Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናኦሮሚያ ከአዲስ አበባ ስለሚያገኘው ልዩ ጥቅም የሚደነገግ ሕግ ሊወጣ ነው

ኦሮሚያ ከአዲስ አበባ ስለሚያገኘው ልዩ ጥቅም የሚደነገግ ሕግ ሊወጣ ነው

ቀን:

ኢሕአዴግ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከአዲስ አበባ ከተማ ማግኘት ያለበት ልዩ ጥቅም በአዋጅ ተደንግጎ እንዲወጣ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ ሰሞኑን በተካሄደው የኢሕአዴግ ምክር ቤት 15 ዓመት የተሃድሶ ግምገማ በኦሮሚያ ክልል ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት ከተካሄደ በኋላ፣ ቀደም ሲል በተካሄዱ ጥናቶች ላይ ተመሥርቶ የክልሉን ልዩ ጥቅም የሚያስጠብቅ አዋጅ እንዲዘጋጅ ውሳኔ ተላልፏል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ሐሙስ ነሐሴ 26 ቀን 2008 ዓ.ም. ከተለያዩ የወጣት ፎረሞች ጋር ባካሄዱት ውይይት ላይ፣ የኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ ከተማ ማግኘት ስላለበት ልዩ ጥቅም በሕገ መንግሥቱ ተደንግጎ እያለ ተግባራዊ ያልተደረገበትን ምክንያት እንዲያብራሩ ከተሳታፊዎች ተጠይቀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕገ መንግሥቱን ማክበርና ማስከበር ወሳኝ ጉዳይ ነው ካሉ በኋላ፣ አዋጁን በማውጣት በኩል መንግሥት መዘግየቱን አምነዋል፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት አዋጅ እንዲወጣ በመወሰኑ፣ በአዲሱ ዓመት አዋጁ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚቀርብ በማረጋገጥ፣ ይፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡

‹‹መንግሥት የኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ ስለሚያገናኘው ልዩ ጥቅም በዝርዝር አጥንቷል፡፡ ጥያቄውም በአዋጅ የሚመለስ ይሆናል፤›› ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተሰብሳቢዎቹ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በተካሄደው ደም አፋሳሽ ግጭት የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የጋራ ማስተር ፕላን መነሻ ምክንያት መሆኑ ይታወሳል፡፡ ነገር ግን አንዳንድ የኦሮሚያ ልሂቃንና መንግሥት የጋራ ማስተር ፕላኑ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ያምናሉ፡፡ በ1987 ዓ.ም. በፀደቀው ሕገ መንግሥት በአንቀጽ 49(5) ላይ የኦሮሚያ ክልል የአገልግሎት አቅርቦት ወይም የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም የመሳሰሉትን ጉዳዮች በተመለከተ፣ እንዲሁም አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል መሀል የሚገኝ በመሆኑ የሚነሱ ሁለቱን የሚያስተሳስሩ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ያለው ልዩ ጥቅም እንደሚጠበቅ፣ ዝርዝሩም በሕግ እንደሚወሰን ይደነግጋል፡፡

አንዳንድ የኦሮሚያ የልሂቃን ሕገ መንግሥቱ ከወጣ ከሁለት አሥርት ዓመታት በላይ ተቆጥሮም ሕገ መንግሥቱን ተፈጻሚ የሚያደርገው አዋጅ ሳይወጣ፣ ማስተር ፕላኑን ማውጣት ለምን አስፈለገ ሲሉ ጥያቄ አንስተው ነበር፡፡ በቅድሚያ የክልሉ ልዩ ጥቅም ሊከበር ይገባል የሚል መከራከሪያም ያነሳሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ማስተር ፕላኑ ተግባራዊ እንዳይሆን የሚቃወሙ ሠልፎች በብዛት ተከናውነዋል፡፡ የሰው ሕይወት አልፏል፣ በአካልና በንብረት ላይ ጉዳት አስከትሏል፡፡

ይህን ግጭት ለማስቀረት የኦሮሚያ ክልል የማስተር ፕላን ዝግጅቱን በተለይ በልዩ ዞኑ በኩል ያለው እንዲቆም ከማድረግ በተጨማሪ፣ ክልሉ ከአዲስ አበባ ማግኘት ያለበትን ልዩ ጥቅም የሚያጠና ግብረ ኃይል ማቋቋሙ ይታወሳል፡፡

የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ፈቃዱ ተሰማ በወቅቱ ከሪፖርተር ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ኦሮሚያ ከአዲስ አበባ ማግኘት ስላለበት ልዩ ጥቅም የሚያጠና በከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮች የተዋቀረ ግብረ ኃይል መቋቋሙን አስታውቀው ነበር፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...