Sunday, June 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበእነ አቶ መላኩ ፈንታ መዝገብ ላይ ለሦስተኛ ጊዜ የመቃወሚያ ማሻሻያ ጥያቄ ቀረበ

በእነ አቶ መላኩ ፈንታ መዝገብ ላይ ለሦስተኛ ጊዜ የመቃወሚያ ማሻሻያ ጥያቄ ቀረበ

ቀን:

–  የዋስትና መብት ጠያቂዎች ጥያቄው ሕገወጥ ነው ብለዋል

የተጠረጠሩበት ከባድ የሙስና ወንጀል ውድቅ በተደረገላቸው በእነ አቶ መላኩ ፈንታ የክስ መዝገብ ቁጥር 141352 ውስጥ የተካተቱ ተከሳሾች ዋስትና ላይ፣ ዓቃቤ ሕግ ለሦስተኛ ጊዜ የዋስትና መቃወሚያውን አሻሽሎ እንዲያቀርብ ለፍርድ ቤት ጥያቄ አቀረበ፡፡

‹‹የዋስትና መቃወሚያ አስተያየታችንን ለማሻሻል የቀረበ አቤቱታ›› በማለት የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ለሦስተኛ ጊዜ ያቀረበው ጥያቄ፣ በተከሰሱበት ከባድ የሙስና ወንጀል ነፃ በተባሉት የኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ባለቤት አቶ ስማቸው ከበደና የተከሰሱበት ወንጀል ዋስትና እንደማይከለክል ገልጸው አቤቱታ በማቅረብ የዋስትና መብት እንዲጠበቅላቸው የጠየቁት የአቶ ገብረዋህድ ወልደ ጊዮርጊስ ባለቤት ኮሎኔል ሃይማኖት ተስፋዬ ላይ ነው፡፡

የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ለሦስተኛ ጊዜ የዋስትና መቃወሚያ ማመልከቻውን እንዲያሻሽል የጠየቀ ቢሆንም፣ ‹‹ሕገ መንግሥታዊ መብታችን ከመሆኑም በላይ ኮሚሽኑ በሌለው ሥልጣን ከሕግ ውጪ ሊያስከለክለን ወይም ተቃውሞ ሊያቀርብብን አይችልም፤›› በማለት ተከሳሾቹ ተቃውሞ አቅርበዋል፡፡

የኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ባለቤት አቶ ስማቸው ከበደ መስከረም 2 ቀን 2009 ዓ.ም. ክሳቸውን እያየው ለሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ባቀረቡት የመቃወሚያ አቤቱታ እንዳስረዱት፣ ቀርቦባቸው የነበረው የሙስና ወንጀል ክስ ቀሪ ሆኗል፡፡ በሒደት ላይ ያሉት ክሶች በቀጥታ ከገቢዎችና ጉምሩክ ጋር እንደሚገናኙና ክሶቹም ዋስትና እንደማያስከለክሉ፣ ዋስትና ደግሞ ሕገ መንግሥታዊ መብት በመሆኑ ያለበቂ ምክንያት ሊሸረሽርና ሊገደብ እንደማይችል በሕገ መንግሥቱ መሥፈሩን አስረድተዋል፡፡

የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ በአዋጅ ቁጥር 943/2008 ለኮሚሽኑ የተሰጠው የመክሰስ ሥልጣን ለፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ መሰጠቱን አስታውሷል፡፡ በወቅቱ በሽግግርና በርክክብ ላይ ሆኖ እያለ ያቀረበው የዋስትና መቃወሚያ ጉዳዩን በጥልቀት ሳይመለከትና ዋስትና የተከለከለባቸውን አስገዳጅ የሰበር ውሳኔዎችንና ሕጋዊ ምክንያቶችን ባለመጥቀሱ፣ ማሻሻያው እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡ ቀደም ብሎ ካቀረበው የዋስትና መቃወሚያ አንፃር ውሳኔ ቢሰጥ፣ ሊተካ የማይችል የፍትሕ መጓደል ሊያስከትል ይችላል የሚል እምነት እንዳለውም ዓቃቤ ሕግ በማመልከቻው ጠቅሷል፡፡

አቶ ስማቸው የከሳሽ ዓቃቤ ሕግን ‹‹መቃወሚያዬን ላሻሽል›› ጥያቄን በሚመለከት ለፍርድ ቤቱ ባቀረቡት አስተያየት እንደገለጹት፣ በዋስትና የመለቀቅ አቤቱታ ለፍርድ ቤት ሲቀርብ ማመልከቻው ወይም አቤቱታው ሳይዘገይ ታይቶ በ48 ሰዓታት ውስጥ ውሳኔ መሰጠት እንዳለበት፣ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 66 ላይ ተደንግጓል፡፡ ዓቃቤ ሕግ እሳቸው ባቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ላይ በቂ ጊዜ ተሰጥቶት አለኝ የሚለውን መቃወሚያ በጽሑፍ አቅርቦ፣ እሳቸውም መልስ መስጠታቸውን አስታውሰዋል፡፡

በመሆኑም የዓቃቤ ሕግ ‹‹መቃወሚያዬን ላሻሽል›› ጥያቄ ከሕግ ውጪና አሳማኝ ባለመሆኑ ተቀባይነት እንደሌለው ገልጸዋል፡፡

ኮሚሽኑ የሙስና ክስ ባልሆኑ ሊከራከርባቸውና አስተያየት እንዲሰጥባቸው የሥረ ነገር ሥልጣን ሳይኖረው፣ ጥያቄ ማቅረቡም ተገቢ አለመሆኑን አቶ ስማቸው አስረድተዋል፡፡ ለፍርድ ቤቱ በቀረበ የዋስትና ጥያቄ ላይ መቃወሚያና አስተያየት ተሰጥቶ ብይን ለመስማት በቀጠሮ ላይ ባለ መዝገብ፣ ዓቃቤ ሕግ መቃወሚያውን አሻሽሎ እንዲያቀርብ የሚፈቅድለት የሕግ ድንጋጌ እንደሌለ ጠቁመዋል፡፡ በ48 ሰዓታት ውስጥ ውሳኔ ማግኘት የነበረበት ሕገ መንግሥታዊ የመብት ጥያቄ ከአንድ ወር በላይ መቆየቱን ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ የዓቃቤ ሕግን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ዋስትና ተፈቅዶላቸው በውጭ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ማሻሻል ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ የሚቀሰቀስበት...

 መፍትሔ  ያላዘለው  የጎዳና  መደብሮችን  ማፍረስ

በአበበ ፍቅር ያለፉት ስድስት ዓመታት በርካቶች በግጭቶችና በመፈናቀሎች በከፍተኛ ሁኔታ...

የተናደው ከቀደምቱ አንዱ የነበረው የአዲስ አበባ ታሪካዊ ሕንፃ

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ መናገሻ ከተማቸውን...

የአከርካሪ አጥንት ሕክምናን ከፍ ያደረገው ‘ካይሮፕራክቲክ’

በአፍሪካ ከጀርባ ሕመም ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ለከፍተኛ የአካል...