Wednesday, December 7, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትነት 22 ዕጩዎች ቀረቡ

  ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትነት 22 ዕጩዎች ቀረቡ

  ቀን:

  • ከዕጩዎቹ መካከል የጠቅላይ ሚኒስትሩ ታናሽ ወንድም ይገኙበታል

  ለአንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትነት 22 ዕጩዎች ቀረቡ፡፡ የዩኒቨርሲቲው የሕዝብ ግንኙነት ጽሕፈት ቤት በማኅበራዊ ሚዲያ ድረ ገጹ እንዳስታወቀው፣ ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ 22 ምሁራን ዩኒቨርሲቲውን በፕሬዚዳንትነት ለማገልግል በወጣው ማስታወቂያ መሠረት ማመልከቻቸውን አስገብተዋል፡፡

  ከእነዚህ አመልካቾች ውስጥ የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የወቅቱ ፕሬዚዳንትና የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ታናሽ ወንድም የ49 ዓመቱ ፕሮፌሰር ፍቅሬ ደሳለኝ ይገኙበታል፡፡ ፕሮፌሰር ፍቅሬ ከአንድ ዓመት በፊት የሲቪል ሰርቪስ ፕሬዚዳንት በመሆን ተሹመው አሁንም እየሠሩ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

  አሁን እንደ አዲስ የተጀመረው የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶችን አወዳድሮ የመምረጥ ሥርዓት ከዚህ ቀደም ከነበረው አሠራር የተለየ ነው፡፡

  ከዚህ በፊት የዩኒቨርሲቲ ቦርድ በሥራ ላይ ባለው የከፍተኛ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 650/2001 መሠረት አወዳድሮ ከሚያቀርባቸው ዕጩዎች መካከል፣ እንደ አግባቡ በትምህርት ሚኒስትሩ ወይም በሚመለከተው የክልል ፕሬዚዳንቱ ይሾሙ ነበር፡፡ ከዚህ ዓመት ጀምሮ ግን ይኼ አሠራር ተቀይሯል፡፡ በትምህርት ሚኒስቴር በወጣው አዲስ መመርያ መሠረት ማንኛውም ለቦታው እመጥናለሁ የሚል ተወዳዳሪ፣ በዩኒቨርሲቲው በሚወጣው ክፍት የሥራ ማስታወቂያ መወዳደር ይችላል፡፡

  ይኼ አዲስ አሠራር ከተዋወቀ በኋላ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከወራት በፊት አዲስ ፕሬዚዳንት መሾሙ ይታወሳል፡፡ 60 ዓመታት ያስቆጠረው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም በአዲሱ አሠራር መሠረት ፕሬዚዳንቱን በመሾም ሁለተኛ ይሆናል፡፡

  በ1950 የተመሠረተው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ ቀደም አሥር ፕሬዚዳንቶች የመሩት ሲሆን፣ ከ2003 ዓ.ም. እስከ 2010 ዓ.ም. ድረስ  አድማሱ ፀጋዬ (ዶ/ር) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት እንደነበሩ ይታወሳል፡፡

  ከአሁኑ የፕሬዚዳንት አሰያየም ጋር በተያያዘ ለ16 ቀናት እስከ ታኅሳስ 9 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አመልካቾችን ሲቀበል ነበር፡፡ ካመለከቱት 22 ተወዳዳሪዎች ውስጥም 12 የሚሆኑት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ እየሠሩ ያሉ ምሁራን ናቸው፡፡ ቀሪዎቹ ከሌሎች ተቋማት፣ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ውጭ በሚገኙ የትምህርት ተቋማት የሚሠሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የውጭ ዜጎች እንደሚገኙበት ማወቅ ተችሏል፡፡

   

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመው ጭፍጨፋና ሥጋቱ

  ኦሮሚያ ክልል ከቀውስ አዙሪት መላቀቅ ያቃተው ይመስላል፡፡ ከ200 በላይ...

  እናት ባንክ ካፒታሉን ወደ አምስት ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ወሰነ

  መጠባበቂያን ሳይጨምር የባንኩ የተጣራ ትረፍ 182 ሚሊዮን ብር ሆኗል እናት...

  ቡና ባንክ ዓመታዊ ትርፉን ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ማሻገር ቻለ

  ቡና ባንክ በ2014 የሒሳብ ዓመት ዓመታዊ የትርፍ ምጣኔውን ለመጀመርያ...