Saturday, May 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊበከፍተኛ ባለሥልጣናት ሰብሳቢነት የተጀመረው የመምህራን ውይይት በአብዛኞቹ ተቋማት ቀጥሏል

በከፍተኛ ባለሥልጣናት ሰብሳቢነት የተጀመረው የመምህራን ውይይት በአብዛኞቹ ተቋማት ቀጥሏል

ቀን:

–  በወሊሶ የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ካምፓስ አወያዮች እንዲቀየሩ ተደርጓል

በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን ያሳተፈው ውይይት ከመስከረም 5 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ ቀጥሏል፡፡

በተለይ የተሻለ ውይይትና ክርክር ሊደረግባቸው እንደሚችሉ የተገመቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በከፍተኛ የመንግሥት ባላቸው ባለሥልጣናት የቀጠለ ሲሆን፣ የጎንደርና የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲዎች ውይይቱን ከመስከረም 9 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ያካሂዳሉ፡፡

- Advertisement -

በጎንደርና በባህር ዳር ከተሞች በቅርቡ ተከስቶ ከነበረው ተቃውሞ ጋር በተያያዘ የተከሰተው ግርግር እስኪረጋጋ መጠበቅ በማስፈለጉ፣ ሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲዘገዩ ሳይደረግ እንዳልቀረ የሪፖርተር ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የሥልጠናው ዋነኛ አጀንዳዎች ባለፉት 25 ዓመታት በአገሪቱ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታና ልማት የትምህርት ድርሻ፣ የፌዴራል ሥርዓት፣ የሥነ ምግባርና የሥነ ዜጋ ትምህርቶች የፈጠሩት ተፅዕኖዎች የሚሉት እንደሚገኙ መጠቀሳቸው ይታወሳል፡፡

በዚህም መሠረት ከመስከረም 5 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በበርካታ የትምህርት ተቋማት ውይይቱን ሲጀምሩ፣ በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ውይይት ለመጀመር መፈራራት ታይቶባቸው እንደነበርም ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተጨማሪም በተወሰኑ የትምህርት ተቋማት መምህራን በአወያዮቹ ደስተኛ እንዳልነበሩም የገለጹ አሉ፡፡

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሚካሄደውን ውይይት የመሩት የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሊቀመንበር የሆኑትና በኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት የወጣቶች ሊግ ሰብሳቢዋ ወ/ሮ ሙፈርያት ከማል፣ ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጋር በመጣመር ነው፡፡ ሰብሳቢዋም ከፍተኛውን የውይይት ጊዜ መንግሥት ባለፉት 25 ዓመታት አስመዝግቤያቸዋለሁ የሚላቸውን ስኬቶች ላይ ለማብራሪያነት ሲጠቀሙበት፣ በወቅታዊ ጉዳዮች ለሚነሳላቸው ጥያቄ ቀጥተኛ መልስ ከመስጠት ይልቅ በማድበስበስ ማለፋቸውን አንድ በመሳተፍ ላይ የሚገኙ መምህር ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ተሳታፊዎች በወቅታዊ ጉዳዮችና የመንግሥት ተሿሚዎችን የሕግ ጥሰት በሚመለከት ጥያቄዎች መነሳታቸውንና ክርክር እየተደረገ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡

የመGለ ዩኒቨርሲቲ በሐሙስና በዓርብ ውሎው በአብዛኛው ውይይቱ ያተኮረው ተመሳሳይ አጀንዳ ላይ ሲሆን፣ የተነሱት ጥያቄዎች ከመወያያ አጀንዳው ሳይርቅ ቢሆንም  ከኢኮኖሚ ተጠቃሚነት፣ ከወጣቶች የሥራ ፍላጎትና ከመናገር ነፃነት ጋር በተገናኙ ጥያቄዎች ተነስተው ክርክሮች እንደተደረጉ ተሳታፊ የሆኑት መምህር ዓብይ ጨልቀባ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የመGለው ውይይት በዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢና በትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር አዲስ ዓለም ባሌማ እየተመራ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡ እንደ መምህር ዓብይ ገለጻ በሚቀጥሉት ቀናት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጠንከር ያሉ ክርክሮች ሊነሱ ይችላሉ፡፡

በአምቦ ዩኒቨርሲቲም የመምህራኑ ውይይት ሲካሄድ በተለይ በዩኒቨርሲቲው የወሊሶ ካምፓስ ግን በመጀመርያው ቀን ውሎ ውይይት አልባ የነበረ ሲሆን፣ ተወያይ መምህራኑና ሠራተኞች በአወያዮቹ ደስተኛ እንዳልነበሩ ገልጸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ባለፈው ዓርብ ዕለት በነበረው የሁለተኛው ቀን ውይይት አወያዮቹ ተቀይረው በፓርላማ የአካባቢው ተወካይና የበጀትና ፋይናንስ አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ገነት አበበ ከአምቦ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ምትኩ ቴሶ ጋር ውይይቱን በመምራታቸው፣ የውይይት መንፈስ ማንሰራራት መቻሉን በዩኒቨርሲቲው የፖለቲካ ሳይንስ መምህር የሆኑት አቶ ሥዩም ተሾመ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ውይይቱን ለመምራት ተመድበው የነበሩት ካድሬዎች በፖለቲካው ብዙም ያልቆዩና ከአቅም በታች ናቸው በሚል መንፈስ፣ መምህራኑም ሆኑ ሌሎች የአስተዳደሩ ሠራተኞች ክርክር ከማድረግ ይልቅ ዝምታን በመምረጥ ደስተኛ አለመሆናቸውን ያሳዩበት መድረክ እንደነበር መምህር ሥዩም ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የማዳበሪያ አቅርቦትና ውጣ ውረዱ

በቅፅል ስሙ “The Father of Chemical Warfare” እየተባለ የሚጠራው...

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትርፍ ምጣኔውን ከ70 በመቶ በላይ አሳደገ

ከሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ...