አጀንዳዎችን አገር አቀፍ በማድረግ ረገድ በርካታ ክፍተቶች ስለሚታዩ፣ በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችና በትግሉ አስተባባሪዎች በኩል የሚታየውን ችግር ማስተካከል እንደሚያስፈልግ መድረክ አሳስቧል፡፡

መድረክ ይህን ያስታወቀው መስከረም 2 ቀን 2009 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ነው፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች ሕዝቡ በሰላማዊ አግባብ ሲያካሂድ የቆየው ፍትሐዊ ትግል ሰሚ በማጣቱና ምላሹም የኃይል ዕርምጃ በመሆኑ ነው ብሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት በብዙ አካባቢዎች ትግሉ ወደ ሰላማዊ እምቢተኝነት መሸጋገሩን መድረክ ጠቁሞ፣ የዚህ ሁሉ ምክንያት ደግሞ ‹‹ገዥው ፓርቲ ለሕዝቦች ሰላማዊ ጥያቄ ባለፉት 25 ዓመታት ሲሰጥ የቆየው የኃይልና የአፈና ዕርምጃ ነው፤›› በማለት ገልጿል፡፡

ስለሆነም የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሕዝባዊ ትግሉ አስተባባሪ የሆኑ ዜጐች ሁሉ የሕዝቡን አንድነት ከሚጐዱ ማናቸውም ተግባራት እንዲቆጠቡ ብሎ፣ ‹‹የአገራችንና የሕዝባችን አንድነት የተረጋገጠበትን ትክክለኛ ዴሞክራሲያዊና ፌዴራላዊ የሆነ ሥርዓት ለመገንባት በጋራ በምናካሂደው ትግል የድርሻቸውን ይወጡ፤›› ሲል ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

በአማራ ክልል በመተማ ከተማና በአካባቢው ከ6,000 በላይ የትግራይ ብሔር ተወላጅ የሆኑ ዜጐቻችንን ለመፈናቀል ያበቃ አስነዋሪ ሁኔታ መከሰቱ እንደሚያሳስበው መድረክ ገልጾ፣ ‹‹ሁሉም የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በሚኖሩባቸው አካባቢዎች ሁሉ በአንድነት ቆመው በፀረ ጨቋኝ አገዛዝ ትግል መተባበር እንጂ እርስ በርስ መጋጨት ፈጽሞ አይገባም፤›› በማለት አሳስቧል፡፡

ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት እንዲቻል በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 60 ንዑስ አንቀጽ 1 እና 3 መሠረት ከሕዝቡ እምነትና ይሁንታ ውጪ በ2007 ዓ.ም. በተካሄደው የተጭበረበረ ምርጫ ላይ ተመሥርቶ የተቋቋመው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ይህንን ፀረ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ያስፈጸመው ምርጫ ቦርድ ፈርሰው፣ ገለልተኛነቱ በሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎችና የኅብረተሰብ ክፍሎች በጋራ የሚታመንበት የምርጫ አስፈጻሚ አካል ተቋቁሞ ነፃ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒነት ያለው ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በአስቸኳይ እንዲካሄድ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት፣ ኢሕአዴግ ከመድረክና ከሌሎች ሀቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር በአስቸኳይ ወደ ድርድር እንዲገባ ጠይቋል፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ የኢሕአዴግ አገዛዝ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱና በሕዝቡ ላይ እያመጣ ያለውን አስቸጋሪ ሁኔታ እንዲገነዘብ፣ መድረክ ያቀረበውን ወቅታዊና ዘላቂ የሆነ የመፍትሔ ሐሳብ በመደገፍ የበኩሉን ሚና እንዲጫወት ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...