Monday, May 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊበተጠናቀቀው ዓመት በተሽከርካሪ አደጋ ከ4,300 በላይ ሰዎች ሞተዋል

በተጠናቀቀው ዓመት በተሽከርካሪ አደጋ ከ4,300 በላይ ሰዎች ሞተዋል

ቀን:

2008 ዓ.ም. በርከት ያሉ አስደንጋጭ ክስተቶችን ያስተናገደ ዓመት ሆኖ ሲጠናቀቅ፣ 4,352 ሰዎች ሕይወታቸው ያለፈበት የተሽከርካሪ አደጋ ቀዳሚውን ሥፍራ ይዟል፡፡

በ2008 ዓ.ም. አገሪቱን ክፉኛ ፈትነዋትና ከበድ ያሉ ጫናዎችን አሳርፈውባት ያለፉ በርከት ያሉ ክስተቶች የተስተዋሉ ሲሆን፣ ከ10 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጐችን ለአስቸኳይ ዕርዳታ የዳረገው ድርቅ ተጠቃሽ ነው፡፡ እንዲሁም በተወሰኑ ሥፍራዎች የተከሰተው የመሬት መንሸራተት፣ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች የፈነዱ ሕዝባዊ ተቃውሞዎች፣ በጎንደር፣ በደብረ ታቦርና በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤቶች የተነሱ የእሳት አደጋዎች፣ የአተት በሽታና የመሳሰሉት ዋና ዋናዎቹ በመሆን ይጠቀሳሉ፡፡ ነገር ግን የዜጐችን ሕይወት በመቅጠፍ፣ አካል ጉዳተኛ በማድረግና ከፍተኛ ግምት ያለው ንብረትን በማውደም የተሽከርካሪ አደጋ ጥሎት ያለፈው ጉዳት አገሪቱን ከፈተኑት አደጋዎች ውስጥ በቀዳሚዎቹ ተርታ ሲመደብ፣ በተቃውሞዎቹ የደረሰው የሕይወት መቀጠፍ፣ የአካል ጉዳትና ንብረት ውድመትም በከፍተኛ ደረጃ ተመዝግቧል፡፡

ከፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን በተገኘ መረጃ መሠረት ከመስከረም 1 እስከ ጳጉሜን 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ ከ4,000 በላይ የተሽከርካሪ አደጋዎች ተመዝግበዋል፡፡ በእነዚህም አደጋዎች 4,352 የሞት አደጋ ሲመዘገብ፣ 13,957 የሚሆኑ ሰዎችን ለአካል ጉዳተኝነት ማጋለጡ ተረጋግጧል፡፡ በንብረት ረገድም ከ887.3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን የንብረት ጉዳት ተመዝግቦበት ዓመቱ ተጠናቋል፡፡ በዓመቱም የተከሰተው አደጋ ከቀዳሚው ዓመት (ከ2007 ዓ.ም.) የሞት ቁጥሩ በ501 አብላጫ ሲኖረው፣ በአካል ጉዳት ያስከተለው ከ2,000 በላይ፣ እንዲሁም 200 ሚሊዮን ብር የሚገመት ተጨማሪ የንብረት ጉዳት ተመዝግቦበታል፡፡

- Advertisement -

ምንም እንኳ የተሽከርካሪ አደጋን ለመቀነስ በዓመቱ ከሚሠሩ ዕቅዶች አንዱ ሆኖ በመንግሥት ተለይቶ የነበረ ቢሆንም፣ ዕቅዱን አለማሳካት ብቻ ሳይሆን ትልቁ የተሽከርካሪ አደጋ ተስተውሎበት አልፏል፡፡

የተሽከርካሪ አደጋው መባባስ ቅድሚያ ድርሻውን በመያዝ ከአሽከርካሪ ብቃት፣ ከመንገዶች ተስማሚነት፣ ከተሽከርካሪዎች ቴክኒክ ሁኔታና ከሌሎች ጉዳዮች ጋር የሚያያዙ ሁኔታዎች ይጠቀሳሉ፡፡ ሌላው ወደ ተግባር በማስገባት ተቃውሞ ገጥሞት እንዲዘገይ የተደረገው አወዛጋቢው የ2003 ዓ.ም. የትራፊክ ደኅንነት አዋጅ፣ በዓመቱ አደጋውን ለመቀነስ አለመግባቱ የአደጋ ቅነሳ ዕቅዱን እንዳይሳኩ ካደረጉት ምክንያቶች መካከል ትልቁን ድርሻ እንደሚወስድ የባለሥልጣኑ ኃላፊዎች ያስረዳሉ፡፡

በፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን የመንገድ ደኅንነት ዳይሬክተር አቶ ስሜ በላይ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በዓመቱ የተከሰተው አደጋና ያስከተላቸው ጉዳቶች በቁጥር ደረጃ ከፍ ብለው ቢታዩም በአደጋ መለኪያ መሥፈርቶች ከተሽከርካሪዎች ብዛት አንፃር መጠነኛ ቅናሽ አሳይቷል ብለዋል፡፡

‹‹ዓመታዊ አደጋውን ከቁጥር አንፃር ሲታይ ከፍ እያለ መምጣቱንና አስደንጋጭነቱን ያሳያል፡፡ ይህ ደግሞ ምን ያህል ጠንክረን ልንሠራ እንደሚያስፈልግ ያሳስባል፡፡ ነገር ግን የትራፊክን አደጋ ልንለካባቸው የምንችላቸው በዓለም አቀፍ የሚታወቁ ሁለት መሥፈርቶች አሉ፡፡ እነዚህም ከመቶ ሺሕ ሕዝብ ምን ያህል በተሽከርካሪ አደጋ ነው የሞተው? ከ10 ሺሕ ተሽከርካሪዎች ምን ያህል ሞት ተመዘገበ በሚሉ መንገዶች ይለካል፤›› ብለዋል፡፡ ነገር ግን አሁን ባለው ሥርዓት በኢትዮጵያ የሚተገበረው ሁለተኛው መንገድ መሆኑ የጠቀሱት አቶ ስሜ፣ ከዚህ አንፃር ሲታይ በ2008 ዓ.ም. ከ10 ሺሕ ተሽከርካሪዎች የደረሰው ሞት 62 መሆኑን፣ ከቀደመው ዓመት ሲነፃፀር አደጋው መቀነሱን ገልጸዋል፡፡ በ2007 ዓ.ም. በ10 ሺሕ ተሽከርካሪዎች የተመዘገበው ሞት 64 እንደነበር ገልጸዋል፡፡

ለአደጋው መጨመርም ሆነ መከሰት ዋና ዋና መንስዔዎች በርከት እንደሚሉ አስረድተው፣ በግምገማ በተለየው መሠረት ሰውኛ ችግሮች በሚባሉት ሥር የሚገኝ የአሽከርካሪ ብቃት፣ ባህሪና ሥነ ምግባር፣ ርቀትን ጠብቆ ካለማሽከርከር የሚመጡ ችግሮች በዋነኝነት ይጠቀሳሉ ብለዋል፡፡ ከተሽከርካሪ ብቃት ችግር፣ ከመንገዶች ተነባቢነት መጓደል፣ ከቁጥጥር ሥራ አጥጋቢ አለመሆን ጋር የሚገናኙ ተጨማሪ የአደጋ መንስዔዎችን አስረድተዋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...