Friday, October 7, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፖርትየኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለተኛውን የሩጫ ውድድር በመቐለ  አካሄደ

  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለተኛውን የሩጫ ውድድር በመቐለ  አካሄደ

  ቀን:

  በባንክ ኢንዱስትሪው በቀዳሚነቱ የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዩቤልዩ ክብረ በዓሉን በማስመልክት በተለያዩ ከተሞች እያከናወነ በሚገኘው የሩጫ ውድድር በማክበር ላይ ይገኛል፡፡

  ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የባንኩን 75ኛ ዓመት ክብረ በዓል አስመልክቶ እየተካሄደ የሚገኘው የሩጫ ውድድር፣ እሑድ ታኅሣሥ 8 ቀን 2010 ዓ.ም. የመጀመርያውን ዝግጅት በሐዋሳ ከተማ ማከናወኑ ይታወሳል፡፡ ሁለተኛውን ደግሞ ባለፈው እሑድ ታኅሣሥ 15 ቀን በመለ ከተማ አድርጓል፡፡

  በክልሉ የሚገኙ የአትሌቲክስ ክለብ ተወዳዳሪዎችን ባካተተው ውድድር የባንኩን ማኅበረሰብ ጨምሮ ከ3,000 በላይ ተሳታፊዎች የተካፈሉበት ነበር፡፡ ‹‹ባንኬ ኩራቴ›› በሚል መሪ ቃል የሐዋሳና የመለውን ጨምሮ በአምስት የክልል ከተሞች በባሕር ዳር፣ በአዳማና በአዲስ አበባ ጥር 6፣ የካቲት 18 እና መጋቢት 23 ቀን እንደሚያከናውን የዝግጅት ክፍሉ አስተባባሪ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አስታውቋል፡፡

  7.5 ኪሎ ሜትር በሚሸፍነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 75ኛ ዓመት ክብረ በዓል የሩጫ ውድድር፣ በሴቶች ፎቴን ተስፋዬ 25፡04.45 ከመሰቦ ሲሚንቶ፣ ሳራ ግርማይ 25፡15.17 ከመስፍን ኢንደስትሪያል ኢንጂነሪንግና ለምለም ግርማይ 25፡17.43 ከመሰቦ ሲሚንቶ ሲሆኑ፤ በወንዶች ሞገስ ፅኡማይ 22፡04.86 ከመሰቦ ሲሚንቶ፣ መብራቱ ገብረ እግዚአብሔር 22፡12.23 እና ገብሩ ንጉሤ 22፡17.20 ሁለቱም ከትራንስ ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እንደ አዘጋጁ ከሆነ፣ ለክልል ከተሞች አሸናፊዎች ከ10,000 ብር ጀምሮ በየደረጃው እስከ አሥረኛ ለሚወጡ ተወዳዳሪዎች የገንዘብ ሽልማት ይበረከትላቸዋል፡፡ በተጨማሪም የሆቴል ቆይታ የሚኖራቸው አራት የአገር ውስጥ ነፃ የበረራ ትኬት እንደሚኖርም ተገልጿል፡፡

   

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img