Sunday, December 10, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
የሳምንቱ ገጠመኝየሳምንቱ ገጠመኝ

የሳምንቱ ገጠመኝ

ቀን:

በጥንታዊቷ ግሪክ አፈ ታሪክ (Mythology) ማይደስ የተባለ አንድ ንጉሥ አለ። ይህ ንጉሥ በአሁኒቷ ቱርክ ውስጥ ሰፊ ግዛት የነበረው ዝነኛ ሰው ነበር።

ከዕለታት አንድ ቀን ዳይኖሰስ የተባለው አማልክት መምህሩ የሆነው ሲለነስ ወይን አብዝቶ ጠጥቶ ርቆ ይጠፋል። የማይደስ ወታደሮችም ያገኙትና ወደ ንጉሣቸው ይዘውት ይመጣሉ። ለአሥር ቀናትም በቤተ መንግሥቱ ከፍተኛ መስተንግዶ እየተደረገለት ሲጋበዝ ሲደሰትም ቆይቶ ወደ ወዳጁ ዳይኖሰስ በክብር ይመልሰዋል።

ንጉሥ ማይደስ ሁሉ በእጁ የሆነ አዋቂና ባለፀጋ ንጉሥ ነው። ነገር ግን አማልክቱ ዳይኖሰስ ‹‹ምን ዓይነት ፀጋ ለዚህ ውለታህ እንድከፍልህ ትፈልጋለህ?›› ሲል ይጠይቀዋል።

የዚህ ጊዜ ማይደስ ለተመላኪው መለኛ ‹‹የነካሁትን ሁሉ ወርቅ አድርግልኝ፤›› ሲል ይመኛል።

የነካሁትን ሁሉ ወርቅ አድርግልኝ።

ንጉሡ ማይደስ እንደተመኘውም ውለታው ተከፈለው። የተሰጠውን ፀጋ ይዞ ወደ ቤተ መንግሥቱ በመመለስ ላይ ሳለ ለሙከራም በመንገዱ ያገኛችውን ድንጋዮችና ዛፎችን በሙሉ በእጁ ቢነካቸው ወርቅ ሆኑለት።

ማይደስ በደስታ በቤተ መንግሥቱ ደርሶ ምሶሶው ሕንፃው ሁሉ ሳይቀር እየነካ ወደ ወርቅነት ቀየረው። ግብዣም እንዲዘጋጅ ትዕዛዝ ሰጥቶ ትልቅ ድግስ ቢሰናዳም፣ ሊባርክ የነካው እህል በሙሉ ወደ ወርቅ ተቀየረበት።

ይባስ ብሎም በጣም የሚወዳት ሴት ልጁ አባቷን ናፍቃ ተንደርድራ ስትመጣ ጫፏን የነካት ጊዜ ወደ ወርቅነት ተቀየረች። ማይደስ ደስታው ከመቅጽበት ወደ ሐዘን ተቀየረ። መመገብ ፈጽሞውኑ አልቻለም። በልጁ ሞት ሐዘንም ልቡ ተሰበረ። በረሃብ ተንገላታ። ድካም ፀንቶበት ወደ አልጋው ቢሄድም እንዲያ በምቾት የሚያውቀው ለስላሳው መኝታ ወደ ጠንካራ ወርቅ ተቀይሮ ምቾቱን ነጥቆ እንቅልፍ ነስቶ አሰቃየው።

ማይደስ የነበረው ምርጫ ያገኘውን ፀጋ በሙሉ መልሶ ማስገፈፍ ነበርና አማልክቱ ዳይኖሰስን በድጋሚ ለመነው። ዳይኖሰስም ‹‹በፓክቶለስ ወንዝ ወኃ እጅህን ታጠበው፣ ፀጋህንም በሙሉ ታጣለህ፤›› ሲል ነገረው። ንጉሡ ማይደስ ከወንዙ ሄዶ ቢታጠብ ፀጋው በሙሉ ተገፎ የወንዝ ውስጥ አሽዋ ላይ ወርቁን በሙሉ አረገፈው። ከዚህም በኋላ ተራ የአማልክቱ አሽከር ከመሆን ውጪ ፀጋውን መልሶ አላኘውም፣ ይላል እንግዲህ የግሪኮቹ አፈ ታሪካዊ ሥነ ተረት።

በዘመናችን የነካነው ወርቅ ነው ብሎ ማመን እያመጣ ያለውን ችግር በስፋት እያስተዋልን ነው። ‹‹ከዚህ በፊት ነክቼው ወርቅ አድርጌ ሰላም አግኝቼያለሁ። ስለዚህም አሁንም የነካሁት በሙሉ ወርቅ ይሆናልና የሚሳነኝ የለም፤›› ብሎ ማሰብ ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍላል።

ይህ ምኞት የገዛ ልጅን ሕይወት ያሳጣል። ይህ ምኞት ለስላሳውን አልጋ የሚቆረቁር አብለጭላጭ ብረት ያደርጋል። ይህ ምኞት ምቹውን ወንበር የሚጎረብጥ ለመቀመጥ የሚያቁነጠንጥ እብን ያደርገዋል።

እየተስተዋለ።

‘ይህ ችግር ለኛ ቀላል ነው፣ ስንነካው ይፈወሳል’ ማለት፣ ‹‹የነካነው በሙሉ ወርቅ ይሁን!›› ብሎ መመኘት ነውና በኋላ ወደ አፍ የሚገባውም እንዳይቸግር ቆም ተብሎ ሊታሰብ ይገባል።

የተመረጡ ነገሮችን ብቻ ስንነካ ወርቅ እንዲያደርግልን እንመኝ ጎበዝ። ‹‹ለሁሉም ችግር መፍትሔው አንድ ነው፣ እሱም በእጃችን ነው፤›› ማለት ጥሩ አይደለም።
እንደማመጥ፡፡ እየተስተዋለ። ሰላም ለኢትዮጵያ!!

(ያሬድ ሹመቴ፣ በፌስቡክ ገጹ እንዳሰፈረው)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሰው ልጅ መብት መከበር ስናወራ 75 ዓመት ሞላን!

በገነት ዓለሙ ዓለም ስለሰብዓዊ መብቶች ሲያወራ፣ ሲምል፣ ሲገዘት፣ ሲፈጠም፣ ቃል...

ካልተማከለ የካፒታል ገበያ ወደ ዘመናዊና የተደራጀ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ

በእሱፈቃድ ተረፈ በአገራችን የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ...

ለማይቀረው ምክክርና ድርድር እንዘጋጅ

በያሲን ባህሩ  የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ደንብ አስከባሪዎች ደንብ ያክብሩ!

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች፣ ሌሎች የፀጥታ አካላት፣ እንዲሁም...