Friday, December 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየአትሌቲክሱ አዲሱ ጅምር

የአትሌቲክሱ አዲሱ ጅምር

ቀን:

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቀስ በቀስ እያሽቆለቆለ የውጤት ቀውስ ውስጥ ለመግባት እየተንደረደረ መሆኑ ሲያነጋግር ቆይቷል፡፡ እንደ ቀድሞው ውጤታማና ብቃትን የተላበሱ አትሌቶች፣ ክብረ ወሰኖችን እየሰባበሩ ኢትዮጵያን አልፈው ዓለምን የሚስማሙባቸው መድረኮች እየተቀዛቀዙ፣ በምትኩ የውድድር አድማቂ በመሆን የቀድሞ ተፈሪነታቸውና አነጋጋሪነታቸው እየተዳከመ የመምጣቱ ምክንያት ውስብስብ እየሆነ በየጊዜው ሲገለጽ ቆይቷል፡፡

የአትሌቲክሱ የውጤት ቀውስ የቀድሞዎቹን የአትሌቲክስ አመራሮች በዘርፉ ያላቸውን የአቅም ውስንነት ግምት ውስጥ በማስገባት በሒደት በሙያው ሰዎች እንዲተኩ ያስገደደበት አጋጣሚም መፍጠሩ አይዘነጋም፡፡ ይህም ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በቀደምቶቹ በእነ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ፣ ደራርቱ ቱሉና ገብረ እግዚአብሔር ገብረ ማርያም የሚመራው አዲስ አመራር እንዲተካ ተደርጎ በዚሁ አመራርም አዳዲስ የተግባር ጅምሮ መታየት ጀምሯል፡፡

ፌዴሬሽኑ ከሰሞኑ ይፋ ካደረጋቸው አሠራሮች መካከል በአገሪቱ በሁሉም ክልሎች በሙያተኞች የተደገፈ የመስክ ጉብኝትና ግምገማ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የመስክ ጉብኝቱንና ግምገማ ከመደረጉ አስቀድሞ ከአሠልጣኞች ምደባ፣ ዝግጅት ምልመላና ሥልጠናን አስመልክቶ እንደ ቀድሞው ሊቀጥል እንደማይችል በመግለጽ በተለይም የብሔራዊ ቡድን ዝግጅት ክልሎችን ባማከለ አቅምና ብቃት ላይ ተመሥርቶ እንዲቀጥል መወሰኑ አይዘነጋም፡፡

በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በአማራና በትግራይ የሚገኙትን የአትሌቲክስ ማሠልጠኛ ማዕከላትን ጨምሮ በሁሉም ክልሎች ያለውን ተሰጥኦና ክህሎት መነሻ በማድረግ በወራት የሚቆጠር የመስክ ግምገማ እያከናወነ መሆኑ ያስታወቀው ፌዴሬሽኑ፣ የክልሎችን ግብረ መልስ በመንተራስ የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ ስትራቴጂካዊ ዕቅዶችን ይፋ እንደሚያደርግ የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዚዳንት ገብረ እግዚአብሔር ገብረ ማርያም ያስረዳል፡፡

እንደ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ከሆነ፣ ሁሉንም ክልሎች ባማከለው በዚህ የመስክ ጉብኝትና ግምገማ፣ በአገር አቀፍ ደረጃ ተተኪና ውጤታማ አትሌቶችን በማፍራቱ ረገድ ጉልህ ድርሻ እንዳለው ያምናል፡፡ የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ በዘጠኙም ክልሎች ፌዴሬሽኑ ያሰማራቸው ሙያተኞች እስከታች ወረዳና ቀበሌ በመውረድ ትክክለኛ ጥናት በማድረግ ላይ ስለመሆናቸው ጭምር ያስረዳል፡፡

የፌዴሬሽኑን ፕሬዚዳንት ኃይሌ ገብረ ሥላሴን ጨምሮ አመራሩ በሁሉም ክልሎች በመዟዟር ከክልል ከፍተኛ አመራሮች ጀምሮ ከመስክ ምልከታው የተገኘውን ግብረ መልስ መነሻ በማድረግ ውይይት በማድረግ ላይ እንደሚገኝም ተናግሯል፡፡ ወደ ጋምቤላና ትግራይ ክልሎች በማምራት ተጨባጭ ለውጥ በሚያመጡ ጉዳዮች መግባባት ላይ ስለመደረሱ የብሔራዊ ፌዴሬሽኑና የክልሎች ድርሻ ክለቦችን ጨምሮ ምን መምሰል እንዳለበት፣ በዚያው ልክ ተጠያቂነትና ግልጽነትን ያካተተ መሆን እንደሚገባው የውይይቱ አካል ስለመደረጉም ገልጸዋል፡፡

እንቅስቃሴውን አስመልክቶ ፌዴሬሽኑ በድረ ገጹ እንዳስታወቀው፣ እየተከናወነ ባለው የመስክ ጉብኝትና ግምገማ፣ አትሌቲክሱ አሁን ከሚገኝበት ደረጃ በተሻለና አስተማማኝ መሠረት ይዞ ይቀጠል ዘንድ በተለይ ክልሎች ከሪፖርት ያለፈ ሊታይ የሚችል ስትራቴካዊ ዕቅድ ነድፈው መንቀሳቀስ እንደሚጠበቅባቸው ጭምር በውይይቱ መካተቱን ገልጿል፡፡

በዚሁ መነሻነት ክልሎች ካነሷቸው ጥያቄዎች መካከል የማዘውተሪያ ሥፍራ፣ የአትሌቶችና አሠልጣኞች ምልመላና ምርጫ አቅምና ብቃት ላይ ሊመሠረት እንደሚገባው፣ በዋናነትም የአትሌቲክሱን ውጤት በቅብብሎሽ አስጠብቆ ለማስቀጠል ከአትሌቶች ዕድሜ ጋር የተያያዙ የመረጃ አያያዝና በተለይም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከውጭ ጉዞ ጋር ተያይዞ የሚነሱ እሰጣ ገባዎች እስከወዲያኛው ሊያስወግድ የሚችል የአሠራር ሥርዓት ጉዳይ በዝርዝር መታየቱም ተነግሯል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...