Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅየደርግ ዘመን ፖስተር

የደርግ ዘመን ፖስተር

ቀን:

የኅብረተሰብአዊት ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ (1967-1979)፣ በይቀጥላልም የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢሕዲሪ) መንግሥት (1980-1983) የፀረ ሙስና ዘመቻውን እንዲመራለት በ1973 ዓ.ም. ያቋቋመው ተቋም፣ ብሔራዊ የሠርቶ አደር ቁጥጥር ኮሚቴ ነበር፡፡ ኮሚቴው ኅብረተሰቡን ስለንቅዘትና ጉቦ፣ ስለግል ብልጽግና አስከፊነት ለመስበክ ልዩ ልዩ መንገዶችን ይጠቀም ነበር፡፡ አንዱ የዋናው ኦዲተር የዘመቻው አስተባባሪ ጽሕፈት ቤት ያሳተመው ይህ ፖስተር ይገኝበታል፡፡ (ሔኖክ መደብር)

* * *

ድብ ድብ

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ሀገር ማለት ሰው ነው

ሕዝብ ማለት ሀገር

ያንድ ሳንቲም ተምሳል

የዘውድና ጎፈር

ይሉትን ምሳሌ … ወስኜ ላጣራ

ድብ ተጫወትኩኝ … ከንጉሤ ጋራ፡፡

እሱ ሀገር ወካይ… እኔ ያው ሕዝብ ነኝ

የማስፈነጥራት… ድምብሎም የሌለኝ፡፡

እሱ አሽቀነጠረ… ሽቅብ ወረወረ

መልሶ ቀለበ… ከመዳፍ አኖረ

ጥያቄው ይኼ ነው

ከጁ መሀል ያለው

ዘውዱ ነው? ጎፈር ነው?

ጥያቄው ይኼ ነው፡፡

ዘውዱን በአምበሳ… አጥሮ ለከበበው

ጥያቄም ጥያቄ… ጥያቄም መልሱ ነው፡፡

ብዬ ግጥም መጻፍ… መጻፍ ጀመርኩና

ጀምሬ አቋረጥኩት… ተደናገርኩና፡፡

  • አንዱዓለም ጌታቸው ‹‹ዮሬካ››፣ 2008

‹‹በፍቅር ንክሻ›› ምክንያት የሞተው ወጣት ቤተሰቦች ፍቅረኛውን ተጠያቂ አደረጉ

የ17 ዓመቱ ጁሊዮ ጐንዛሌዝ የፍቅረኛውን ‹‹የፍቅር ንክሻ›› ወይም ጥልቅ መሳም ተከትሎ በደረሰበት ስትሮክ ሕይወቱ አለፈ፡፡ የጐንዛሌዝ ቤተሰቦችም የሴት ጓደኛውን ተጠያቂ አድርገዋል፡፡

የሜክሲኮ ዜና አውታሮች እንደዘገቡት፣ ከጐንዛሌዝ በሰባት ዓመት የምትበልጠው ጓደኛው የተደበቀች ሲሆን፣ ለጐንዛሌዝ ሞት ምክንያት የሆነውም፣ የንክሻ ያህል ስማው በነበረበት ሥፍራ ደሙ በመርጋቱና ወደ ጭንቅላቱ የረጋ ደም በመዘዋወሩ በገጠመው ስትሮክ ነው፡፡

በፍቅር ግንኙነት መካከል የሚኖር ጥልቅ መሳሳም ወይም ንክሻ ለስትሮክ ያጋልጣል ተብሎ ባይገመትም፣ እንደዚህ ዓይነቱ ገጠመኝ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን ዘገባው ያሳያል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2011፣ የ44 ዓመቷ ኒውዚላንዳዊት የግራ እጇን ለማንቀሳቀስ ተቸግራ ሆስፒታል ሄዳ ነበር፡፡ በወቅቱም ዶክተሮች መጠነኛ ስትሮክ ገጥሟት እንደነበር፣ ይህም ‹‹በፍቅር ንክሻ›› ወይም በመሳሟ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የሕክምና ባለሙያዎቹ እንዳሉት፣ ሴቲቷ አንገቷ ሥር በጥልቅ በመሳሟ/በመመጠጧ ምክንያት ከሰውነቷ የወጣው ፈሳሽ ዋና የደም መዘዋወሪያዋን ጐድቶታል፡፡ ይህም ደም እንዲረጋ ያደረገ ሲሆን፣ የረጋው ደም ወደ ልቧ በመሄዱ መጠነኛ ስትሮክ ገጥሟታል፡፡ ይህ ግራ እጇ እንዳይንቀሳቀስ አድርጓል፡፡  

* * *

በጋብቻ በቆዩባቸው 52 ዓመታት ተመሳሳይ ቀለም ያላቸው የለበሱ ጥንዶች

የልብስን ቀለም ከጫማ ወይም ከቦርሳ አዋህዶ መልበስ የተለመደ ነው፡፡ ጥንዶቹ የ76 ዓመቱ ኢድ እና የ74 ዓመቷ ፍራን ደግሞ የልብሳቸውን ቀለም ከጫማ ወይም ከቦርሳ የሚያመሳስሉት ለየግላቸው ሳይሆን፣ የሁለቱንም ነው፡፡

ጥንዶቹ ላለፉት 52 ዓመታት የውስጥ ሱሪያቸውን ጨምሮ በየቀኑ ለብሰው የሚወጡትን ልብስ ቀለም አመሳስለው ተጠቅመዋል፡፡ በዚህም በአካባቢያቸው የታወቁ ሲሆን፣ ልጃቸው ሪቺም ‹‹ሁሉም ሰው በየቀኑ እናትና አባቴ ምን ዓይነት ለብሰው እንደሚወጡ ለማየት ይጓጓል›› ሲል ለሲኤንኤን ተናግሯል፡፡

የጥንዶቹ የልጅ ልጅ የአያቶቹን ፎቶ በትዊተር ከለቀቀ በኋላ ጥንዶቹ ይበልጥ ታዋቂነትን አትርፈዋል፡፡ ማክሰኞ ነሐሴ 24 ቀን 2008 ዓ.ም. ትዊት የተደረገው የጥንዶቹ ፎቶና ታሪክ በጥቂት ቀናት ብቻ በ34,369 ሰዎች ተመልሶ ትዊት ተደርጓል፡፡

* * *

በሪዮ ኦሊምፒክ ወርቅ ላገኘችው ኬንያዊት መንደር ኤሌክትሪክ ተዘረጋ

በኦሊምፒክ የሚያሸንፉ አትሌቶች ከሚያገኙት ሜዳል በተጨማሪ በየአገራቸው ሲመለሱ፣ መሬት፣ መኪና ገንዘብና የተለያዩ ስጦታዎች ከመንግሥታቸው ብሎም ከግለሰቦች ያገኛሉ፡፡ በኬንያ የተፈጠረው ግን ከዚህ ቀደም ከነበረው ልማድ የተለየ ነው፡፡ በሪዮ ኦሊምፒክ በ1,500 ሜትር የሴቶች ሩጫ የወርቅ ሜዳልያ ተሸላሚ የሆነችው፣ ፌዝ ኪፕያጐን፣ ለመንደሯ ነዋሪዎች መብራት እንዲዘረጋ ምክንያት ሆናለች፡፡

የኪፕያጐን አባት ሳሙኤል ኪፕያጐን፣ ሩጫው ከመካሄዱ አስቀድሞ፣ ‹‹ልጄ ስትሮጥ እንዳይ ለመንደራችን መብራት ይግባልን›› ብለው የአገሪቱን ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታን ጠይቀዋል ሲል ዴይሊ ኔሽን ዘግቦ ነበር፡፡ ዘገባው በወጣ በማግስቱ፣ የፌዝ መንደር በሆነችውና በኬንያ ናኩሩ ግዛት በምትገኘው እንዳቢት መንደር የኤሌክትሪክ ዝርጋታ ተጀምሮ ከዘጠኝ ቀናት በኋላም ተጠናቋል፡፡ መንደርተኛውም የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኗል፡፡ የፌዝ አባት መብራት ቢያገኙም፣ ቴሌቪዥን ስላልነበራቸው ስትሮጥና ስታሸንፍ አላዩም፡፡ ይህንንም ተከትሎ ፊዝ በቀጣይ የሚኖራትን ውድድር ቤተሰቦቿ መከታተል እንዲችሉ፣ ቴሌቪዥን እንደሚለግሳቸው ሳምሰንግ ቃል መግባቱን ኢንዲያ ቱዴይ ዘግቧል፡፡ ፌዝ ከሪዮ ስትመለስ ቀይ ምንጣፍ ብቻ ሳይሆን መንደሯም በመብራት አሸብርቆ ነበር የተቀበላት፡፡

* * *

በፖሊስ በመፈለግ ላይ ያለች አውስትራሊያዊት ሚዲያዎች የተሻለ ፎቶዋን እንዲጠቀሙ ጠየቀች

የ18 ዓመቷ አውስትራሊያዊት ሚዲያዎች የሚያስተላልፉትና ፖሊስ እሷን ለመያዝ የበተናቸው ሁለት ፎቶዎች ቆንጆ ስላልሆኑ የተሻለ ፎቶ እንዲጠቀሙ ጠየቀች፡፡

ኤንዲቲቪ በድረ ገጹ እንዳሰፈረው፣ ኤሚ ሻርፕ፣ በእስር የነበረችው ከንብረት ጋር በተያያዘ ወንጀል ነው፡፡ ከሲድኒ እስር ቤት ያመለጠችው ወጣት፣ ለሕዝብ ሥጋት አለመሆኗን ፖሊስ የገለጸ ሲሆን፣ ያለችበትን ለጠቆመ ደግሞ ወረታውን እንደሚከፍል አሳውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...