Saturday, June 10, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በከባድ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስምንት የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች ተከሰሱ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

–  ከባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ድርጅት 5.8 ሚሊዮን ብር ተወሰደ

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፊንፊኔ ቅርንጫፍ ከከፈተው ሒሳብ ላይ 5,815,000 ብር ሐሰተኛ ሰነድ ላቀረቡ ግለሰቦች እንዲከፈላቸው በማድረግ የተጠረጠሩ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡራዩ፣ እንቁላል ፋብሪካና ፊንፊኔ ቅርንጫፎች ሥራ አስኪያጆችና የደንበኞች አገልግሎት መኮንን ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

ተከሳሾቹ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የእንቁላል ፋብሪካ ቅርንጫፍ የደንበኞች አገልግሎት ሥራ አስኪያጅ አቶ መካሻ ሰዒድ፣ የቅርንጫፉ ሥራ አስኪያጅ አቶ አበራ ይልማ፣ ከፍተኛ የቅርንጫፉ ተቆጣጣሪ ሥራ አስኪያጅ ወ/ት ቤዛዊት በላይ፣ የፊንፊኔ ቅርንጫፍ የደንበኞች አገልግሎት ሥራ አስኪያጆች አቶ ዳንኤል ኩምሳ፣ አቶ ሀብታሙ መንግሥቱ፣ አቶ ምትኩ ጭምዲ፣ አቶ ሰለሞን ጉርሙና ወ/ት ሰብለ ወንጌል የኋላሸት፣ የቡራዩ ቅርንጫፍ የደንበኞች አገልግሎት መኮንን አቶ ዳዊት ለማ፣ እንዲሁም አቶ ሰላም አበበና ሕይወት ብርሃኑ ንጉሤ መሆናቸውን ክሱ ይገልጻል፡፡

አቶ ሰላም አበበና ያልተያዙት ሕይወት ብርሃኑ ንጉሤ በተባሉት ተከሳሾች ከአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 የተሰጠ ሐሰተኛ የነዋሪነት መታወቂያ፣ ከንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ጽሕፈት ቤት የተሰጠ ሐሰተኛ የንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ እንዲሁም ሐሰተኛ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር አዘጋጅተው ወደተጠቀሱት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች መሄዳቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡

ግለሰቦቹ ከላይ የተጠቀሱትን ሐሰተኛ ሰነዶች ወደ ባንኮቹ ይዘው በመቅረብ ይማ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በተባለ ሐሰተኛ ድርጅት ስም ተንቀሳቃሽ ሒሳብ እንዲከፈትላቸው ሲያመለክቱ፣ የባንኩ ኃላፊዎች የቼክ ቁጥራቸው ከ980976 እስከ 9809100 የሆኑ ባለ 25 ቅጠል ቼኮችን እንዳስረከቧቸው የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ችሎት ያቀረበው ክስ ያስረዳል፡፡

ሁለቱ ግለሰቦች በተዘጋጀላቸው ቼክ ኅዳር 27 እና ታኅሳስ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የተጻፈ በማስመሰል፣ ከድርጅቱ ሒሳብ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፊንፊኔ ቅርንጫፍ 2,863,000 ብር እና ከተመሳሳይ ቅርንጫፍ 2,952,000 ብር በድምሩ 5,815,000 ብር ማውጣታቸውን ክሱ ያብራራል፡፡ ሁለቱ ተከሳሾች ያገኙትን ገንዘብ ተከፋፍለው ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡ ሐሰተኛ ሰነዶችን መንግሥታዊ ሰነዶች አስመስለው በማቅረብና በመገልገላቸው በከባድ የሙስና ወንጀል መከሰሳቸው በኮሚሽኑ ክስ ተገልጿል፡፡    

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች