Tuesday, April 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊባልና ሚስቱ የኮርያ ዘማቾች ለሙዚየም ስጦታ አበረከቱ

ባልና ሚስቱ የኮርያ ዘማቾች ለሙዚየም ስጦታ አበረከቱ

ቀን:

ከዛሬ 60 ዓመት በፊት በኮርያ ልሳነ ምድር ዘምተው ዓለም አቀፍ ግዳጃቸውን የተወጡ ባልና ሚስት ይገለገሉባቸው የነበሩ ልዩ ልዩ ዕቃዎችን ለኮርያ ዘማቾች ማኅበር ሙዚየም ታኅሣሥ 17 ቀን 2010 ዓ.ም. በስጦታ አበረከቱ፡፡

ስጦታውን ያበረከቱትም የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ለመጀመርያ ጊዜ በነርስነት ሙያ አሠልጥኖ ካስመረቃቸው መካከል አንዷ የሆኑትና በኮርያ ልሳነ ምድር ዓለም አቀፍ ግዳጃቸውን የተወጡ መቶ አለቃ ሲስተር ብርቅነሽ ከበደ፣ እንዲሁም በኮሪያና በኮንጎ የጦር ቀጣናዎች አኩሪ ግዳጃቸውን የተወጡ፣ በአገር ውስጥ ደግሞ በውትድርና መስክና በልዩ ልዩ የመንግሥት መዋቅር በአስተዳደርነት አገልግለው አሁን በጡረታ ላይ የሚገኙ ባለቤታቸው ብርጋዴር ጄኔራል ደስታ ገመዳ ናቸው፡፡

መቶ አለቃ ብርቅነሽ ለሙዚየሙ ያበረከቱት በስተግራ በኩል የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ዓርማ ያለበት የነርስ ካባቸውን ሲሆን፣ ብርጋዴር ጄኔራል ደስታ የሰጡት ደግሞ በኢትዮጵያ የመጀመርያ የሆነው የክብር ዘበኛ ጦር አካዴሚ አንደኛ ኮርስ አባላት በወታደራዊና በሲቪል መስኮች በአገር ውስጥ፣ በኮርያ ልሳነ ምድርና በኮንጎ የግዳጅ አፈጻጸም ላይ የተወጡትን የጀግንነት ውሎ የሚያወሱ ልዩ ልዩ መጻሕፍት ናቸው፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ከተበረከቱት መጻሕፍት መካከል፣ ‹‹የ1928 ዓ.ም. ኢትዮጵያ በኢጣሊያ መወረር›› እና ‹‹የ1953ቱ የመንግሥት ግልበጣ ሙከራ ከ1958 እስከ 1966 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ታሪካዊ ሒደት››፣ ‹‹የኢትዮጵያውያን የረዥም ዘመናት ትግል የዘመናዊ ሠራዊት አመሠራረት ከ1855 እስከ 1974›› የሚሉ ይገኙባቸዋል፡፡

ከዚህም ሌላ፣ ያሳለፍኩት የትግል ዘመን፣ የትግል ፍፃሜ፣ አባቴ ያቺን ሰዓት እና መልካም ይዘት በሚሉ ርዕሶች የተዘጋጁ መጻሕፍትም ለሙዚየሙ ተሰጥተዋል፡፡

እንዲሁም የክብር ዘበኛ ጦር አካዳሚ አንደኛ ኮርስ ተመራቂዎች፣ የትምህርት ቤቱ አዛዥ ስዊድናዊ ሜጄር ጄኔራል ታጊ አለን፣ የጄኔራል መንግሥቱ ንዋይና የጄኔራል ሙሉጌታ ቡሊ ፎቶግራፎች የተካተቱበት ሰሌዳም ለሙዚየሙ ተበርክቷል፡፡

በአገር ውስጥ በነርስነት ሙያ በቀደምትነት ከሠለጠኑት የመጀመርያ ምሩቃን መካከል የመቶ አለቃ ብርቅነሽ ከበደ በኮርያ፣ ሻምበል አስቴር አያና ሊካሳ በኮርያና በኮንጎ የጦር ቀጣናዎች የፈጸሙትን ተጋድሎ የሚዘክር የኢትዮጵያ ጥናት መጽሔት ለመቶ አለቃ ብርቅነሽ ተበርክቷል፡፡

ሁለቱም ነርሶች በዓለም አቀፍ ደረጃ የተጫወቱትን አኩሪ ተግባር በመጽሔቱ ላይ በፈረንሣይኛና በእንግሊዝኛ ያሰፈሩት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ የጥናትና ምርምር ተቋም ዳይሬክተር አህመድ ሁሴን (ዶ/ር) ናቸው፡፡

ሻምበል አስቴር አያና ሊካሳ በ1987 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ቢለዩም እናት ባንክ አቃቂ ቃሊቲ የሚገኘውን ቅርንጫፍ ለመታሰቢያነት በስማቸው ሰይሟል፡፡ መቶ አለቃ ብርቅነሽ ከበደ ግን ከባለቤታቸው ብርጋዴር ጄኔራል ደስታ ገመዳ ጋር በትዳር እስካሁን አብረው ያሉ ልጆችና የልጅ ልጅ ያዩ ናቸው፡፡  

የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ኮሎኔል መለስ ተሰማ ስጦታውን ከተረከቡ በኋላ እነዚህ ታሪክ ቀመስ መጻሕፍት ወደፊት ለሚቋቋመው ቤተ መጻሕፍት ከፍተኛ ዕገዛ እንደሚያደርጉ ገልጸው፣ በሙዚየሙ በጥንቃቄ እንደሚቀመጡ አስረድተዋል፡፡

ፋሺስት ጣሊያን የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም. በርካታ ኢትዮጵያውያን የፈጀበትን ቀን በመጀመርያ እንዲከበር ያደረጉት የክብር ዘበኛ ጦር አካዴሚ አንደኛ ኮርስ መኰንኖች መሆናቸውን ጠቁመው በክንዳቸው ላይ በተለጠፈው የክብር ዘበኛ ዓርማ ሥር ‹‹ሠልፍ የጀግና ድል የእግዚአብሔር ነው›› የሚል ጥቅስ እንደነበረበት ተናግረዋል፡፡

መቶ አለቃ ብርቅነሽ ከርክክቡ ሥነ ሥርዓት በኋላ የተሰማቸውን እንዲገልጹልን ጠይቀን፣ ‹‹ከእኛ በፊት በነርስነት የሠለጠኑት ልዕልት ፀሐይ ኃይለ ሥላሴ ናቸው፡፡ የሠለጠኑትም በእንግሊዝ አገር ነው፡፡ በአገር ውስጥ ግን የመጀመርያዎቹ  ሠልጣኞችም እኔን ጨምሮ ዘጠኝ ነበርን፡፡ እኔና ሌሎች ሁለት በሕይወት እስካሁን አለን፡፡ ሁለቱ ነዋሪነታቸው ውጭ አገር ነው፤›› ብለዋል፡፡

በነርስነት በተመረቁበት ሥነ ሥርዓት ላይ የለበሱትንና በማንኛውም ጊዜ ስብሰባ ሲኖርና የሕዝብ በዓላት ቀን የሚለብሱትን ካባ በሙዚየም እንዲቀመጥ ማድረጋቸው፣ እንዲሁም ስለእሳቸውና ጓደኛቸው ሻምበል አስቴር አያና ሊካሳ የሚተረከውን መጽሔት ማግኘታቸው እጅግ አድርጎ እንዳስደሰታቸው ሳይናገሩ አላለፉም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰው መሆን ምንድን ነው? ቅርስና ማኅበራዊ ፍትሕ

በሱራፌል ወንድሙ (ዶ/ር) ዳራ ከጎራዎች፣ ከመፈራረጅ፣ ነገሮችን ከማቅለልና ከጊዜያዊ ማለባበስ ወጥተን...

ኢኮኖሚው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሳት ያሠጋል

በጌታቸው አስፋው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሱ የሚያሠጉኝ አንድ ሁለት ብዬ ልቆጥራቸው የምችላቸው...

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል በሕግ አምላክ ይላል

በገነት ዓለሙ የአገራችንን ሰላም፣ የመላውን ዓለም ሰላም ጭምር የሚፈታተነውና አደጋ...

በሽግግር ፍትሕ እንዲታዩ የታሰቡ የወንጀል ጉዳዮች በልዩ ፍርድ ቤት ሳይሆን በልዩ ችሎት እንዲታዩ ተወሰነ

የኤርትራ ወታደሮች በሌሉበትም ቢሆን ይዳኛሉ ተብሏል በፅዮን ታደሰ የሽግግር ፍትሕ የባለሙያዎች...