Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናኢዴፓን ጨምሮ 16 ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት መሠረቱ

ኢዴፓን ጨምሮ 16 ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት መሠረቱ

ቀን:

በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተፈጠረውን የፖለቲካ ችግርና የፖለቲካ ምኅዳር መጥበብ ያስከተላቸው ክልላዊና አገራዊ ግጭቶችን መሠረት በማድረግ አሳሳቢ የሆነውን ወቅታዊ የፖለቲካ ችግር መፍታትና የብሔራዊ ዕርቅ አጀንዳ ይዞ መቅረብ ጊዜ አይሰጠውም ያሉ፣ 16 አገር አቀፍና ክልላዊ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ‘ጥምረት ለብሔራዊ መግባባትና አንድነት’ የተሰኘ ጥምረት መመሥረታቸውን አስታወቁ፡፡

ፓርቲዎቹ ጥመረት መመሥረታቸውን ይፋ ያደረጉት፣ ሐሙስ ጳጉሜን 3 ቀን 2008 ዓ.ም. ለአገር ውስጥና ለውጭ አገር ጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ነው፡፡

‹‹ኢትዮጵያ ካለፈችበት ረዥም የታሪክ ሒደት በርካታ የሚያኮሩ ገጽታዎች ያሉዋት አገር እንደመሆኗ ሁሉ፣ በዚያው መጠን ዛሬ ዓለም ከደረሰበት ቁሳዊም ሆነ ሥነ ልቡናዊ የዕድገት ደረጃ አንፃር ስትመዘን የሚያሳዝንና የሚያስቆጭ ደረጃ ላይ ከመገኘቱም በላይ፣ ከዓለም የዕድገትና የማኅበረሰብ ኑሮ ደረጃ ስትመዘን ከመጨረሻዎቹ ደሃ አገሮች ትመደባለች፤›› በማለት የጥምረቱ መግለጫ ያትታል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ከዚህ ዓይነቱ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና የማኅበራዊ ቀውስ ለመውጣትና የተረጋጋ ማኅበረሰብ ለመፍጠር የሚያስችል አስተማማኝ የፖለቲካ ሥርዓት መገንባት አልቻልንም የሚለው ጥምረቱ፣ ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገዥውን ጨምሮ ብሔራዊ መግባባት ያልፈጠሩና ሁሌም በጠላትነት ስሜትና መንፈስ የሚፈራረጁና ለመጠፋፋት የሚፈላለጉ ናቸው፤›› ሲሉም ሁሉም አካላት ብሔራዊ እርቅ ላይ እንዲያተኩሩ ያሳስባል፡፡

አሁን በአገሪቱ የተፈጠሩት ችግሮች መንስዔ በሕገ መንግሥቱ የሠፈሩት መብቶች አለመከበር እንደሆነ እንደሚያምንም ጥምረቱ አስታውቋል፡፡

‹‹በሕገ መንግሥቱ የተደነገጉትን ድንጋጌዎችና በዓለም አቀፍ ኅብረተሰብ ዘንድ ተቀባይነት ያገኙት የግለሰብ ነፃነቶችና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ማረጋገጫ መርሆዎች በተግባር ሲታዩ፣ ሕዝብን ያልጠቀሙ የሕግ አተገባበሮች ዋነኛ የችግር ምንጮች ናቸው፤›› በማለት ጥምረቱ በመግለጫው ገልጿል፡፡

‹‹ባልተስተካከለ የፖለቲካ ሒደት ያጣነውን ብሔራዊ አንድነት መልሰን ለማምጣት አሁን ካለንበት የመጠላለፍና የመወነጃጀል አዙሪት ወጥተን በመከባበርና በመደማመጥ የሕግ የበላይነትን በማስፈን፣ በሰላምና ብሔራዊ ዕርቅ እንዲመሠረት ጥረት እናደርጋለን፤›› በማለት አትቷል፡፡

በብሔራዊ እርቅ እንቅስቃሴ የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱና በብሔራዊ እርቅ መድረኩ እንዲሳተፉ ጥያቄም አቅርቧል፡፡

በተጨማሪም በብሔራዊ የእርቅ መድረኩ ላይ የተለያዩ አገሮች መንግሥታት፣ ታዋቂ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችና የዲፕሎማቲክ ተቋማት ተወካዮች የታዛቢነት ድርሻ እንዲኖራቸው ጥምረቱ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

ጥምረቱ 16 የተቃዋሚ ፓርቲዎች ተወካዮች በተገኙበት የተመሠረተ ሲሆን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ማንነት እንዲገለጽ ሪፖርተር ቢጠይቀም፣ ‹‹የፓርቲዎቹን ማንነት አሁን መግለጽ አስፈላጊ ነው ብለን አናምንም፤›› በማለት የኢዴፓ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጫኔ ከበደ ተናግረዋል፡፡

ከ16ቱ ፓርቲዎች ተወካዮች መካከል ግን ኢራፓን ወክለው አቶ ተሻለ ሰብሮ፣ አንድነትን ወክለው አቶ ትግስቱ አወሉ ተገኝተው ነበር፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...